Get Mystery Box with random crypto!

  አስለቃሽ የቴሌግራም               ፕሮፋይል እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታ | Best disk

  አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል ሀያ  አምስት▬▬



#የመጨረሻዉ #ክፍል
   ፊርዶስ ደወለች ስልኩን አነሳሁት ...ምንም አልተፈጠረም ለወሬ አቸኩሉ
  .....ፊርዶስ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ  አንድ ነገር ልጠይቅሽ ነበር አለችኝ
......እኔም ምን ነበር ፊርዱ ??አልኳት
........እሷም ምሳ የጠራችሁን ሁለታችን ነበር ግን አንድ ሰዉ አብሬ እናንተ ጋር ካልሄድኩ አለን ምን ትያለሽ ሂኩ??? አለችኝ
.....እኔም ችግር የለም እሄዳለሁ ያለዉን አብራችሁ ይዛችሁ ኑ አልኳት
....ፊርዱም የዛሬዉ ቀን እኮ ለ ዙበይር
 ታላቅ ቀን ነዉ ትናንት ቅዳሜ አዳር እንቅልፍ ሳይወስደዉ ነዉ ያደረዉ በደስታ ተባብለን ተሳስቀን ፊርዶስ አሁን ከቤት እየመጣን ነዉ ብላ ነገረችኝ፡፡ እኛም ተዘጋጅተን ነዉ እየጠበቅናቸዉ ያለነዉ...
      ከ30 ደቂቃ ቡሀላ እቤት ደረሱ ፡፡ ወደ ቤት ሲገቡ ያየሁትን ማመን አቃተኝ የፊርዶስ እናት አብረዉ መጥተዋል ቅድም ደዉላ አንድ ሰዉ ይዤ ልምጣ ያለችዉ እናታቸዉን እንደሆነ ተገለፀልኝ ፡፡ የእኔ እናት እና አባት ብድግ ብለዉ ተቀበሉ ፊርዶስ የእኔን እናት ከእሷ እናት አስተዋወቀች አባቴንም ..የፊርዶስ እናት  እና የእኔ ቤተሰቦች ሲያወሩ ዛሬ አዲስ የተገናኙ አይመስሉም ነበር በጣም ደስ አለኝ ፡፡
     ዙበይር ግን ፈርቶ ዝም ብሏን አባቴ አብሽር ተጨዋት አትፍራ እንጂ እያለዉ ነዉ፡፡
 ከዛም ምሳችንን በልተን ጨረስን ቡናዉ ተፈልቶ ተመራርቀዉ ቡናዉን ተጠጥቶ ከጨረሱ ቡሀላ የዙበይር እናት እስኪ የመጀመሪያ ስለሆነ ማስታወሻ  ብለዉ የተጠቀለለ ስጦታ ሰጡን ስጦታዉ ለእናቴ የሚያምር ድርኢና ጎጎራ እና የሚያምር ጫማ ሲሆን ለአባቴ ደግሞ ሽቶ የዙበይር እናት አበረክተዉ ለምሳዉ ፕሮግራም አመስግነዉ ተመራርቀዉ ተለያዩ  ፡፡ እናቴም አባቴም በጣም ተደስተዉ ከአሁን ቡሀላ ምን ቀረ እንግዲህ ልጄ ያሰብሽዉን አላህ ያሳካልሽ ብለዉ አባቴም እናቴም መረቁኝ፡፡
    ማታ ላይ ዙበይር ደወለልኝ ብዙ ነገሮችን አዉርተን ሂኩ መኖሪያ ቤቴን ያከራየሁትን ሰዎቹን ቤት እንዲፈልጉ ደዉየ ነግሪያቸዉ እሺ በቅርብ ቀን ለቀዉ እንደሚወጡ ነግረዉኛል ስለሆነም ተዘጋጂ ብሎ ነገረኝ፡፡
....እኔም እሺ  አልኩት
ዙበይርም ሂክማ እወድሻለሁ አላህ ሀላሌ ስላረገኝ የአንቺ በጣም ደስተኛ ነኝ አለኝ፡፡
እኔም እወድሀለሁ ዙበይር አንተ ማለት የሂወቴ ብሩህ ተስፋየ ነህ ጥሩ ልጅ ወልደን በዲነል ኢስላም ገንብተን እንደምናሳድግ ይታየኛል ኢንሻ አላህ አልኩት፡፡ ብዙ ደቂቃዎች አዉርተን ተሰነባብተን ወደ መኝታየ አመራሁ፡፡ የእኔ እናት እና የዙበይር እናት በስልክ ማዉራት መቀራረብ ጀምረዋል በጣም ደስተኛ ነኝ
 
  ፊርዶስም እቤት መቼ ሽምግልና እንላክ ??ብላ ጠየቀችኝ ...ቤተሰቦቼን ጠይቄ የሚመችባቸዉን ቀን ቤተሰቦቼን ጠይቄ ለፊርዶስ ነገርኳት
ዙበይርም መኖሪያ ቤቱ አስለቅቆ የቤት እቃ እያሟላ ነዉ ፡፡ በስልክ ቀን በቀን እያወራን ነዉ አልፎ አልፎ በአካል እንገናኛለን ግን ተሳስመን አናቅም የወደፊት መሆን ያለባቸዉን ተወያይተን እንለያያለን....
   ሸምግልና የሚልኩበትን ቀን ቤተሰብ የሚመችባቸዉን ጠይቄ ለዙበይር ነገርኩት.....

አስታዉሳለሁ ቅዳሜ ቀን የዙበይር አባትን አብሮ በመምጣት እስከ 10 የሚደርሱ ሽማግሌዎች መጥተዉ ልጅህን ለልጄ ተባብለዉ ለዙበይር ታጨሁ ...በዛዉም የሰርጉን ቀን ተቆርጦ ሽማግሌዎቹ ተመለሱ ....በጣም በሂወቴ ደስተኛ እየሆንኩ ነዉ የዙበይር የሰራዉ የመኖሪያ ቤት ሸጎሌ መንገድ 7 አካባቢ  ነዉ፡፡ ምን የራሱ ለወደፊት አብረን ልጅ ወልደን የምናሳድግበት ቤት ነዉ እንጂ
  

የሰርጉ ቀን ደረሰ ሰርጋችንንም ..
ሁለታችንም ተነጋግረን ጦር ሀይሎች አካባቢ በሚገኘዉ  በኡማ ሆቴል ነበር ፡፡ ፊርዶስ ለኔ የመጀመሪያ ሚዜ ሆነች ሁለቱ ሚዜዎቼ ደሴ ከተማ ካሉት የአጎቴ ልጆች አረኩኝ  ..ፊርዶስ ለዙበይር መጀመሪያ የሱን ደስታ ያስቀደመች እህቱ ለእኔ ደግሞ የዲን እህቴም ጓደኛየም ..የወንድሟ ባለቤት(አይቷ)  ነኝ፡፡ ሰርጉ በሚያምር ዘመድ ጓደኛቼ በተገኙበት በአማረ ሁኔታ በኡማ ሆቴል ተፈፀመ፡፡ ፊርዶስ ጋር ከበፊቱ በበለጠ ከአገባሁም ቡሀላ ተቀራርበናል ደስ የሚል ሂወት እየመራሁ ነዉ፡፡

 አንተን ያወቅኩ ለታ
የዛን እለት ማታ
ትዝ ይልሀል ያኔ
ያወራሀኝ አንተ የወደድኩህ እኔ
ያን ምገዛውን ፈጣሪዬን ትቼ
ህጉን ተላልፌ ራሴን ሰዉቼ
      ትዝ ይልሀል ያኔ
መዉደድህ ሲያሰክረኝ
ፍቅርህ እንዲያ ሲያንገላታኝ
መውደድህ የእውነት
ማፍቀርህ የእውነት
ማውራትህ የእውነት
ሁሉም ነገር እውነት መስሎ ያዘናጋኝ
ትዝ ይልሀል ያኔ
ከቤት  ተደብቄ ምክንያት ፈጥሬ
የውሸት  ጋጋታ  አውርቼ ደርድሬ
አንተ ጋር ለመምጣት ብዙ ቀባጥሬ
  ትዝ ይልሃል ያኔ
አሁን  አስብና ያን ሁሉ መሆኔ
ፈገግ  እላለሁ አወይ ስልጣኔ
  ለካ
ፍቅር የሚሰምረው
ፈክቶ  የሚጠነክረው
ከአላህ  ጋር ሁኖ የተመሰረተ ነው
በትላንቴ አፍራለሁ በዛኛው ዘመኔ
     ግና
መሀሪው ጌታዬ እስኪ ተቀበለኝ ፀፀት  ፍራቻዬን
አዲሱን ህይወቴን ካንተ ጋ ልጀምር
አንተ የገባህበት አያውቅም  ድንግርግር

    ፊርዶስ ከእኛ ሰርግ አራት ወር ቡሀላ ስለታጨች  የምታገባበት ቀን ደርሷል ......እኔም ዙበይር ጋር ጥሩ የትዳር ሂወት መኖር ጀመርኩ፡፡ ሁሉም ወንድ አንድ አይደለም ለምን ሁሉም ሴት አንድ ስላላይደል...አንድ ሰዉ የምንቀርበዉ የምንወደዉ ሰዉ ሲሸዉደን መጥፎ ስራ ሲሰራብን ጥሩ ሰዉን ማመን ስለሚያቅተን ሂወታችን ህልማችን ዳግም  አይሳካም በሚል እኔ ዙበይርን ላጣዉ ነበር፡፡ የሰዉ ልጅ ነን እና እንሸወዳለን ግን ከተሸወድን ቡሀላ በዛ ነገር ላይ ቋሚ ወንጀለኛ መሆን የለብንም ወደ አላህ መመለስ መቻል አለብን፡፡ ዙበይር ጋር በደስታ በፍቅር እየኖርኩ ነዉ .. በቅርብ ቀን ደግሞ ፊርዶስ ልታገባ ነዉ እኔም የመጀመሪያ ሚዜየ አንቺ ነሽ ተዘጋጂ ብላኝ ዝግጅት ላይ ነኝ፡፡

እህቶቼ  ብዙ ሴቶች በቻት የሚያወሩ አሉ ቻት እና የተለያዩ group እንደ እኔ እንደሚጎዱ ከመቶ አንድ የሚቆጠሩ እንደዙበይር ያሉ ወንዶችን ለማግኘት በቻት ሳይሆን በዱአ ነዉ እንጂ በቻት አይደለም ቻት የዚና መስመር ነዉ እንጂ የትዳር መስመር የሚጀመረዉ በኒካህ ነዉ፡፡ አንዴ በራስሽ ፍቃድ ሂወትሽን አበላሽተሽ ፈጣሪሽን አታማሪ ወንድንም አታማሪ መጀመሪያ ብልጥ መሆን ያለብሽ አንቺ ነሽ ሴት ልጅ ክብር ነሽ ..ክብርሽን በማያቁ ወንዶች ክብርሽን አትነፈጊ

ነግሬሽ ነበረ በአጥር ተንጠልጥዬ
የTelegram ወንድ ዉሽማ እንጂ
ባል አይሆንም ብዬ
  ታሪኬን እዚህ ላይ ጨረስኩኝ፡፡
---

----------------------------------------
#ተ........ #ፈ....... #ፀ....... #መ


ዉድ የቻናል ምርጥ ቤተሰቦችይህን እዉነተኛ ታሪኩን ጨርሰናል ማመስገን የምፈልገዉ ሁላችሁንም የቻናላችን ቤተሰቦች ነዉ ታግሳችሁ አብራችሁ ስለጨረሳችሁ ከልብ አመሰግናለሁ
ለአስተያየት


  
@Z_afro02