Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ ሰሞን በምንሰግድበት ጊዜ የምጠራቸው ቃላት “ ናይናን ፤ እብኖዲ ፤ ታኦስ ፣ ማስያስ ፤ ት | 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™

በዚህ ሰሞን በምንሰግድበት ጊዜ የምጠራቸው ቃላት

“ ናይናን ፤ እብኖዲ ፤ ታኦስ ፣ ማስያስ ፤ ትስቡጣ፣ አምነስቲቲ ፣ ሙኪርያቱ፣ ሙዓግያ ፣ሙዳሱጣ "


እኒህም ቃላት ከዕለተ ሰኞ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ዓርብ ድረስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሲነበብ በሚሰነብተው ግብረ ሕማማት በተባለው ነገረ ሕማማቱን መዝግቦ ካስቀመጠው ታላቅ የቤተክርስቲያን መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው የሚገኙና ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ እንደወረደ ሳይለወጡ ተጽፈው የምናገኛቸው የዕብራይስጥ፣ የቅብጥና የግሪክ ቃላት ናቸው።

•••
ናይናን

ናይናን የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም በግዕዙ “መሐረነ” በአማርኛው “ማረን” ማለት ነው፡፡

•••
እብኖዲ

እብኖዲ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “አምላክ” ማለት ነው፡፡ “እብኖዲ ናይናን” ሲልም “አምላክ ሆይ ማረን” ማለቱ ነው

ታኦስ

ታኦስ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ ጌታ፣ አምላክ” ማለት ነው፡፡ “ታኦስ ናይናን” ማለትም በአማርኛ ትርጉሙ “ጌታ ሆይ ማረን” ማለት ነው፡፡

ማስያስ

ማስያስ ማለትም የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙም በእነርሱ ቃል “ መሲሕ” ማለት ነው፡፡ “ማስያስ ናይናን” ሲልም ” መሲሕ ሆይ ማረን” ማለት ነው።

ትስቡጣ

“ዴስፓታ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ደግ ገዥ” ማለት ነው።

አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ
በመንግሥትህ አስበኝ»ማለት ነው፡፡

አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን.«ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ - ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው።

አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

•••
በአቅራቢያችን ቤተክርስቲያን ባይኖርም ሰዓት እየጠበቅን እንዲህ እያልን የጌታን ሕማሙን እያሰብን አቅማችን በፈቀደ መጠን ባለንበት ስፍራ እንዲህ እያልን እንስገድ።
•••

•ኪርዬ ኤለይሶን ኪርዬ ኤለይሶን ኪርዬ ኤለይሶን
•ኪርዬ ኤለይሶን ኪርዬ ኤለይሶን #እብኖዲ #ናይን ኪርዬ ኤለይሶን
•ኪርዬ ኤለይሶን ኪርዬ ኤለይሶን #ታኦስ ናይን ኪርዬ ኤለይሶን
•ኪርዬ ኤለይሶን ኪርዬ ኤለይሶን #ማስያስ ናይን ኪርዬ ኤለይሶን
•ኪርዬ ኤለይሶን ኪርዬ ኤለይሶን #ኢየሱስ ናይን ኪርዬ ኤለይሶን
•ኪርዬ ኤለይሶን ኪርዬ ኤለይሶን #ክርስቶስ ናይን ኪርዬ ኤለይሶን
•ኪርዬ ኤለይሶን ኪርዬ ኤለይሶን #አማኑኤል ናይን ኪርያ ላይሶን
•ኪርዬ ኤለይሶን ኪርዬ ኤለይሶን #ትስቡጣ ናይን ኪርዬ ኤለይሶን

•••

እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ጻማ ወድካም
አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ
እግዚአብሔር በሰላም

ፋሲል ግቢ ጉባዔ
@fasil_gibi_gubae_official

መልእክት ወይም አስተያየትና ጥያቄ ካሎት @Fasil_gibi_gubae_bot ላይ ላኩልን።
https://t.me/fasil_gibi_gubae_official