Get Mystery Box with random crypto!

  አስለቃሽ የቴሌግራም               ፕሮፋይል እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታ | Best disk

  አስለቃሽ የቴሌግራም
              ፕሮፋይል

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

       ▬▬▬❁ክፍል አስራ ሰባት▬▬




........ሂኩየ አንቺ ከእነዚህ ሰዎች ትለያለሽ ወንጀል ሰርተሽ  ወደ አላህ ነዉ እያለቀሽ ያለሽዉ እንጂ ወንጀል አብራችሁ ወደ ሰራሽዉ ሰዉ አይደለም ስንት እህቶቻችን ይህን ወንጀል ሰርተዉ ወንጀል ከሰሩት ሰዉ ጋር ተጣብቀዉ አንተዉ ቅብረኝ እሞታለሁ መርዝ እጠጣለሁ የሚሉ የፈጠራቸዉን ጌታ የረሱ አሉ አይደል፡፡ አንቺ እኮ የምታለቅሽዉ ወደ ፈጠረሽ ጌታ ወደ አላህ እንጂ ወደ ሀይደር አይደለም ስለሆነም አንቺ ከሌሎቹ ሴቶች ልዩ ነሽ፡፡
ጥራት የሚገባዉ አላህ ጌታችን እንዲህ ይላል፦ የባሮችን ጉዳይ ተውልኝ እስኪ ከነሱ ወደኔ የተመለሰ (የተፀፀተ) እኔ ወዳጁ ነኝ። እኔኮ እናት ለልጇ ከምታዝነው በላይ ለባሮቼ አዛኝ ነኝ። ከነሱ ወደኔ ተፀፅቶ የተመለሰ «አንተ ተውበት አድራጊ ሆይ
እንኳን ደህና መጣህ ብየ ከርቀት እቀበለዋለሁኝ ።ወንጀል ሰርቶ ከኔ ለሚሸሸው ደግሞ፦ ወደርሱ ቀርቤ ፦ ባርያዬ ወዴት ነው የምትሄደው??? ከእኔ ውጭ ሌላ ጌታ አገኘህን??? ከኔ ውጭስ ሌላ
አዛኝ የሆነ ጌታ አገኘህን የምትሸሸኝ??? »በማለት እጠራዋለሁኝ።
እናንተ ስንዝር ስቀርቡኝ በእርምጃ እቀርባችሇለሁ ....በእርምጃ ስቀርቡኝ እኔ በሩጫ በፍጥነት እቀርባችሆለሁ  ብሏል ሂኩየ ፡፡ ስለሆነም ከአሁን ቡሀላ የአንቺን ለቅሶ ሳይሆን የምፈልገዉ ደስታሽን ነዉ ሂኩየ አንቺ ከአሁን ቡሀላ የረከሽ ወንጀለኛ አይደለሽም ልታለቅሺ ሳይሆን.... የባሰ አለ ብለሽ ልታመሰግኚ ነዉ የሚገባዉ  አንቺ ልታለቅሺ አይገባም አላህ መሀሪ አዛኝ የሆነ ጌታ ነዉ ብላ አንገቴ ስር ጥምጥም አለችብኝ፡፡ ከዛም ወደ ቤቴ ልሂድ ብላኝ ሸኝቻት ተመለስኩኝ፡፡

   ዉይ ለፊርዶስ ከነገርኳት ቡሀላ ይህ ሚስጥር ተሸክሜዉ እንዳታሳርፊ የተባልኩ ይመስል አፍኘዉ ኑሮ ቅልል አለኝ ፡፡ ዲፕሬሽን ዉስጥ ነበርኩ አንድ ሰዉ ዲፕሬሽን ዉስጥ ከሆነ መፍትሄ ይሰጠኛል ብሎ የሚያማክረዉ ሰዉ ከነገረዉ 50% ከዲፕሬሽን ይላቀቃል፡፡ የሆነ የደስታ ስሜት ተሰማኝ

ማታ ላይ ልተኛ ስል ፊርዶስ ደዉላልኝ በቃ በደስታ አወረሇት ..
.....እሷም ሂኩ ምን ተገኘ ደስተኛ ሁነሻል ??? ስትለኝ
......ምንም አልተገኘ ግን ቅልል ብሎኛል የደስታ ስሜት ተሰማኝ አልኳት ፡፡ ብዙ ነገሮችን አወራን ስንጨርስ በስልክ ተሰነባብተን ወደ መኝታየ አመራሁ
ለመጀመሪያ ጊዜ ሳልጨናነቅ ደስተኛ ሁኜ አደርኩ፡፡ የመጀመሪያ የደስታ ሂወት የጀመርኩ ይመስለኛል አልሀምዱሊላህ ተገላገልኩ..... ዙበይር ከአሁን ቡሀላ ተስፋ ይቆርጣል ፊርዶስ እዉነቱን ትነግረዋለች ወደ እኔ በጭራሽ አይደርስም ብየ እራሴን አሳመንኩት፡፡
    ሳስበዉ የቸገረን የልባችንን የምነነግረዉ ለአላህ ብለን የምንወደዉ በአላህ መንገድ በዲነል ኢስላም ያገኘነዉ ጓደኛ ነዉ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ አንድ የልብ ጓደኛ ያስፈልገዋል በደስታዉም በሀዘኑም ከጎኑ የሚሆን ሀሳብ ሲያስብ የማያማክረዉ በሀሳቡ ገንቢ አስተያየት መስጠት የሚችለዉ  ሰዉ ለሌላ ሰዉ መድሀኒት ነዉ ፡፡ ተማክረዉ የፈሱት ፈስ አይሸትም አይደል የሚባለዉ የልብ ጓደኛ ወሳኝ ነዉ፡፡ ጓደኛ ማለት በክፉም በደስታም በሀዘንም አብሮ መግባባት ሲቻል ነዉ፡፡ መጠንቀቅ ያለብን ሴቶች ማንኛዉም ነገር እስከ ዚና መስራት ወንጀል ድረስ የሴት ጓደኛ ተፅእኖ ግፊት ነዉ ጥሩ ሴቶች እየተበላሹ ያሉት በመጥፎ ሴቶች ጓደኛ ይዘዉ ነዉ፡፡ 
       የአሁን ጓደኝነት ስታማክረዉ ወይ ሚስጥርህን ለሌላ ያሳልፈዋል ወይም በቀኝ ጆሮዉ አዳምጦ በግራ ጆሮዉ ያፈሰዋል፡፡ ጫት ማን አስጀመረህ?? ጓደኛየ..የቱርክ ልብስ ማን ልበሺ አለሽ?? ጓደኛየ....የያሽዉ የወንድ ጓደኛ ማን አስተዋወቀሽ?? ጓደኛየ...ሶላት አልሰገድሽም የት ነበርሽ?? ጓደኛየ ቤት....ሜካፕ ሊፒስቲክ ኮስሞቲክስ ማን እንድትቀቢ አስለመደሽ ???ጓደኛየ.......ዚና እንድሰሪ ማን አስተዋወቀሽ ???ጓደኛየ...ነዉ መልሳችን፡፡ አሁን የያሽዉ የሴት ጓደኞችሽ ከስንት አንድ ካልሆነ ከነዚህ ዉጭ ያሉት ብዙዎቹ ሴቶች የሚሸወዱት የሚበላሹት በሚይዙት የሴት ጓደኛ ስበብ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡
     ሴትን ለሴት እሾህን ለሾህ አይደል የሚባለዉ በጓደኛ አመራረጥ ቢያንስ እንደፊርዶስ አይነት ጓደኛ መያዝ መቻል አለብን፡፡
አሁን ላይ ትዉልዱ ከቤተሰብ ቁጥጥር ዉጭ ሁነናል ጊዜዉ የተራቀቀ ነዉ በፊት ቤተሰብ ይቆጣጠረን ነበር አሁን ግን በስልክ ሁኗል ስራዉ በስልክ ያልቃል ወንጀል ለመፈፀም አንቺ እሱ እና ጌታሽ ብቻ የሚያቃቸዉ ብዙ የዚና መስሪያ ቦታዎች ምን ይሰራ ማን ይግባ ማን ይዉጣ የማይታይበት የወንጀል መስሪያ ቦታዎች በሁላችንም የመኖሪያ ሰፈሮች ቦታዎች እናገኛለን ፡፡  የሂክማ ነገር አላለቀም
                 
#እስኪ #ፈገግ #እንበል
 .....አንዷ ሁሌ ላይብረሪ እያለች ትሄዳለች አቧቱ ሲጠይቃት ሁሌ ላይብረሪ እያለች ስታስቸግር ..አንድ ቀን አባቷ ማታ ስትመጣ በብትር ይገርፋታል የት ነዉ የምትሄጅዉ ??ሲሏት ላይብረሪ ስትል...አባቷ አልተማሩም ነበር ላይም ብረሪ ታችም ብረሪ የሄድሽበትን ብቻ ተናገሪ እንዳሉት አባት ትክክለኛ መሆን መቻል አለብን፡፡
 መቼም ቀን በቀን ይፈራረቃል አንድ ቀን ባሳለፍን ቁጥር ወደ ሽምግልና እየሄድን እና ወደ ሞት እየተጠጋን መሆኑን እረስተናል፡፡ እኛ ሞትን ብንረሳም ሞት ግን እኛን አይረሳም፡፡
ካልተሳፈሩበት ቶሎ ተሽቀዳድሞ
ጊዜ ታክሲ አይደለም አይጠብቅም ቁሞ
ተብሏል፡፡ ግን አሁን ጊዜ ሰዉ ታክሲ ተሰልፎ ይጠብቃል እንጂ ታክሲ ተሰልፎ ሰዉ መጠበቅ አቁሟል፡፡ ምን ለማለት ነዉ አንተም አንቺም እሱም እሷም ሞት ቁሞ እየጠበቀን ስለሆነ ጥርት ያለ ተዉበት አድርገን ሞትን እንጠብቀዉ፡፡

ነግቶ ፊርዶስ ጋር ተገናኘን ከበፊቱ በበለጠ ፍካቷ እየጨመረ ለኔ ያላት አመለካከት እየጨመረ ሄደ ፡፡ በቃ ምን ልበላችሁ እስከዛሬ በመደበቄ እኔ ስጨናነቅ እንደኖሩኩ አወኩኝ ቢሆንም አልሀምዱሊላህ አሁንም እፎይ ማለቱ በጣም ደስታ ፈጠረልኝ፡፡
ፊርዶስ እኛ ቤት እየመጣች አንድ ላይ እንሆናለን ፡፡

አንድ ቀን እናቴ ለፊርዶስ ምንድን ነዉ አታገቡም እንዴ ፊርዱ??? ሴት ልጅ ትዳር የሚያምረዉ በልጅነት ነዉ፡፡ እኔ ያገባሁት በ19 አመቴ ነዉ ፡፡ ከሁለት አንዳችሁ አግቡ እና በሰርጋችሁ እንልፋ አለቻት፡፡ ለፊርዶስ
..ፊርዱም ኢንሻ አላህ አይቀርም እኔ የማመቻቸዉ ስላለ ነዉ እንጂ በቤተሰብ የመጣልኝ አለ ታጭቻለሁ  ሆነም ቀረ የሂክማ ይቀድማል ተዘጋጂ አለች ሳቅ እያለች
.....እናቴም ማሻ አላህ ብያለሁ ለድግሱ ልዘጋጃ ብላ ቀለድ አረገች፡፡
telegram ...Facebook ...ከገባሁ በጣም ቆየሁ ቻት የሚባል አቁሚያለሁ፡፡ ከሰለሙ ስልም ነዉ ከከፈሩ እንክፍርር ነዉ ይባል የለ፡፡ እኔም አላህ ተዉበቴን እንዲቀበለኝ ወንጀል ወደሰራሁበት ቦታ መመለስ ማየት ማስታወስ ጥሩ የወደፊት ጥሩ ህልም አያሳካም፡፡ ማታ ኢሻን ሰግጄ ቁርአኔን እየቀራሁ .....የማላቀዉ ቁጥር ተደወለብኝ እኔም ሳላነሳዉ ቀረሁ፡፡ መልሶ ተደወለ ሁለተኛ መቼም በዚህ ሰአት ሰዉ ያለምክንያት ሁለቴ አይደዉልም ብየ አሰብኩ፡፡ ከዛም ስልኩን አነሳሁት የወንድ ድምፅ ነዉ፡፡ ድምፁም የማቀዉ ድምፅ ነዉ፡፡ ስልኩን እንደያዝኩት ደንግጬ  ቆምኩ...የደወለልኝ.....
✎ ክፍል  አስራ ስምንት