Get Mystery Box with random crypto!

  አስለቃሽ የቴሌግራም               ፕሮፋይል እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታ | Best disk

  አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል ሀያ  አራት▬▬



    እኔም እናት እና አባቴ በዚህ ጉዳይ ሲጣሉ ሲቸካቸኩ አባቴ አይሆንም እያለ ሲጮህ ይህ ችክችክ ወደ ሌላ ወደ ቤተሰብ ፀብ እንዳይዞር እኔዉ እራሴ መፍታት ማስታረቅ አለብኝ ብየ ወሰንኩ ግን አባቴን ማሳመኑ አደራዉ እኔ ጋር እንደሆነ ተገነዘብኩኝ ...በራስ መተማመን ይዤ አባቴ የተናገረኝን ቢናገረኝ ላልቀየም ላላለቅስ የአላህ ቀድር ከሆነ በእኔ ምንም መለወጥ አልችልም ብየ አስቤ.. እራሴን አሳምኜ በሩን ስከፍተዉ እናት እና አባቴ መቸካቸካቸዉን አቁመዉ ሁለቱም ወደ እኔ ትኩረታቸዉን አደረጉ፡፡

   ቤቱ ፀጥ አለ ማን ወሬ እንደሚጀምር አስፈራኝ ግን እኔ መጀመር እንዳለብኝ ተረዳሁ ...ወደ አባቴ ጎን ሂጄ ቁጭ አልኩኝ
    አባቴ ምነዉ እናቴ ጋር አለመግባባት ምን ተፈጠረ??? አልኩት ነገሮችን እንዳልሰማሁ ሁኜ
.....እሱም የምሰማዉ ነገር እዉነት ነዉ እንዴ??? አለኝ
.....እኔም እዉነት ቢሆን ለአንተ ደስ አይልህም እንዴ?? አልኩት
.....እሱም የጠየኩልሽን አጭር መልስ ንገሪኝ ከአፍሽ ልስማዉ አለኝ
...እኔም ከእኔ መነገሩ ጥቅም የለዉም እናቴም ነግረሀለች አዎ እዉነት ባቢ ዙበይርን ነገ እናንተን ላስተዋዉቅ ምሳ ጠርተነዋል ከነ እህቱ አልኩት
....አባቴም እኔ አባትሽ አይደለሁ?? እስከ አሁን እንዴት ሳትነግሪኝ እኔ የልጄን ሂወት መወሰን አልችልም ማለት ነዉ?? ቢሆንም ባይሆን እንዴት አንድ ቀን ሲቀረዉ ትነግሪኛለሽ ?? እኔ ከእናተ እርቄ የመንግስት መስሪያ ቤት የምሰራዉ አስተካክየ ቁርስ በልቼ ምሳ በቅጡ የማልበላዉ ለማን ብየ መሰለሽ ለአንድ ፍሬ ልጄ ለአንቺ ብየ እኮ ነዉ፡፡ በጣም ጥፋተኞች ናችሁ አዝናለሁ አለኝ፡፡
 አባቴ እዉነቱን ነዉ የቤተሰብ ፍቅር እርቆ  በአገኘዉ የወር ደመወዝ ነዉ የሚያስተዳድረን ግን ዙበይር ጋር እዚህ ደረጃ ለትዳር እንደርሳለን ብየ ትዝም ብሎኝ አያቅም..... ደግሞ ቀድሜ ብነግራቸዉ ይሆናል ብየ ባይሳካ ቤተሰቦቼ እኔን ምን ይጠረጥሩኛል ?? አጃጅሎ ተዋት ብለዉ ወይ እኔን አያምኑኝም ወይ እሱ ጋር ፀብ እንደሚኖር መዘንጋት የለብኝም፡፡
   አሁን ያለኝ አማራጭ አባቴ ያለኝን የጠየቀኝን ከመመለስ እኔ ይቅርታ ብለዉ የተሻለ መሰለኝ፡፡

  ከአባቴ ጎን ተነስቼ  ከእግሩ ስር ተደፍቼ አባቴ ጥፋተኛ ነኝ ይቅር በለኝ እኔ እንደዚህ ይከፋሀል ብየ ትዝም አላለኝ ሰርፕራይዝ ላረግህ ነበር ሀሳቤ ይቅር በለኝ እኔ ይሄ ትዳር ይሆናል ብየ አላሰብኩትም ፡፡ ለእናቴ እንኳ የነገርኳት ከሶስት ቀን በፊት ነዉ እኔ ዙበይር የሂወት አጋሬ ይሆናል ብየ አስቤዉም አላቅ አዉፍ በለኝ ብየ አለቀስኩኝ አባቴ እግር ላይ ተደፍቼ፡፡
    አረ ልጄዋ አታልቅሺ እኔ የአንቺን ለቅሶ አልፈልግም ሀገር ለሀገር የምዞረዉ አንቺ ደስተኛ እንድትሆኝ ነዉ አዉፍ ብየሻለሁ ብሎ ግንባሬን ሳመኝ
.....እኔም በደስታ እሺ የነገዉን ምሳ ፕሮግራም እዚሁ ልትገኝ ተስማማህ?? አልኩት
   አንዴ ጥያቄ ልጠይቅሽ ??አለኝ
..... ስለዙበይር ብዙ ነገር ጠየቀኝ መለስኩለት የጓደኛየ ወንድምም እንደሆነ..እናቴ እንደጠየቀችኝ
..... ሀብቱን አይተሽ እንዳይሆን አለኝ፡፡ እኔም በጭራሽ ይሄ እንዳለዉ ያወኩት ቅርብ ቀን ነዉ እኔ መስፈርቴ ብር አይደለም ነበር እኔ ማንነቴን አዉቆ ስለተቀበለ ነዉ የመረጥኩት አልኩት
    አባቴም ግን ልጄ እኔ የጠየቁኝ አሉ እሺ ከህመሟ ይሻላት እያልኩ መልሻለሁ  የነገዉን ምሳ ችግር የለም እንተዋወቃለን ፡፡ ግን ብትረጋጊ እና እኔ የጠየቁኝን ሰዎች አጥንተሽ ለምን መርጠሽ አታገቢም??? አለኝ
......እኔም ሳቅ እያልኩ አባቴ የመጡልኝ እኮ ማንነታቸዉን አላዉቅም ፀባያቸዉን ከኔ ምን እንደሚፈልጉ የማቀዉ የለኝም ዙበይር እኮ ከኔ የሚፈልገዉ ፍቅሩን እና የትዳር አጋሩ እንድሆን ነዉ፡፡ አንተን የጠየቁህ ለክብራቸዉ ለዘራቸዉ ሊጨነቁ ይችላሉ ደግሞ መቀራረብ እንጠናና በሚለዉ እኔም የእሱን ፀባይ ልወቅ ስል እሱም የኔን ፀባይ ልወቅ ሲል መቀራረብ አላህ ብዙ የከለከሉ ወንጀሎችን ልንሰራ እንችላለን ፡፡አንተ አስተዋወከን  ቀርባችሁ ተዋወቁ ነዉ የምትለን ..ቀርባችሁ ተዋወቁ  ማለት ከዚህ የባሰ ምን ይፈጠራል?? አባቴ አልኩት
   እሱም ይሄ ቂርአት ብዙ አስተምሮሻል ብሎ እየሳቀ እሺ ይሁና ልጄ እኔ የምፈልገዉ አግብተሽም ደስታሽን ነዉ አለኝ ቤቱ በደስታ አባቴም እናቴም እኔም ተቃቀፍን የቅድሙ ጭቅጭቅ በጠረንቤዛ ዙሪያ ዉይይት በመሰለ አጀንዳ በሰላም በፍቅር ተፈታ ቤታችን በአንዴ ወደ ቤተሰብ ፍቅር ዞረ ፡፡
    ቤተሰብም ጋር ሳያለቅሱ ሳይናደዱ  ተረጋግቶ ማዉራት ጥቅም አለዉ፡፡ ግን አንዳንድ እህቶቼ ይዘሀኝ ጥፋ...እሱን ካልዳራችሁኝ እታነቃለሁ በሂወት አታገኙኝም የሚሉ አሉ፡፡  ይሄ አግባብ አይደለም ማንኛዉም ቤተሰብ ለልጆቹ ክፉ አይደለም ብቻ የትዳር ሂወት ማለት ሁለተኛ ሂወት ስለሆነ ቤተሰብም በትንሹም ቢሆን ጣልቃ መግባቱ አይቀሬ ነዉ፡፡ ትዳር ጋር አለመስማማት ቢኖር ተመልሰን የምንመጣዉ ወደ ቤተሰብ ነዉ፡፡
   
እሷ እና ጠቢቡ

#እሷ
አምላክ ልጠይቅህ ፍቅር ግን ምንድነው
ያኛውም ይሄኛውም ወደድኩሽ የሚለው
የቱ ነው የወደደኝ የቱ ነው ያፈቀረኝ
አንተው መልስልኝ እኔስ ግራ ገባኝ

#ጠቢቡ
ልጄ ተባረኪ ጥሩ ጥያቄ ነው
መውደድ በጣም ብዙ ማፍቀር ግን 1 ነው
አንቺን የሚወዱሽ ተቆጥረው አያልቁም
ያፈቀረሽ ሰው ግን ከ 1 እንኳን አይበልጥም

#እሷ
እንዲ ከሆነማ አፈቀርኩሽ ያሉኝ
ከ 1 እኮ ይበልጣሉ መጥተው የጠየቁኝ
ከነዛ ሰው ሁሉ ተድያ እንዴት ልለየው
የእውነት እፍቃሪ ምልክት ምንድነው

#ጠቢቡ
በማስመሠል ዘመን ማመኑ ቢከብድም
የእውነት ፍቅርን ግን መለየት አያቅትም
ተወኝ ብትይውም ሊተውሽ ቢፈልግ
ልቡ ግን አይፈቅድም ይሄንን ለማድረግ

አንቺን እንዲተውሽ ፊት አንኳን ብትነሺው
ፊትሽን ይተውና ልብሽን ነው የሚያየው
አፈቀርኩሽ ብሎ ፅናቱ ካልታየ
የውሸት ፍቅር ነው እለፊው ባላየ

 ቅዳሜ ተሻግረን እሁድን የወፎች ጫጫታ አስተጋባ ትናንት ጀምሮ እናቴ ጋር አብሬ ደፋ ቀና እያልን ነዉ ስድስት ሰአት ላይ ስራዉን አጠቃለልን ስድስት ተኩል ሲል ከፊርዶስ ስልክ ተደወለ.... ስልኩን አነሳሁት ..ፊርዶስም ማመን የማልችለዉን በስልክ ነገረችኝ.....
ምን ተፈጥሮ ይሆን ?? የሂክማ ነገር አንዱን ፈተና ስጨርስ ሌላ የማትወጣዉ ፈተና ይመጣባታል ...


   የሂክማ ታሪክ በመጨረሻዉ ክፍል እና በማጠቃለያ ፁሁፋችን ይጠብቁን ...

---------------------------------