Get Mystery Box with random crypto!

ማዙካ ሸበጡን አውልቃለት፣ ልብሱን ቀናንሳለት አስተካክላው ልታስተኛው ስትል እሱ አስተካክሎ ሳማት፡ | ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ማዙካ ሸበጡን አውልቃለት፣ ልብሱን ቀናንሳለት አስተካክላው ልታስተኛው ስትል እሱ አስተካክሎ ሳማት፡፡ እሷም ‹‹ተው አይሆንም የነብዩን ትንቢት አስብ ያ የተባለው ልጅ እንዳይፈጠር›› ስትለው መስሚያውን ጥጥ አድርጎ ያለ ውድ በግድ ተገናኛት፡፡ እኔም ተፈልጌ ሳልሆን ሳልፈለግ፣ በትንቢት ወግ ተጸነስኩ፡፡ እስኪ ፈራጆች! እንኳን ጌታዬን የሸጥኩበት መንገድ ቀርቶ የተወለድኩበት መንገድ አይገርማችሁም? አሁን ሰው በእኔ ይፈርዳል? ብቻ አይወለድ የለ ተወለድኩ፡፡

ምን አለ ያኔ እናቴ ሆድ ውኃ ሆኜ በቀረሁ፡፡ ማዙካ በዚህ ዘመን ኖራ ቢሆን በጥቂት ገንዘብ ሜሪ ስቶፕ ታስወጣኝ ነበር፡፡ ድግሞም ትንቢት ስለነበር እሷ በነበረችበት ዘመን ምንም ልታደርግ አልቻለችም፡፡ እኔም ከች አልኩ ተወለድኩ፡፡

ፋዙካም እርግማኑንና ትንቢቱን ሽሽት ምንም የማላውቀውን ሕፃን በሳጥን ውስጥ ዱቅ አድረጎ በባህር ላይ ጣለኝ፡፡ ያልታደለ ግን ለነፍስ ያለ ያስቆሮቱ ሰው አግኝቶኝ አሳደገኝ፤ በነገራችን ላይ የአስቆሮቱ ይሁዳ የተባልኩት ከባህር ላይ አንስቶኝ ባሳደገኝ ሰው ስም እንደሆነ ቲንክ አደረጋችሁ? ኦኬ! እኔም ኃይለኛ ጦረኛ ሆንኝ፡፡ ማን አባቱ ከፊቴ ይቆማል፡፡

በል ያለኝን በካልቾ፣ የጠገበውን በእንጭብጭቢት በስግሪት መታው ነበር፡፡ /አዳሜ የእንጭብጭቢት እና የስግሪት አመታት እዛው ሲኦል ስንገናኝ አሳይሻለሁ/

እባካችሁ ደከመኝ! የሲኦሉም አሳት አቃጠለኝ! ለዛሬ እዚህ ላይ ይብቃ ነገ ሁሉንም ጥቁር ታሪኬን አጫውታቹኃለሁ፡፡ ሰላም ዋሉ እደሩ ልላችሁ ብዬ እኔ ሰላም ያለበት ቦታ ስላልሆንኩ እንደፈለጋችሁ ሆናችሁ ዋሉ እደሩ፡፡

ይቀጥላል …….

ይሁዳ ነኝ ከሲኦል!

ሚያዝያ 6-8-15 ዓ.ም
አዲስ አበባ