Get Mystery Box with random crypto!

የውሸት እርግዝና (pseudocyesis) or (phantom pregnancy) ምንድነው? በዶ/ | Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የውሸት እርግዝና (pseudocyesis) or (phantom pregnancy) ምንድነው?

በዶ/ር ነጋልኝ (የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት) እና ዶ/ር ሱራፌል (የስነ አዕምሮ ስፔሻሊስት) የተፃፈ።

በአንድ ወቅት የ50 ዓመት ታካሚዬ የአስራ ሁለት ወር እርጉዝ ነኝ ልጁም አልወለድ ብሏል የምጥ መርፌ ስጠኝና ገላግለኝ አለችኝ። ይህን ገጠመኝ በመንተራስ ስለ phantom pregnancy ይህን ፅፈናል። መልካም ንባብ!

የውሸት እርግዝና እርግዝና ሳይኖር የእርግዝና ምልክቶች ሲታዩ እና ነፍሰጡር ነኝ ብሎ አይምሮን በማሳመን የሚፈጠር የአይምሮ ችግር ነው።

በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የመከሰት እድሉ ግን በጣም አናሳ ነው።

የታወቀ የአዕምሮ ወይም የአካል ህመም ሳይናኖርባቸው በውል በማይታወቅ ምክንያት እርግዝና አለኝ ብሎ ማመን የሚታዩ የእርግዝና ምልክቶችን ማንፀባረቅ የዚህ ችግር ተጠቂነትን ያመለክታል።

ምልክቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦

- የሆድ መግፋት(መነፋት)
- ማቅለሽለሽና ማስመለስ
- የወር አባ መጥፋት
- ክብደት መጨመር
- የጡት መጠን መጨመር
- የምግብ ሽታ መጥላት
- የሽንት መፋጠን
- የልጅ እንቅስቃሴ መስማት

ምክነያቶቹ ምንድናቸው?

ለዚህ ችግር ምክያት ይህ ነው የሚባል ህያው መንስኤ ባይኖረውም የተለያየ አይነት ሳይንሳዊ መላምቶች ተቀምጠዋል ከእነዚህም መላምቶች የሆርሞን መዛባት፣ የአዕምሮ ጭንቀት፣ የአከባቢ ጫና በጋራ ወይም በተናጥል የሚፈጥሩት ኡደት ነው።

ተጋላጮቹ ማናቸው?

በማንኛውም እድሜና በየትኛውም ሀገር የሚኖሩ ሴቶች ሲጠቁ የሚከተሉት ችግር ይበልጥ ተጋላጭነትን ይጨምራሉ

- ከ20-39 ዓመት ያሉ
- ልጅ የጠፋባቸው
- ውርጃ ያላቸው
- የመካንነት ችግር
- የቤተሰብ እና የአካባቢ ጫና
- ትዳር ውስጥ አለመስስማማት
- የፍላጎቶች አለመሟላት
- ያለ ጊዜ ማረጥ እና የመሳሰሉ ችግሮች
እንደ አጋላጭ ባህሪያት ይታያሉ::

እስከመቼ ይቆያል?

ይህ አይነት ስሜት በአብዛኛው ከቀናት እስከ ዘጠኝ ወር ሲቆይ አስከ አንድ አመት ሊድርስ እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።

በዚህ መካከል እርግዝና የለም ሲባሉ ስለማይስማሙ ብዙ የጤና ባለሙያዎችን ይጎበኛሉ፣ ይመረመራሉ። በውጤቱም አይረኩም ሌላ ቦታ ለመታየት ይሄዳሉ ይህም ''doctor shoping'' ለአመታት ሊዘልቅ ይችላል።

የሚመሳሰሉ ችግሮች ምንድናቸው?

- Delusional pregnancy (የቅዠት እርግዝና) በአይምሮ ህሙማን ላይ የሚከሰት ሲሆን በቃ ነፍሰጡር ነኝ ብሎ ሙጭጭ የማለት ሁኔታ ነው።

- Covouid syndrome (ተላላፊ እርግዝና) ከነፍሰጡር ሴት ጋር ከመቆየት የተነሳ ነፍሰጡሯ አንዳረገዘች ያህል የሚሰማት ጊዜያዊ ሁኔታ ነው።

- Feigned pregnancy አንድ ነገር ለማግኘት (ጥቅምን ያማከለ) ሲባል እርግዝና ሳይኖር እንዳለ የማስመሰል ሁነት ነው።

መፍትሄውስ?

እስካሁን ድረስ ይህ ችግር የሚፈታ የስነ አዕምሮ መድሃኒት የሌለ ሲሆን የስነ አዕምሮ ባለሙያ እና የማህፀን ፅንስ ስፔሻሊስቶች በጥምረት በመሆን ታካሚውን መርዳት ይቻላል።

- የስነ-አዕምሮ ምክር
- ቤተሰብን ማሳተፍ
- ምርመራዎችን አድርጎ ሁኔታዎችን ግልፅ ማድረግ
- የወር አበባ ወቅቱን ጠብቆ አንዲመጣ ማገዝ
- Delusional pregnancy በስነ-አዕምሮ መድሃኒቶች ሊታከም ይችላል።

ለበለጠ መረጃ ሃኪም ያማክሩ።

@melkam_enaseb