Get Mystery Box with random crypto!

  አስለቃሽ የቴሌግራም               ፕሮፋይል እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታ | Best disk

  አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል ሀያ▬▬



        እኔም ቀጥታ ወደ ቤት ሄድኩኝ.......እቤቴም ደረስኩኝ ዙበይር ሲደዉልልኝ ስልክ አላነሳሁም ነበር....መልሳ ፊርዶስም ደወለች ግን ለእሷም ማንሳት አልፈለኩም መረጋጋት ስላለብኝ እንባየን ጠረኩኝ እና እቤቴ ቁርአኔን ቀርቼ ኢሻን ሰግጄ ተኛሁኝ፡፡  ከሱብሂ ቡሀላ ትንሽ ጋደም እንዳልኩኝ ጠዋት ላይ የፊርዶስ ስልክ ተደወለ ግን ማንሳቱን ፈራሁ ለምን ማታ ወንድሟን አስቀይሜዋለሁ.......ከአሁን ቡሀላ ከእኔ ተስፋ ቁረጥ ብየዋለሁ ግን እኔ ዙበይር ጠልቸዉ አይደለም በፊት የሰራሁት ስራ እኔን የበታች አርጌ ስለማይ እንጂ......
   ለፊርዶስ ደግሞ እንደነገራት እርግጠኛ ነኝ ለምን ለእሷ ምንም ነገር አይደብቃትም ....ፊርዶስ ደግማ ስደዉል ...አላስችለኝ አለ ለምን ፊርዶስ የኔ ምርጥ ጓደኛየ ባለዉለታየ ሀሳቤን ያካፈልኳት የሀሳቤ ተካፋየ ነች...ከዛም ስልኩን አነሳሁት ሰላማታ ከተለዋወጥን ቡሀላ
.... ፊርዶስ እየቀለደች አሁን ስልክ አላነሳም ያልሽኝ እቤትሽ አካባቢ መሆኔን አይተሽኝ ነዉ እንዴ ??አለችኝ
እኔም ወላሂ በይ ሰፈራችን መጥተሻል እንዴ?? አልኳት
....እሷም እኔ ግቢያችሁ በር ላይ ነኝ መቆርቆሩ ደብሮኝ ነዉ መጥተሽ ክፈችልኝ አለችኝ
...እኔም ምንም ጊዜ ሳልፈጅ ሂጄ የግቢዉን በር ስከፍተዉ ፊርዶስ ቁማለች ...ከዛ የተራራቁ ዘመዶች ይመስል ተቃቀፍን  ወደ ቤት ገባን እናቴ ጋር ሰላም ከተባባሉ ቡሀላ  ቁርስ አልበላሁም ነበር እናቴ ቁርስ አዘጋጅታ አብረን በላን...

ቁርስ በልተን ከጨረስን ቡሀላ እናቴ ወደ ዉጭ ስትወጣ  ፊርዱም እየቀለደች ትናንት የት ለመድረስ ነዉ ያን ያህል እሩጫ?? እኔ ደግሞ ሂክማ የመቶ ሜትር ሩጫ አለባት እንዴ??  መቼም አንደኛ ወጥተሽ ተሸልመሽ እንደሆነ ሽልማቱን ለማየት ነዉ የመጣሁት አለችኝ እየቀለደች፡፡
ወይ ፊርዶስ ቀልዷ በጣም አሳቀኝ እኔ የጠበኩት ለምን ዙበይርን እንደዛ ጥለሽዉ ተናግረሽዉ ትሄጃለሽ ብላ የምትቆጣኝ መስሎኝ አይኗን ለማየት እየፈራሁ ነበር፡፡ እኔም ሳቅ ብየ ዝም አልኳት ጥሩም ክፉም አልተናገርኩም.....መቼም ዙበይር እንደሚነግራት አልጠራጠርም...

ፊርዶስም ሂክማ አንቺም እህቴ ነሽ ክፉሽን አልወድም ጥሩሽን ነዉ የምወደዉ...ዙበይር ወንድሜ ነዉ የእሱንም ክፉንም አልወድም ስለሆነም ትናንት የተፈጠረዉን ነገር ነግሮኛል ...የአንቺን ጉዳት አቃለሁ እሱ ደግሞ አንቺን ወዶሻል በዚህ የሚቀጥል ከሆነ  ከአንቺ በላይ እንደሚጎዳ ነዉ የሚታየኝ  ወንድሜ ደግሞ በፍቅር ሲንገላታ ሲያለቅስ ማየት አልፈልግም ....አንቺን መዉደዱን እንኳን  እናቴ ታቃለች ዙበይር በህልሙም ሂክማ ሲል ነዉ የሚያድረዉ፡፡ እናቴ ለምን አታገባም?? ብላ ጠይቀዋለች ..
....መስመር ላይ ነኝ ዱአ አድርጊልኝ ነዉ ሁሌ መልሱ  ፡፡ እናቴም ቀን በቀን ስትጠይቀዉ አንቺን እንደሚወድ እና አንቺን ማግባት እንደሚፈልግ ነግሯታል፡፡ የትናንትናዉ የምሳ ግብዣ እናቴ ሂክማን ማወቅ አለብኝ አንቺን ለማወቅ ጓጉታ ሂክማን አስተዋዉቂኝ የወደፊት የልጄን ሚስት ብላኝነዉ..ስለሆነም አንቺም ወንድሜን ተረጂዉ እየወደደሽ አንቺን ቢያጣ አሁን ባለበት ሁኔታ ወንድሜ ሰዉ አይሆንም፡፡ ለወንድሜ እኔ እመሰክርለታለሁ ሴትን ልጅ ቀጥ ብሎ የማያይ ዲን ያለዉ ሰዉ አክባሪ ነዉ ..ስለሆነም ሁለታችሁም ተግባቡ ሂክማ ...አላህ ፅፎላችሁ ይሆናል ስለሆነም ወንድሜ ጋር አብራችሁ ብትኖሩ ደስ ይለኛል አንቺ ለኔ የልብ ጓደኛየ ለወንድሜ ደግሞ የትዳር አጋሩ ስትሆኝ ደስ አይልም እንዴ አለችኝ፡፡

ደግሞ ስለአለፈዉ ማንነትሽ ያቃል ስነግረዉ አዝኖ የብስ ፍቁሩ ጨመረበት ሂክማ አለችኝ.......

      ካልደበረሽ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ሂኩ?? አለችኝ..
.....እኔም እሺ ጠይቂኝ አልኳት
...በእስከአሁኑ ቆይታችሁ ዙበይርን ትወጅዋለሽ አትወጅዉም ???አለችኝ
......እኔም የምመልሰዉ አጣሁ በእርግጥ ዙበይርን ወድጀዋለሁ ግን ለወደፊት አብረን የምንሆን ስለማይመስለኝ እሱን ልርቅ ወስኛለሁ ለምን በሀይደር የሴትነቴን ክብር አጥቻለሁ በዙበይር ደግሞ ሁለተኛ ፍቅር በሚባል መጎዳት አልፈልግም ብየ ወስኛለሁ፡፡
.....ፊርዶስም መልሽልኝ እንጂ አለችኝ
........እኔም አዎ እወድዋለሁ ግን....ስል ወሬየን አቋረጠችኝ

ሰባራ ነው ልቤ~

በፍጹም ቅንነት ከልብህ ቀርበኸኝ
የ ሃሳብ ተካፋይ እህትህ አድርገኸኝ
የሆዴን ብሶት በዝርዝር ስነግርህ
ቁስልህ ስለሆነ ቁስሌ አመመህ
ብዙ አይነት ፈተና ቢፈራረቅብኝም
ያን ሁሉ መከራ ችየ አሳልፌም
ግማሹን ታሪኬን በአፌ ስነግርህ
ያለፍኩትን ዘመን ዳስሼ ሳወራህ
ድንገት ሳላስበው ብሶት አስለቀሰኝ
መሆኑ ሳይገባህ በአንተ ህይወት ውስጥ እራሴን አጊቼ
አብሽሪ አልከኝ ማልቀሴ ቢመስልህ ላንተ ተከፍቼ
በጥርሴ ደብቄ የያስኩት ሚስጥር
ታሪኬ ሰፊ ነዉ ገብቶ ሲመዘብር
ያለፍኩትን ህይወት ብነግርህ በዝርዝር
እንዴት እንደሆነ ሰውን አምኖ ማጣት
ቁልጭ ብሎ ታየኝ የልቤ ስብራት
የኔ ነገር ብዙ ነው አንዴ ላጫውትህ
ያንጀቴን የሆዴን ውስጤን ልንገርህ
እናትና እህትህ ባለቤት ልሁንህ
ሰባራውን ልቤን ከሰባራው ልብህ ልገጣጥመውና
አንተም በኔ ድነህ እኔም ልሁን ደህና
ሃሳቤን ዘርዝሬ ልነግርህ አልኩና
ተመልሼ ተውኩት ደግሞ ፈራሁና
ምን አልባት ምን አልባት ህልሜ ይከሽፍና
ማገገሚያ ባጣስ በሰባራው ልቤ ዳግም እጎዳና


.......እኔ የምፈልገዉ እሱን መዉደድሽን ብቻ ነዉ ..ሌላ ምክንያት አልፈልግም አለችኝ...

ከተመቸሽ ዛሬ የምንሄድበት ቦታ አለኝ ፍቃደኛ ከሆንሽ እቤት ስራ ከሌለሽ እንሄድ አለችኝ....እኔም እሺ አልኳት


✎ ክፍል  ሀያ አንድ ከ 300 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch
11