Get Mystery Box with random crypto!

  አስለቃሽ የቴሌግራም               ፕሮፋይል እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታ | Best disk

  አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል  ሀያ ሁለት▬▬




        እምባሺን ጥረጊ ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በእጁ እምባየን ጠረገልኝ......አይን አይኔን እያየ ሂኩ ብቻ ዉደጅኝ አንቺን ማጣት አልፈልግም ..እኔ እስከማንነትሽ አንቺ ጋር ጥሩ የፍቅርሽ ተካፋይ የትዳር አጋሪ ልትሆኝ ዝግጁ ነሽ?? አለኝ......
ዙበይር እኔ እኮ ....እንዳጨርሺዉ ጨረስን እኮ እኔ የምፈልገዉ ፍቅርሽን ዲንሺን እንጂ ደምሽን አይደለም ሸይጧን አሳስቶሽ የሰራሽዉ ወንጀል ተዉበት አርገሻል...... ኢነሏሀ ዩሂቡ ተዋቢነ ወዩሂቡ ሙተጦሂሪን ተብሎ የለ አንድ ሰዉ ወንጀል ይሰራል ይሳሳታል ፡፡ ነብዩሏህ አደም ዐ.ሰ ተዉ ይሄን ፍሬ አትብላ ተብሎ በልቶ አይደል ከጀነት የተባረሩት....ሸይጧን በፊት ስሙ አብዱረህማን አልነበር አርሽን ሁሉንም ሰግዶበታል ስንዝር ያልሰገደበት አይገኝም ግን ኩራት ይዞት ከጌታዉ ተጣልቶ ሰዎችን ለማሳሳት ተነስቷል፡፡
       ስለሆነም ሂክማ ወንጀል እንደሆነ እያወቅሽዉ ትሸወጃለሽ ስንት ሰዉ በአለበት ወንጀል ሳይቶብት በሰራዉ ወንጀል ሲመፃደቅ እየኖረ አይደል?? ስለሆነም አንቺ ቶብተሽ ወደ አላህ ተመልሰሻል ማታ ማታ ስታለቅሺ ዱአሽ እኔም ዱአ ሳደርግ የዱአ ዉጤት አላህ እኔ እና አንቺን አገናኘን ስለሆነም እኔ አንቺን በማሰብ መርካቶ በቅጥረኛ ሰራተኞች ነዉ ልብሱ ሲሸጥ የሚዉለዉ እሺ በይኝ እና እኔም ወደ ስራየ ጥቅልል ብየ ገብቼ ስራየን ልስራ አለኝ፡፡
......እኔም የደስታ እምባ እያነባሁ እሺ ዙበይር እኔም እወድሀለሁ አፈቅርሀለሁ የወደፊት ሚስትህ ከአላህ ጋር እሆናለሁ አልኩት ...አላቅፈዉ አልስመዉ ገና ነዉ የእኔ እና እሱ ነገር ለመተቃቀፍ ለመሳሳም ኒካህ ያስፈልገናል፡፡

ዙበይር በጣም ደስ አለዉ የሚሆነዉ ጠፋዉ በደስታ ከእኔ ፈጠን እያለ መሄድ ጀመረ እንደገና ከሄደ ቡሀላ ቁሞ ጠበቀኝ ፡፡ እሱም አይስመኝ አያቅፈኝ ገና ነዉ ግድ ኒካህ ማረግ አለብን...
ዙበይርም ይሄን ደስታየን ለፊርዶስ ልደዉልልላት አለኝ፡፡
እኔም አዎ ደዉልላት አልኩት
ለፊርዶስ ደዉሎ ዛሬ ደስተኛ ነኝ ተሳካ እኮ አላት.... ፡ፊርዶስም ዙበይርም በጣም ተደሰቱ የሚያስቀኑ እህት እና ወንድም በጣም ደስ ሲሉ....

በአንቺ ክሶኛል
በ ዘ አዶኒ ባርኮት
‹………………..….......…›
አሁን ደስ ብሎኛል ተደስቻለሁ
የልፋቴን ዋጋ ምላሽ አጊቻለሁ
ከከበረው ሁሉ ትበልጭብኛለሽ
ከቶ አልችልም ተመን ላወጣልሽ
ወጥቴ ወርጃለሁ ብዬ ፍቅርሽን
ግን አልተቻለኝም ማሸነፍ ልብሽን

ቢደከምልሽ የሚገባሽ ፍጥረት
ፀባዬ ሰናይ  ነሽ በእውነት
ስሜቴን አክብሬ ሳልጎዳ ስሜትሽን
ፍቅርን ፍለጋ ጠንቻለሁ ደጅሽን
ሃሳቤ ነጉዶ ልቤ ብሎ አንቺን
ዓይኖቼ ናፍቀው ለማየት ዓይንሽን
ተስፋ አድርጌ አምኜው ፍቅርሽን
ስጠብቅ ነበረ መምጫ ቀንሽን

ዛሬ ግን ተሳካ ቀን ወጣልኝ
በሩን ከፈተና ልብሽ ልቤን ታደገልኝ
አሁን ደስ ብሎኛል ተደስቻለው
ያ ሁሉ አለፈና ሰላም አጊቻለው
ፍፁም የነፃ በደል ያልቆጠረ
ከወርቅ ከአልማዝ እጂግ የከበረ
ቸርነትን የሚያደርግ የማይሰስት
የማያስመስል የሚጠላ ወረት

የልቤን አይቶ ጥማት ረሃቤን
አንቺን አመጣሽ አዝኖ ሃዘኔን
እውነተኛ ፍቅር ፅናት ይጠይቃል
በለሷን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል
እድለኛ ነኝ እኔ አምላክ የረዳኝ
ጥማቴን አይቶ አንቺን የሰጠኝ
ተደስቻለሁ ፍቅሬ አሁን ደስ ብሎኛል
ያከበርኩት ፍቅር ባንቺ ክሶኛል፡፡

ሂኩ ከአሁን ቡሀላ ጊዜ መስጠት አያስፈልግም እኔ እቤት ላሳዉቅ ነዉ አንቺም ለቤተሰቦችሽ  አሳወቂ አለኝ ፡፡ እኔም እሺ አሳዉቃለሁ መቼ እናሳዉቅ?? አልኩት
...እሱም እኔ እንኳ እናቴ ታቃለች እናቴን በፊት አማክሪያታለሁ በህልሜ ሂክማ ስል አይደል የማድረዉ አለኝ ...ሁለታችንንም ተሳሳቅን....
አንቺ አሳዉቂ ለኔ ቀላሌ ነዉ ተባብለን ወደ ገርጂ የሚሄድ ታክሲ አስይዞኝ ተለያየን፡፡ በሒወቴ እንደዛሬዉ ቀን ተደስቼ አላቅም ዙበይር በጣም ወደድኩት ለካ ሁሉም ወንድ አንድ አይደለም...

፡ሁሉንም ወንድ አንድ ነዉ እያልኩ ተስፋ ቆርጬ ነበር ግን እንደነዙበይር አይነት ወንዶች እንዳናገኝ እንደ ሀይደር ያሉ ወንዶች ግርዶ ሽፋን ይሆንብናል..እኔ ሂወቴ የሚስተካከል አይመስለኝም ነበር..ግን በዙበይር እንደገና ህልሜ ሊሳካ ሆነ አልሀምዱሊላህ... ታክሲ ላይ ሁኜ ሀሳብ ገባሁ የዛሬዋ ቀን ለኔ ተስፋ የሰነቀች ቀን ናት፡፡

   መቅሪብ አካባቢ እቤቴ  ደርስኩ ስገባ እናቴን ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጥቼ ገብቼ ግንባሯን ሳምኳት፡፡ መቼም እናቶች በኛ ፊት ላይ ደስታን እና ሀዘንን ማንበብ ይችላሉ
........እንዴ ልጄ ዛሬ ምን ተገኘ ??ደስተኛ ትመስሊያለሽ አለችኝ
 .....እኔም እናቴ መንገድ ላይ ዙበይር ጋር ያየችኝ መሰለኝ ፍርሀት ተሰማኝ ፊቴ በደስታ አብርቷል ገና እናቴን ሳልነግራት በፊቴ አወቀችዉ......
  እኔም እንዴት አወቅሽ??? አልኳት
.....እናቴም ዛሬ ልጄ የተገኘ ነገር አለ ማለት ነዉ ቀርበሽ እንደ እናት አዉርተሽኝ አታቂም እኮ ስገቢም ግንባሬን ከሳምሽኝ ቆየሽ ከመታመምሽ በፊት ነበር እኮ ግንባሬን የምስሚኝ ..... እስኪ ዛሬ የተገኘዉን ታጫዉችኛለሽ እርግጠኛ ነኝ አዲስ ነገር አለ ማለት ነዉ አለችኝ፡፡
ለነገሩ ዛሬ እቤት አገባቤ በጣም በደስታ ስለሆነ እናቴ ፊቴን አንብበዋለች ግን ዛሬ የደስታ ቀኔ ነዉ ዙበይርም ጋር ዛሬ እቤት እናሳዉቅ ተባብለን ነዉ የተለያየነዉ፡፡
.....እናቴን እሺ መቅሪቢን ሰግጄ አንድ የማማክርሽ ጉዳይ አለ እናወራለን ብየ መኝታ ክፍሌ ገብቼ መቅሪቢን ሰግጄ ወደእናቴ ጋር ሳሎን ተመልሼ እናቴ ጎን ቁጭ አልኩኝ፡፡
....እናቴም ፀጉሬን እየሻሸች ዛሬ ምን ተገኘ ልጄ??? አለችኝ
.....እኔም ዝም ብየ ቀረሁ አፌ ላይ ወሬዉ እያለ መተንፈስ ተሳነኝ
....እናቴም አይዞሽ ወይ እኔ ልጀምርልሽ እንዴ ???አለችኝ
እኔም......... እሺ ጀምሪዉ አልኳት
......የትዳር ጥያቄ የመጣልሽ መሰለኝ ባልሳሳት አለችኝ
....እኔም እንዴ ማን ነገረሽ?? አልኳት
.....እናቴ ሳቀች  ማንም አልነገኝ ግን ስመጪ ፊትሽ የደስ ደስ ይዞ ነበር የገባዉ ፡፡ ደግሞ ባለፈዉ በተከታታይ  አዳሬን ጥሩ ህልም አይቸልሻለሁ...
ዛሬ  አዳሬንም ጥሩ ህልም አየሁ ህልሙ ተደጋገመብኝ....ያየሁትን ህልም  ዛሬ ማታ እነግርሻለሁ እያልኩ የእናትሽ ህልም አንቺዉ መጥተሽ ሳልነግርሽ ህልሙን ፈታሽዉ አለችኝ፡፡
እኔም እናቴን እቅፍ አርጌ ሳምኳት ...እናቴ በደንብ አዳምጪ ሁሉንም ልነግራት ጀመርኩ ስለ ዙበይር እናቴ ዙበይር የሚባል ልጅ እንድንጋባ ጥያቄ አቅርቦልኛል ....... ዙበይር ማለት .......

✎ ክፍል  ሀያ ሶስት ከ 300 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ
#ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :
@melkam_lboch11