Get Mystery Box with random crypto!

  አስለቃሽ የቴሌግራም               ፕሮፋይል እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታ | Best disk

  አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል  ሀያ ሶስት▬▬


    እኔም እናቴ ጎን ቁጭ ኡልኩኝ...ሁሉንም ልነግራት ጀመርኩ ስለ ዙበይር እናቴ ዙበይር ማለት .......የፊርዶስ ታላቅ ወንድም ስለ ፀባዩ እና እስከሚሰራዉ ስራ መርካቶ ሱቅ እንዳለዉ መኖሪያ ቤትም እንዳለዉ አከራይቶት እሱ ቤተሰብ ጋር እንደሚኖር ነገርኳት፡፡
     እናቴም ጥሩ ግን ፊርዶስ በጣም ጥሩ ልጅ ናት ማሻ አላህ የነ እሱ ዘር ጋር አንቺ መጋብትሽ ደስ ይለኛል፡፡ ግን ልጄዋ አለችኝ በስስት እያየችኝ የወደድሽዉ ብር ስላለዉ ሱቅ ስላለዉ መኖሪያ ቤት ስላለዉ ነዉ ወይ ?.. አንቺ በብር አስበሽ ከሆነ አላህ ያይሻል አንቺ በብር የምትገዢ ሸቀጥ አይደለሽም እኔ የምፈልገዉ ኢማን ያለዉ አንቺን ወዶሽ በፍቅር ተሳስራችሁ ልጅ ወልዳችሁ የአንቺን ደስታ ማየት ነዉ እንጂ ገና እሱ ብር አለዉ ብለሽ አስበሽ የትዳር አጋር የመረጥሽዉ ከሆነ ልጄዋ ይቅርብሽ፡፡ እኔ ዲን ያላቸዉ አብራችሁ ማደግ የምትችሉ ሁለት ሰዉ ቅርብ ቀን ልጅሽን ዳሪኝ ያሉኝ አሉ፡፡ ልጄ እኔ የምፈልገዉ የአንቺን ደስታ እንጂ ወንድ ልጅ በብር ሀይል አግብቶሽ የሀብታም እስረኛ እንድትሆኝ አልፈልግም አለችኝ፡፡
.....እኔም እናቴን ምንም አላልኳት ወሬዋን አስጨረስኳት እዉነቷን ነዉ ትዳር ማለት ሁለተኛ ሂወት ማለት ነዉ እንጂ እንደ ሆቴል ገብቶ ተጠቅሞ የሚወጣበት ሂወት አይደለም፡፡ እናቴ ልክ ነሽ ግን ዙበይርን በብዙ ነገር ፈትኘዋለሁ እናቴ ብዙ ለአንቺ መንገሩ ጥሩ መስሎ ያልታዩኝ ሂወቶች ነበሩኝ..... ዙበይር ነዉ የተረዳኝ እሱ በብሩ የማይተማመን እኔ ለራሱ ይሄ ሁሉ እንዳለዉ የሰማሁት ቅርብ ቀን ነዉ ...የቀረበኝ ፍቅሩን ይዞ ትዳርን አስቦ እንጂ ይሄ ቤት አለኝ መርካቶ ሱቅ አለኝ ብሎ አንድ ቀን አዉርቶኝ አያቅም ማሚ በዲኑም ጎበዝ ነዉ ፡፡ የሚገርምሽ እንደ አንዳንድ ወንዶች አይደለም እናቱ ምሳ አዘጋጅተዉ ጠርተዉኝ አስተዋዉቆኛል፡፡ ለእናቱ የወደፊት ሚስቴ ናት ብሎ አሳዉቋል ማሚ እናቱም ወደዉኝ ስጦታ ሰጥተዉኛል ..ዙበይር የሚፈልገዉ እኔን ማጃጃል ሳይሆን ወደ በሀላል ወደ ትዳር ለመግባት ነዉ፡፡ እኔ ወድጀዋለሁ አንቺም ዉደጅልኝ ማሚ አልኳት፡፡
 
....እናቴም እኔ አንቺን እወድሻለሁ የወደድሽዉንም እወዳለሁ የምጠይዉንም እጠላለሁ ግን አንድ ፍሬ ልጄ ነሽ ጥሩ ትዳር እንዲኖርሽ እፈልጋለሁ ድል ባለ ሰርግ ነዉ የምድርሽ ግን ዙበይርን አምነሽበታል??? አለችኝ
...እኔም አዎ እናቴ ዙበይር ነዉ ምርጫየ ብየ ብዙ ነገሮችን አጫወትኳት ያዉ የሚደበቀዉ ያለ ሁኖ መቼም እናቴ ናት እና ሀይደር ጋር ያሳለፍኩትን እና በዛ ነገር ሀኪም ቤት የተኛሁበትን ሂወት እኔም እናቴም እንድታስታዉሰዉ አልፈልግም........

በመጨረሻም እናቴ እሺ አላህ ያሳካላችሁ አለችኝ
......እኔም ደስ አለኝ ደግሞ ደስታየን እናቴ እንዲህ ብላ ጨመረችልኝ፡፡ ዙበይር አንቺን ለእናቱ ካስተዋወቀሽ በጣም ጎበዝ አስተዋይ ልጅ ነዉ እኔንም እሁድ ምሳ አዘጋጅተን ዙበይርን አስተዋዉቂኝ እሁድ ንገሪዉና ምሳ እንጋብዘዉ   እህቱ ፊርዶስም አብረዉ ይምጡ  ...እኔም ነገ ጠዋት ደዉየ ለአባትሽ እቤት እንደመጣ እነግረዋለሁ .. አባትሽም ይወቀዉ ነገ ከሰአት መጥቶ ከአባትሽ ጋር እንመካከርበታለን  ብላ እናቴ አስደሰተችኝ

እኔም እናቴ ጋር ተቃቅፈን ሁለታችንም በጣም ደስ አለን ፡፡ እሁድ ለመድረስ ገና አራት ቀናቶች አሉ፡፡ እናቴ ለአባቴ ደወለችለት መምጣት የሚመቸዉ ቅዳሜ እንደሆነ ነገራት፡፡ ቅዳሜ አደራ እንዳቀር ለአስቸኳይ ጉዳይ ነዉ የምትፈለገዉ አለችዉ እናቴ...
.....አባቴም ለመስማት ጓጉቶ አሁን በስልክ ንገሪኝ ቢላት አይሆንም በስልክ ተነግሮ አያልቅም በአካል ስንገናኝ ነዉ የምነግርህ አለችዉ...
   ወዳዉ መኝታ ቤት በመግባት ለዙበይር ደወልኩለት ሁሉንም ነገር ነገርኩት እና እናቴ እሁድ ምሳ ትዉዉቅ እናድርግ  ብላኛለች እሁድ ይመቸሀል ከነእህትህ?? አልኩት
......እሱም በደስታ እንዴት አይመቸኝ ቤተቦችሽን ለመተዋወቅ ዝግጁ ነኝ አለኝ፡፡
.......ከዛ ለፊርዶስ ደወልኩላት ብዙ አዉርተን ...እሁድ ስላት .....ወሬየን አቋርጣ ሂኩ ታዘብኩሽ አለችኝ
ምን ሆንሽ ፊርዱ ??አልኳት
.....እሷም የምሳ ግብዣዉን መጀመሪያ ለኔ ሳትነግሪ ለወንድሜ ነግረሽ ነዋ ከእኔ እና እሱ መጀመሪያ ያወቅሽዉ እኔን አይደል ብላኝ ተሳሳቅን፡፡

የማይደርስ የለም ነገ እሁድ ነዉ ዛሬ ቅዳሜ ላይ ነን ቅዳሜ ሙሉቀን ጀምረን እኔ እና እናቴ ለእሁዱ ባሌን የማስተዋዉቅበት የምሳ ፕሮግራም ደፋ ቀና እያልን ነዉ ..አባቴንም ሸዋ ሮቢት ስለሚኖር እሁድ እቤት ምሳ ተዘጋጅቷል ምክንያቱ ስትመጣ ይነገረሀል ብለን ቅድሚያ ስለነገርነዉ ቅዳሜ ማታ እቤት ገባ፡፡

     እቤት እንደገባም ስለ ነገዉ እሁዱ የምሳ ፕሮግራም እናቴ ነገረችዉ ግን አባቴ እና እናቴ በነገዉ ምሳ ላይ የተስማሙ አልመሰለኝም ፡፡ አባቴ ጮክ ብሎ ይሄማ መቼም አይሆንም እኔ ፈቅጄ ልጄን አልሰጥም አንቺ እኔ ሳልፈቅድ ትድሪያት እንደሆነ አያላሁ...እዚህ ቤት ወንዱ ወይ አንቺ ወይ እኔ እንሆናለን አትሰቢዉ እኔን የጠየቁኝ ሰዎች አሉ እንደዉም ለአንዱ ቃል ገብቸለታለሁ ትምህርቷን ስጨርስ ብየ አሁን ከህመሟ ከሻረች እኔም አንቺን አማክርሻለሁ እያልኩ ነበር በስራ ተወጣጥሬ ነዉ እንጂ ዛሬ ላማክርሽም ነበር፡፡ ለአስቸኳይ ስትይኝ ጭራሽ ልጄ ታገባለች ብየ ትዝም አላለኝ፡፡ ወደድሽም ጠላሽም እኔ መቼም አልስማማም እኔ ለመረጥኩት ሰዉ ነዉ ልጄን የምድረዉ ...የነገዉም ምሳ ፕሮግራም እኔ አልኖርም እንደፈለጋችሁ ማረግ ትችላላችሁ...ተስማምቼ እሱን እኔ አልተዋወቅም፡፡ እናተ እሱ እቤት መጥቶ ብትተዋወቁ እኔ እና አንቺ ፍች ነዉ የሚለየን...እኔ ከሀገር ሌላ ሀገር በመንግስት ስራ የቤተሰብ ፍቅር ሳላይ በግዥ በሁቴል ምግብ የምኖረዉ አንቺ እና ልጄ እንድትደሰቱ እንዳትከፉ እንጂ ለራሴ መኖር መች አቃተኝ...ስለሆነም ይሄ የትዳር ነገር መቼም የማይሆን ነዉ ሲል እዉጭ ሁኜ ሰማሁት፡፡

የኔ ፈተና ብዙ ነዉ እኔም ከቤት ዉጭ ሁኜ ደንግጬ ቆምኩኝ...የማወራዉ ጠፋኝ ነገ ምሳ ዙበይርን ጠርቸዋለሁ....ትዳር ቤተሰብ ስቆ መርቆ ሲሰጥ ነዉ አለመግባባት ቢኖር ተመልሰን የምንመጣዉ ወደ ቤተሰብ ነዉ፡፡ ቤተሰብ ለወደደዉ ስቆ ደስተኛ ሁኖ ካልሰጠ ቡሀላ የሆነ ነገር ቢፈጠር ሌላ የቤተሰብ ጫና ይፈጠራል፡፡

....የሂክማ ፈተና በዛ አሁን ደግሞ አባቷ እኔ ያልኩት ካልሆነ አታገባም አለ..ዙበይርም ምሳ ተጠርቷል ምን ይፈጠር ይሆን በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን


✎ ክፍል  ሀያ አራት ከ 400 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :
@melkam_lboch11