Get Mystery Box with random crypto!

Adjustment Disorder ምንድነው? በህይወት ውስጥ ጫና ሲያጋጥም ጭንቀት ወይም መከፋት የ | Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

Adjustment Disorder ምንድነው?

በህይወት ውስጥ ጫና ሲያጋጥም ጭንቀት ወይም መከፋት የተለመደ ነው። ይሄ ጭንቀት ወይም መከፋት በተለምዶ ከሚጠበቀው ጊዜ በላይ ከቆየ ወይም መጠኑ ከሚጠበቀው በላይ ከሆነ Adjustment disorder (Situational depression) ይባላል።

Adjustment disorder የሚፈጥሩት ጫናዎች አንድ ጊዜ በድንገት የሚከሰቱ አሉታዊ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ፍቺ፣ የእሳት አደጋ፣ ከስራ መባረር፣ አዲስ ስራ መጀመር፣ አዲስ ቦታ መሄድ...ወዘተ። ሌላ ጊዜ ደግሞ ጫና የሚፈጥሩት ነገሮች አብረው የሚቆዩ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ትዳር ውስጥ ያለ ጭቅጭቅ፣ ነዝናዛ አለቃ...ወዘተ። ሰዎች Adjustment disorder እንዲያጋጥማቸው የሚያደርጉት መጥፎ ነገሮች ብቻ ሳይሆኑ ጥሩ ነገሮችም ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ትዳር መያዝ፣ ድንገት ሀብታም መሆን፣ ሹመት...ወዘተ።

ሰዎች ጫና ሲያጋጥመን የምንሰጠው ምላሽ እንደየመልካችን ይለያያል። ለአንዳንዶች በጣም የሚያስጨንቃቸው በሌሎች አይን በጣም ቀላል ነው። ይህንን የሚወስነው አስተዳደጋችን፣ የምንጠቀማቸው ራስን የመደለያ መንገዶች (Defence Mechanisms)፣ ያለን ማህበራዊ ድጋፍ ...ወዘተ ነው።

የAdjustment disorder ህክምና በዋናነት የንግግር የስነ ልቦና ህክምና ሲሆን በጣም አልፎ አልፎ ለጥቂት ቀናት ለእንቅልፍ የሚያግዙ መድሀኒቶች ሊሰጥ ይችላል።

በዶ/ር ዮናስ ላቀው (የአእምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት)

@melkam_enaseb