Get Mystery Box with random crypto!

  አስለቃሽ የቴሌግራም               ፕሮፋይል እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታ | Best disk

  አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል  ሀያ አንድ▬▬




  ወደ አምስት ሰአት አካባቢ ከቤት ልብሴን ቀያይሬ ፊርዶስ ጋር አብረን ጉዟችንን ቀጠልን ..ፊርዶስም ዛሬ ምሳ እኔ ነኝ የምጋብዝሽ ብላኝ መገናኛ አካባቢ የሚገኝ  ኢስላም ሬስቶራንት(ምግብ ቤት ) ገባን፡፡ ስንገባ ግን ያየሁትን ማመን አቃተኝ አሁንም ዙበይርን ነበር ያገኘሁት፡፡ ፊርዶስም ዛሬ እስኪ ምሳ አንድ ላይ ሁነን ልጋብዛችሁ ብየ ነዉ አለችን፡፡
...... ምሳችን አዘን በላን....

ከዛም ምሳ በልተን ከምግብ ቤቱ ወጣን ፡፡ ሶስታችን ከመገናኛ ተነስተን እግራችን ወደ አመራን እየተጓዝን ነዉ...ትንሸ እንደሄድን ዙበይርም  ፊርዶስን እስኪ ሁለታችን የምናወራዉ ወሬ አለን አየር ትለቂልናለሽ አላት
...ፊርዱም ከእኔ ደብቀህ የምታወራዉ አለ ዙበይር ------እሺ ካልክ እገነጠላለሁ :: ብቻ የህዝብ ተወካዮች የፓርላማ ዉይይት እንዳታረጉት ብላ እየተሳሳቅን ገንጠል አለች
    እኔ እና ዙበይር ብቻ ቀረን ሁለታችንም ተፋፈርን በዝምታ ብዙ መንገዶች ተጓዝን ማን ወሬ ይጀምር የተባባልን ይመስል አንዳችን የወሬን መጀመሪያ መክፈቻ ዙበይር ተነፈሰ ..
....... የዛሬዉ ምሳ እንዴት ነበር ???አለኝ
.......እኔም አሪፍ ነዉ አላህ ይስጣት እህትህ ጋበዘችን አልኩት
.....እሱም ግን እኔ መኖሬን ብታቂ  ፊርዶስ ብነግርሽ ትመጪ ነበር???? ብሎ ጠየቀኝ
....እኔም እንጃ ግን እህትህ የምትለኝን እሰማለሁ ፊርዶስን የማያት እንደ እህቴ ነዉ፡፡ ስለሆነም ፊርዶስን ያለችን እንቢ የምልበት ድፍረት የለኝም አልኩት፡፡
.......ማሻ አላህ እህቴን እኔም አንቺም እንወዳታለን ፊርዶስ በቤተሰብ የመጣ ትዳር አለ ግን ሁሌ የምትለዉ እኔ ከማግባቴ በፊት ወንድሜን ዙበይርን ደግሼ ድሬዉ ነዉ የማገባዉ ትላለች ፡፡ የእኔ እና እሷ አስተዳደግ የተለየ ነዉ ተከታታይ ስለሆን ተዋደን ነዉ ያደግነዉ ..አሁንም ድረስ ወንድሞቼን ሁሉንም በአንድ አይን ብታይም እሷ ግን እኔ ጋር አስተዳደጋችን የተለየ ስለሆነ በጣም ነዉ የምንዋደደዉ ሚስጥር አደብቀኝም እኔም አልደብቃትም አለኝ፡፡
......እኔም ፊርዶስን እንደ እህቴ ነዉ የማያት የምደብቃት የለኝም አልኩት፡፡
አሁን መፈራራት የለም ሁላችንም ግልፅ ሁነን እያወራን ነዉ፡፡
......ዙበይርም ግን ይሄን  ጥሩ ፀባይ  ይዘሽ እስከአሁን እንዴት ነዉ እንደ እኔ በፍቅር የወደቀ አላስቸገረሽም??? እንዴ አለኝ እየቀለደ ....
      እኔም ለዙበይር ምንም ላልደደብቀዉ ወስኛለሁ፡፡ እኔም የፈነዳ የመኪና ጎማ ይመስል ኡፍፍፍ ብየ
#የት_ይደርሳል_የተባለዉን_ዛፍ_ቀበሌ_ቆረጠዉ፡፡ አልኩት፡፡
.....ዙበይርም ማለት አልገባኝም??? አለኝ
.....እስከ አሁን የት እደርስ ነበር ግን በመሀል ዛፍም ያድጋል ብለሀዉ ሲቆረጥ ማደጉ ያቆማል ይደርቃል  የኔም ሂወት እንደዛ በለዉ አልኩት
..ዙበይርም እንዴ እንደ እሱ አይደለም ዛፍ ሲቆረጥ ሌላ ያወጣል ያቆጠቁጣል አለኝ
...እኔም የኔ አቆራረጥ እንዳያቆጠቁጥ ነዉ ብቻ በሂደት ያንን ማስረሻ እህትህን ሰጠኝ አልሀምዱሊላህ አልኩት
...እሱም በአላህ ተወኩል ነዉ አላህ ያለዉ ነዉ የሚሆነዉ ደግሞ ያሰብሽበት ግብ ለመድረስ የትናንት ትናንት ነዉ አሁን ያለሽዉ አሁን ላይ ነዉ ያለፈ ትዝታ ትርፉ ቁጭት ነዉ፡፡ የወደፊት ራዐይ ግን ተስፋ ነዉ አለኝ፡፡
.....እኔም ኢንሻ አላህ ግን እስከ አሁን አንተ ለምን አላገባህም ???? ማስተዳደሪያ ብርም አለህ ነጋዴ ነህ መኖሪ ቤትም አለህ አከራይተህ ነዉ የምትኖረዉ ለምን እስከ አሁን አላገባህም??? አልኩት
    እሱም እኔ የምመኘዉ ዱአየ አላህ የምወዳትን ልጅ መጀመሪያ የወደድኳትን የትዳር አጋሬ አርግልኝ ነበር የምለዉ .....ግን ብዙ አመታት ማንም ሴት ልቤ ዉስጥ ገብቶ አያቅም ነበር....ግን ከትንሽ ወራት በፊት አንዲት ልጅ ወደድኩኝ ግን ምን ዋጋ አለዉ ፍቅሩ እኔ ጋር ብቻ ሆነ ፡፡ የአንድ ሰዉ መዉደድ ማለት በአንድ እጅ እንደማጨብጨብ ነዉ ዱአ አርጊልኝ ልጅቱ እንደምወዳት እንድትረዳኝ አለኝ፡፡
......እኔም እንደዚህ ሲለኝ እንዴ እኔን ነዉ ወይስ ሌላ ናት ብየ ተወዛገብኩ ለምን እንደሚወደኝ አቃለሁ ደግሞ እኔ ጋር ሁኖ ስለ ሌላ ሴት ያወራኝ መሰለኝ
....እኔም እስከ አሁን ስትወድ የመጀመሪያህ የሆነችዉን ለማግባት ወስነሀል ማለት ነዉ?? አልኩት

እሱም አዎ ወስኛለሁ ልጅቱን እኮ ታቂያታለሽ አለኝ፡፡
...እኔም ማን ናት??? አልኩኝ ፈጠን ብየ
........እሱም ገምች አለኝ
......እኔም መገመት አልችልም አንተዉ ንገረኝ አልኩት
....እሱም ሂኩ አንቺ ነሽ ለምን አትረጂኝም አንቺ በፍልጥ ካልሆነ በፈሊጥ አይገባሽም ማለት ነዉ?? አለኝ ፈገግ እያለ.....
     ግን አንተ እኔን የወደድክብኝ ምክንያት መስፈርቱ ምንድን ነዉ ዙበይር እንዴት የትዳር አጋርህ እንድሆን መረከኝ???? አልኩት...
......እሱም ሂኩ እኔ ከሆነሉም የወደድኩሽ ግልፅነትሽ እና ዲን ስላለሽ የዛሬወን ሳይሆን የነገዉን ሂወት የምታስቢ ነሽ ፡፡ ፊርዶስ በጣም ትወድሻለች ታከብርሻለች ፊርዶስ የወደደችዉ ለኔ የወደፊት ትዳሬ ከሆነ ደስተኛ ነኝ ፡፡ ፍቅር መቼ ?የት ?እንዴት ?ከየት? ወደ የት? የማይባል ግዑዝ ነገር ነዉ አላህ ፍቅሬን በሀላሉ አድርጎ የትዳር አጋሬ ብትሆኝ እድለኛ ነኝ ሂኩ አለኝ
......እኔም የደስታም የሀዘንም እንባ ከየት መጣ ሳይባል በአይኔ እንደምንጭ ዉሀ ኩልል እያለ ወረደ .... ሳለቅስ ዙበይር ደነገጠ ምን ሆንሽ ??መናገር የለብኝም ነበር እንዴ?? ምን ላርግ ተቸግሬ ነዉ ሂኩ አለኝ፡፡
ያለቀስኩት በእሱ መወደዴ የደስታ እምባ ሲሆን በተዘዋዋሪም እኔ ደግሞ ለትዳር ብቁ አይደለሁም ዙበይርን እኔም እወደዋለሁ ግን የኔ እንደማይሆን በማሰብ በዉሸት መዉደድ ጉድ የሰራኝ ሀይደር እዉነተኛ እኔን የሚወድ ሳገኝ  የተደበላለቀ ሁለት ስሜት ያለዉ እምባ ነዉ፡፡
    ግን ዙበይርን ልዋሸዉ አልፈለኩም፡፡ ልነግረዉ ወሰንኩ እሱም አረ በፈጠረሽ አታልቅሺ አታስጨንቂኝ ይለኛል ዙበይር፡፡
.....እኔም እምባየን በክሪሜ አበስ አድርጌ >>>>>> ዙበይር እኔ ለአንተ አልሆንህም ሌላ ፈልግ እኔ አንተን ባገባህ ደስ ይለኝ ነበር ግን ....ብየ ልቀጥል ስል
.......ሂክማ አሁን ያለነዉ ዛሬ ጋር ነዉ ሁሉንም ፊርዱ አስረድታኛለች ......እምባሺን ጥረጊ ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በእጁ እምባየን ጠረገልኝ......አይን አይኔን እያየ ሂኩ ብቻ ዉደጅኝ አንቺን ማጣት አልፈልግም
ዛሬ ቁርጤን ንገሪኝ ሂክማ እኔ እወድሻለሁ..እኔ እስከማንነትሽ ተቀብየ አንቺ ጋር ጥሩ የፍቅርሽ ተካፋይ የትዳር አጋሪ ልትሆኝ ዝግጁ ነሽ ???...የአንቺን ልብሽ ዉስጥ ያለዉን ስለ እኔ ያለሽን ስሜት ንገሪኝ ...ዛሬ ዉሳኔሽን አሳዉቂኝ አለኝ....

✎ ክፍል  ሀያ ሁለት ከ 300 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ
#ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 :
@melkam_lboch11