Get Mystery Box with random crypto!

#ሊታረምሚገባድርጊት በ 'Tourette Syndrome' ወይም 'tics' disorder ታካሚዎች | Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#ሊታረምሚገባድርጊት

በ "Tourette Syndrome" ወይም "tics" disorder ታካሚዎች ላይ መቀለድ

ቤተልሔም አዳሙ ያሳለፍነው እሁድ በተላለፈው የእሁድን በኢቢኤስ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ ተጋባዥ እንግዳ ሆና በመቅረብ "በገንዘብ እጦት ሚከሰት አንጃይተር ዲሶርደር ነው" በማለት መሰል ድርጊቶችን ስታሳይ ነበር።

ቤተልሔም አዳሙ በምትለቃቸው ቪዲዮዎች ከህክምና ባለሙያዎች በቪዲዮዎችዋ ምታደርጋቸው ድርጊቶች "Tourette Syndrome" ወይም "tics" disorder መገለጫ እንደሆኑ በመንገር እንድትታረም በተደጋጋሚ በፅሁፍም ሆነ ቪዲዮዎቿን በማጋራት (duet) መልእክታቸውን ሲያስተላለፉ ቆይተዋል።

በሃገራችን አሉ ከሚባሉት ታዋቂ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው EBS/ኢቢኤስ/ ልጅቷን ትልቅ አስተማሪ የሆነ ነገር ይዛ የቀረበች በማስመሰል ከአቅራቢዎቹ ጋር በልጅቷ እሳቤ እሰይ አበጀሽ አይነት ህመሙ ባለባቸው ታካሚዎች ሪአክሽን ላይ ተመርኩዘው ሲስቁና ሲሳለቁ ይስተዋላል።

ይህ አይት ድርጊት የታካሚዎቹን ስሜት የሚጎዳና ምንም አይነት ትምህርት ለትውልድ ሊያስተምር ስለማይችል ቢታረም እያልን ጉዳዩ የቴሌቪዥን ጣቢያውን በህግ ሊያስጠይቀውም ስለሚችል ተገቢውን ይቅርታ እንዲጠይቁ እናስገነዝባለን።

Via: Hakim

@melkam_enaseb