Get Mystery Box with random crypto!

  አስለቃሽ የቴሌግራም               ፕሮፋይል እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታ | Best disk

  አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል አስራ ስምንት▬▬


      ስልኩን አነሳሁት የወንድ ድምፅ ነዉ፡፡ ድምፁም የማቀዉ ድምፅ ነዉ፡፡ ስልኩን እንደያዝኩት ደንግጬ  ቆምኩ...የደወለልኝ. ዙበይር ነዉ
አሰላሙ አለይኩም
....እኔም ወአለይኩም ሰላም አልኩት
...እንዴትነሽ.... እንዴትነህ ከተባባልን ቡሀላ በሰላም ነዉ መደወሉ?? አልኩት
...መደወል አይቻልም እንዴ ??ስልክሽን ከእህቴ ፊርዶስ ነዉ የተቀበልኩት አለኝ.... አንዳንድ ወሬ አዉርተን ብዙም በስልክ በወሬ ሳንቆይ ቻዉ ተባብለን ስልኩን ዘጋሁት፡፡
ዙበይር በኔ ፍቅር ወድቋል ከንግግሩ ያስታዉቃል በጣም ደንግጧል፡፡
ዙበይር በሂክማ ፍቅር ወድቋል ግን እስከ ማንነቷ ይቀበላት ይሆን ????
#ናፍቆት .
ናፍቀሽኛል ብዬ ቃላት እያወጣሁ
ናፍቆቴን ለመግለፅ ለናፍቆት ቃል አጣሁ
ገና ናፍቀሽኛል ብዬ ሳልጀምረው
ተሰማኝ ናፍቆትሽ ውስጤን ሲያሸብረው
እኔ የፍሬ ናፍቆት ፣ አንቺ የጥበብ ሸማ
ሲመታ አዳምጪው ያን የልቤ ዜማ
በናፍቆት አለንጋ
ደምቶ የማይረጋ
ብዙ ቅኔ ያለው ናፍቆት ሞልቶት ልቤን
ናፈቅሽኝ እላለሁ ላይገልፀው የውስጤን
የመናፈቄን ጥግ የጉጉቴን መጠን
የመውደዴን አቅም የናፍቆት ወሰን
ድንበሩን ለማየት መግለጥ ያሻው ዶሴ
ከምን ደርሶ እንደሆን ይለካ እስትንፋሴ ።

      ዙበይር እንዴት ሊደዉልልኝ ቻለ???? ለፊርዶስ ሂወቴን ከላይ እስከታች ነግሪያት እንዴት ስልኬን ሰጠችዉ ????እያልኩ ተወዘገብኩ፡፡ የማይነጋ የለም ነጋ ፊርዶስ ጋር ተገናኘን ከዛ ስለማታዉ ጉዳይ ዙበይር ደዉሎልኛል ብየ ከነገርኳት ቡሀላ .... እንዴት ለወንድምሽ የኔ ቁጥር ትሰጫለሽ??? ሂወቴን አጫዉቸሽ ነግሬሽ ወንድምሽ እኔን እንዲረሳ ማረግ ሲገባሽ ..ይባስ ብለሽ ስልክ ቁጥሬን ሰጠሽዉ ፊርዱ ጥሩ መስሎ አይታየኝም አልኳት፡፡
  ....ፊርዱም በመቆጣት ከአሁን ቡሀላ ስለ አለፈዉ ሂወትሽ ነግረሽኛል ተረድቸሻለሁ ጨዋና እና ሬድዮ ወሬ አይደጋግምም አይደል የሚባለዉ ..ወደ አላህ ተመልሰሻል ያለፈዉ አልፏል አሁን ያለነዉ ዛሬ ላይ ነን፡፡ አንድ ሰዉ ትናንት ያየዉን ህልም ዛሬ ላይ መድገም አይችልም ፡፡ ሂኩ ከአሁን ቡሀላ ያለፈ ሂወት ብታነሽብኝ የምወድሽን ያህል እጠላሻለሁ፡፡ አንቺ ለኔም ለወንድሜም ለማንም ሰዉ ወንጀለኛ መጥፎ ሰዉ አይደለሽም እንደዉም ጠንካራ ጎበዝ ነሽ ፡፡ ሲደዉልልሽ ፊት አትንሽዉ ዙበይር ወንድሜ አንቺም እንደ እህቴም እንደ ጓደኛየም የማይሽ ነሽ ሁለታችሁም እንድትጎዱ አልፈልግም አለችኝ፡፡
.....እኔም እሺ ከአሁን ቡሀላ ያለፈ ሂወቴን ላነሳ ብየ ፊርዱ አንገት ስር ጥምጥም ብየ አለቀስኩኝ፡፡

ዙበይር ጋር በስልክ ሲደዉልልኝ ማዉራት ጀመረን ዙበይር እንደሚወደኝ አቃለሁ እኔም ትንሽ ለዙበይር ከሌሎቹ ወንዶች ለየት ያለ አመለካከት አለኝ፡፡ ግን ያንን ጥያቄ ቢጠይቀኝ ምን እንደምመልስ አላቅም.... ግን ፊረዱ ያለፈዉ አልፏል አሁን ወደፊት እሰቢ ብላ አስጠንቅቃኛለች፡፡ ዙበይር እንደሀይደር ወደድኩሽ አበድኩልሽ ሳይሆን የጨዋ ወንድ አነጋገር ነበር የምናወራዉ፡፡እያደር ግን ስልክ አዉርተን ስንጨርስ ሂኩ እንደምወድሸ እንዳረሺ ማለት ጀምሯል፡፡ እኔም አረሳም ብየ እጥር ያለ መልስ እመልስለታለሁ፡፡
,
አንድ ቀን ፊርዶስ እሁድ ምሳ እኛ ቤት ጋብዠሻለሁ አንቺ እናትሽን አስተዋወቀሽኛል እናትሽ እኔን የምታየኝ እንደ ልጇ ነዉ ፡፡ እኔ እኮ አላስተዋወኩሽም አለችኝ፡፡
እናም እሁድ ምሳ ጋብዠሻለሁ ቤታችንን ስለማታቂዉ አብረን እንሄዳለን አለችኝ
፡፡ እኔም እሺ ከማለት ዉጭ ምንም አላልኩም፡፡
  

እሁድ ደረሰ ፊርዶስ እኛ ቤት መጥታ አብረን ወደ እነሱ ቤት ወደ  ጎሮ ሰፈር ሔድን ፡፡ ቤታቸዉ ደረስን ቤታቸዉ በጣም ያምራል አባቷ ነጋዴ ነዉ፡፡ ከዟም እናቷ ወይዘሮ ዚነትን አስተዋወቀችኝ ተነስተዉ ጉንጬን ሳሙኝ
... ሂክማ እኔ ልጄን ፊርዶስን በአሳታዋይነቷ በጣም እወደታለሁ ደግሞ ፊርዶስ አንቺን ትወድሻለች ልጄ የወደደችዉን እኔም እወዳለሁ በአካል ዛሬ ስላወኩሽ ደስ ብሎኛል ፡፡ ደግሞም ቆንጅየ ነሽ ማሻ አላህ ብያለሁ አሉኝ ወይዘሮ ዚነት፡፡ እኔም አመሰግናለሁ ማዘር ብየ ግንባሬን ሳሙኝ፡፡ ምሳዉ በጣም ለየት ያለ ዝግጅት ነበር ምሳዉ ቀረበ

--------- ከዉጭ አሰላሙ አይኩም የሚል ድምፅ ሰማሁ ከዛም ወደ ቤት ገባ ፡፡ ወአለይኩም ሰላም ምሳ ላይ ደርሰሀል ና ምሳ ብላ አሉት እናቱ
......እሱም እሺ ብሎ ታጥቦ እኛ ጋር ቀረበ ...እናቱም መቼ ይሆን አንተ ጎጆ መስርተህ ምሳ የምጠራን ዙበይር አሉት
.....ዙበይርም እማየ ዱአ አድርጊ መስመር ላይ ነኝ አላህ ያሳካልህ ብለሽ አላት እናቱን....
ፊርዶስም ከአፉ ቀበል አድርጋ እንዴ ትገርማለህ እኔ የማላቃት ያላስተዋወከኝ ከእህትህ ደብቀህ ያመጠሀት ሚስትማ እኔ አልስማማም አለች ፊርዱ
....ዙበይርም ከአንቺማ ምንም አይደበቅ ፊርዱ እኔ እኮ ታናሽ እህቴም ብትሆኝ አከብርሻለሁ አንቺ የወደድሽዉን ነዉ የምወደዉ አላት ለፊርዶስ፡፡

ወሬዉ እናታቸዉ ዙበይር ፊርዶስ እየተቀባበሉ ስለትዳር ነዉ የሚያወሩት እኔም የሚሉትን ሳዳምጥ ነገሮች ሁሉ ወደ እኔ ያመላከቱ መሰለኝ፡፡ እናቲቱ ማብቂያ ላይ ያሉት ንግግር ገረሞኛል መቼም ከፊርዶስ ጓደኛ ከሂክማ የበለጠ ቆንጆ በሸገር ብትፈልግ አታገኝም ብለዉ ሁሉም ሲስቁ ነገሮች ሁሉ እኔን እንደሆነ ጠረጠርኩ፡፡ዙበይር እና ፊርዶስ  እኔ እና ዙበይር ለወደፊት አብረን ለመኖር መስመር እንደጀመርን እናታቸዉ ቅድምያ ነግረዋቸዋል ማለት ነዉ ?? ይሄ ነገር ባይሳካስ?? ለእናታቸዉ ተናግረዉ ይሆን እንዴ ???እያልኩ እዛዉ እነሱ መሀል ቁጭ ብየ በሀሳብ አለም ዉስጥ ተጓዝኩኝ....


✎ ክፍል  አስራ ዘጠት ከ 300 Like በኋላ  ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 : @melkam_lboch11