Get Mystery Box with random crypto!

  አስለቃሽ የቴሌግራም               ፕሮፋይል እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታ | Best disk

  አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል አስራ ዘጠኝ▬▬



     ከፊርዶስ ጓደኛ ከሂክማ የበለጠ ቆንጆ አዲስ አበባ ብፈልግ አታገኝም ብለዉ ሁሉም ሲስቁ ነገሮች ሁሉ እኔን እንደሆነ ጠረጠርኩ፡፡

ከዛም ምሳ በልተን ጨረስን ግን ሌሎቹን ሁለቱን የፊርዶስ ወንድሞች እቤት የሉም፡፡ ይሄ program ለኔ እና ለዙበይር በዛዉም እናቲቱ እኔን እንዲያቁኝ የተዘጋጀ ዝግጅት መሰለኝ፡፡
   እስከ አሱር ድረስ እነሱ ቤት ፊርዶስ እና እናቷ ጋር እየተጨዋወትን ቆየን፡፡ አሱር እነሱ ቤት ሰግደን ወደ ቤት ልሂድ ተነሳሁ.... ላደረጉልኝ የምሳ ግብዣ አላህ ይስጥልኝ ብየ ከቤት ልወጣ ስል ..... የዙበይር እና ወይዘሮ ዚነት ልጄ እስኪ አንድ ጊዜ ከመኝታ ክፍል እቃ ይዤ ልምጣ ጠብቂኝ ብለዉ ወደ መኝታ ክፍል ገቡ
እኔም እሺ አልኩኝ
.....ማዘር መጡ የሚያምር አበያ ሰጡኝ ልጄ ልበሽዉ የልጄ ፊርዶስ ጓደኛ አይደለሽ በትንሹም ቢሆን ማስታወሻ ይሁን ይሄን አበያ  ባየሽ ቁጥር እኔን እያስታወሽ ዱአ እንድታረጊኝ እና መጥተሽ እንድዘይሪኝ እፈልጋለሁ እኔ ከአንቺ ዝምድናዉን እፈልጋለሁ ብለዉ ግንባሬን ሳሙኝ፡፡
እኔም ማዘር አመሰግናለሁ ብየ ተቃቅፈን ተለያየን ፡፡ ፊርዶስ እና ዙበይር እኔን ሊሸኙኝ አብረዉ ከእነሱ ቤት ወጥተን ጉዟችንን ጀመርን ..

እያወራን እየተጠዋወትን እየሄድን ፊርዶስ አንድ የምታቃት ልጅ አግኝታ አሰላሙ አለይኩም ተባብለዉ ተዘያየሩ እዛዉ ቁመዉ ማዉራት ጀመሩ፡፡
 ፊርዱ እደርስባችሇለሁ እየሄዴችሁ ጠብቁኝ ከምቆሙ አለችን ፡፡ እኔና ዙበይር ብቻ ሁነን ወደ ፊት ጉዟችንን ቀጠልን ከአሁን አሁን ፊርዱ ትመጣለች ብየ ብዞር እዛዉ ቁማለች እርምጃ በተራመድን ቁጥር ፊርዶስን እየራቅናት መጣን እኔ እና ዙበይር ብቻችንን ሆንን ፡፡ ዙበይርን ወድጀዋለሁ ግን የበፊት ማንነቴ ያስፈራኛል ....እሱም እንደሚወደኝ አዉቃለሁ ግን ዉዴታ ሙሉ የሚሆነዉ አብሮ በትዳር መዝለቅ ሲቻል ነዉ፡፡ ብቻ እኔም ቀጥ ስል አይን ለአይን እንጋጫለን ሁለታችንም አንገታችንን እንደፋለን፡፡

ዙበይር የዝምታዉን ድልድይ ለመስበር እየታገለ ነዉ........ሂክማ ተጨዋቺ ወሬ አምጪ ፊርዶስ እንደሆነች ወሬዋን ከጓደኛዋ ጋር እያወራች ነዉ፡፡ በጣም ከእሷ ርቀት አለን የምመጣ አይመስልም  አለኝ፡፡
......እኔም እሺ እጫወታለሁ እልኩት
.........ምሳ እንዴት ነበር??? አለኝ
.............አሪፍ ነበር ጀዛከሏህ አለኩት
አንድ አንድ እያልን በወሬ ተግባባን፡፡ ግን በመጨረሻ ከበድ ያለ ጥያቄ ጠየቀኝ፡፡ ሂክማ ግን ሰለፍቅር ምን ታስቢያለሸ ????አለኝ .....
....ይህን ንግግሩን ስሰማ በጣም ደነገጥኩ የምመልሰዉ ግራ ገባኝ፡፡ ዝም አልኩኝ
.......ሂክማ ምነዉ የማይጠየቅ ጥያቄ ጠየኩሽ እንዴ??? አለኝ
...... አኔም ካላስቸገርኩህ የጠየከኝ መጀመሪያ አንተ ነህ ግን ይህን ጥያቄ አንተ መልስልኝ ስለፍቅር ምን ታስባለህ ???መልስልኝ እና እኔም መልስ እሰጥለሁ አልኩት፡፡
----------------እሱም ፍቅር ሳፈልጊዉ ጊዜ ሰአት ቦታ ሳይል የሚይዝ ነዉ:: ግን ችግሩ ያፈቀረዉ ሰዉ እንዴት እንደሚወድ ለተፈቃሪዉ ግልፅ አለመሆኑ ነዉ; እኔ የወደድኩትን ያፈቀርኩትን የመጀመሪያየ የሆነችዉን ልጅ   እስከ ሂወት አጋሬ የልጆቼ እናት ብትሆን ደስ ይለኛል ....አንቺሰ ምን ታስቢያለሽ???? አለኝ
  ሀይደር ጋር ያሳለፍኩት ያጠባሳ ጊዜ ትዝ አለኝ፡፡
........ከዛም ዙበይር እኔ ለፍቅር ወንድን የምቀበልበት ልቤ ዉስጥ የማስቀምጥበት ቦታ በጣም ተጎድቷል አልኩት፡፡ አንተንም የቀረብኩህ የፊርዶስ ወንድም ስለሆንክ ነዉ፡፡ አንተ ለኔ የጓደኛየ ወንድም ነህ ከዚህ ዉጭ እኔ ብዙ ያለፉ ሂወቶች የተበላሹ ማንነቶች አሉኝ እኔ ለእንደ አንተ አይነት ጥሩ ወንዶች አልገባም አልኩት፡፡ ምንም አማራጭ የለኝም እየፈለኩት የማጣት አይነት ስሜት ይሰማኛል፡፡
........ዙበይርም እኔ እስከዛሬ ደበኩት ግን መደበቄ ለኔ እንቅልፍ ነሳኝ ዛሬ ለአንቺ ልነግርሽ ዝግጁ ነኝ ሂክማ ይህን ስነግርሽ ከኔ ላትርቂ ላትሸሺ ቃል ግቢልኝ፡፡ ሂክማ እወድሻለሁ አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም እባክሽ ተረጂኝ እና ቀጥታ ወደ ትዳር እንግባ አግብቼሽ የወደፊት ሚስቴ እንድትሆኝ እፈልጋለሁ ከአንቺ  ልጆች መዉለድ እፈልጋለሁ፡፡የዛሬዉ ምሳ እናቴ የወደፊት እጮኛህን አስተዋዉቀኝ እያለች ስረብሸኝ አንቺን ስለመረጥኩ ነዉ ምሳዉ እናቴ ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ ነዉ ......አለኝ አንገቱን ደፍቶ

እኔም ዝም ብየ አንገቴን ደፍቼ የሚለኝን እየሰማሁ ነዉ ዙበይር በእድሜም እኔን ቢበልጠኝ ሶስት አመት ነዉ ከዚህ በላይ አይበልጠኝም በጣም አይናፋር ሲሆን ስራዉም መርካቶ ላይ ደርዘን ልብስ ማከፋፈል ነበር፡፡ ግን እኔ ዙበይርን ማግባት አልችልም ለምን ቢጠይቀኝ መልስ የለኝም፡፡ እኔም አንገቴን እንደ ደፋሁ እንባየ ይወርድ ጀመር
....ዙበይርም ደነገጠ
እንዴ በነገርኩሽ ነገር አስከፋሁሽ እንዴ ???እኔም ተቸግሬ ነዉ ሂክማ እንድታለቅሺ ሳይሆን እንድትረጂኝ ነዉ ፡፡
--------------እኔም ዙበይር ሌላ ፈልግ እኔ ለትዳር አልሆንህም .....እኔ እና አንተ አንድ ላይ መኖር አንችልም ብየ ከእሱ በተቻለኝ አቅም እየሮጥኩ ሄድኩኝ

.....ዙበይርም ሂክማ እያለ ሲከተለኝ፡፡ ዘወር ብየ እንዳትከተለኝ ብየ ተቆጣሁት..ዙበይርም ባለበት እንባዉ እየወረደ ቁሞ ቀረ.....

#እንዲህ #አድርጎኛል
ተፃፈ  በ ዘ አዶኒ

ፍቅርሽ እያቃዠ እንቅልፍ ያሳጣኛል
ከእህል ከውሃ ጋር ዘወትር ያጣላኛል
ሆዴን ባርባር እያለ ደርሶ ይጨንቀኛል
በዓለም ለብቻዬ የተተውኩ ይመስለኛል

በውድቅት ሰዓት ከቤት እወጣለው
ፍቅርሽን ፍለጋ ሌሊቱን እሄዳለው
ተጉዤ ሲደክመኝ ኮከብ እቆጥራለው
ለጨረቃ ሳልፈራ የሆዴን እነግራታለው
ጉልበቴን አዝሎ አቅም ነስቶኛል
ቅስሜን ሰባብሮ ወኔ አሳጥቶኛል
የፍቅር ቅጣት ህመሙ መሪር ነው
መጨረሻው ካማረ ሁሉም ለበጎ ነው

ግና እፈራለው ብኩን ሆኜ እንዳልቀር
አይሰምርም ይባላል የአንድ ወገን ፍቅር
ብቻ አለው ዛሬም እኔ እንዳለሁኝ
ህመሜን አይቶ ማንም ሳይጠይቀኝ
የሆንኩትን ሁሉ መግለፅ ቸግሮኛል
ፍቅርሽ በጥቂቱ እንዲህ አድርጎኛል፡፡


✎ ክፍል  ሀያ ከ 300 Like በኋላ  ይቀጥላል