Get Mystery Box with random crypto!

በሕማማት የማይፈጸሙ ተግበራት እና ሥርዓቱ ሼር በማድረግ ያድርሱ መስቀል መ | 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™

በሕማማት የማይፈጸሙ ተግበራት እና ሥርዓቱ
ሼር በማድረግ ያድርሱ
መስቀል መሳለም
የፍትሐት ጸሎት
ታቦት ማውጣት
ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ መቀደስ
መሳሳም
ዕልልታና ጭብጨባ
ሥርዓተ ማኅሌትና ከበሮ
ዝማሬ
ታቦት ማውጣት
የኑዛዜ ጸሎት

በሰሙነ ሕማማት በሌሊት የጸሎትና የስግደት ሥርዓት
ሌሊት ከስድስት ሰዓት ጀምሮ ካህናትና ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ መጀመርያ የራሳቸው ጸሎት ያደርሳሉ
ዲያቆኑ ሦስት ጊዜ እየዞረ ቃጭል ያሰማል
ይህም የሁሉም ዕለታት የጸሎት መጀመርያ ምልክት ነው
ከዚህ በኋላ በጋራ ሆነው ጸሎቱን ይጀምሩ
ካህኑ የአስርቆት ጸሎት ካደረሰ በኋላ
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አመ ከመ ዮም ብሎ አቡነ ዘበሰማያት ይሰጣል ከዚህ ቀጥለው ሰላም ለኪ ብለው ውዳሴ ማርያም ከአንቀጸ ብርሃን ጋር ይድገሙ
መልክዓ መልክዓ ማርያምና መልክዓ ኢየሱስ አይደገምም
ካህኑ ከውዳሴ ማርያም በኋላ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አመ ከመ ዮም ብሎ አቡነ ዘበሰማያት ይሰጣል

አቡነ ዘበሰማያት ከተሰጠ በኋላ በመሪ እየቀደመ በተመሪ እየተከተለ
ለከ ኃይል ይላሉ መሪና ተመሪ በግራና በቀኝ እየተቀያየሩ ያደርሳሉ
የለከ ኃይል ጸሎትና ስግደት ካለቀ በኋላ ምንባባት ይነበባሉ
ምንባባቱ ካለቁ በኋላ ምንተኑ አአስየኪ እሴተ ይባልና በሰላመ ገብርኤል መልአክን ሃሌ ሉያ ለአብንና ናሁ አግብርትኪ ከተባለ በኋላ
በአራራይ እንደ ሥርዓቱ መቅድመ ተአምርንና ተአምረ ማርያምን ተአምረ ኢየሱስስን ያንብቡ

ከተአምረ ኢየሱስ በኋላ ዲያቆኑ ምስባክ ይላል ቀጥሎ ካህኑ ወንጌል ያነባል ቀጥሎ ድኅረ ወንጌል ቀጥሎ ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ መካን ይላል

በመሪ በኩል አያይዘው ኪርያ ላይሶን ጸሎትና ስግደት እንደ ሥርዓቱ ይደርሳል ቀጥሎ የሰዓቱ መልክዓ ሕማማት ይደርሳል

ወንጌል ያነበበ ካህን ድምፁን አሰምቶ አርባ አንድ ጊዜ ኪርያላይሶን እንበል ይላል

ዲያቆኑ በዘማ ማኅዘኒ በወርድ ንባብ ሑሩ በሰላም ውስተ አቢያቲክሙ ንዑ ወተጋብኡ በጊዜ...........ሰዓተ ሌሊት(ሰዓተ መዓልት) ለጸሎት ብሎ ያውጃል
ይህ የሙሉ ሳምንት ሥርዓት ነው

በሰሙነ ሕማማት ዘነግህ
የጸሎትና የስግደት ሥርዓት
ጧት በአንድ ሰዓት ካህናትና ሕዝበ ክርስቲያን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ መጀመርያ እንደ ተለመደው ደወል ያሰማል ዲያቆኑ ቃጭሉን እያሰማ ሦስት ጊዜ ይዞራል
ካህኑ አሥርቆት ያደርሳል ከዛ ቀጥሎ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አመ ከመ ዮም እግዚአብሔር በሰላም ብሎ አቡነ ዘበሰማያት ከሰጠ በኋላ ወዳሴ ማርያም አንቀጸ ብርሃን ይደረሳል ካህኑ አቡነ ዘበሰማያት ከሰጠ በኋላ

ኦሪት ካለ መሪ አቡን ይመራል ኦሪት ከሌለ ውዳሴ ማርያም እንደ ጸለየ አያይዘው 12 ጊዜ ለከ ኃይል ይባላል በመሪ እየቀደ በተመሪ እየተከተሉ ከዘለቁ በኋላ

በመሪ ወገን ኦሪት ያንብቡ ቀጥሎ መጻሕፍተ ነቢያት ይነበባሉ ለሰዓቱ የተሰሩ ምንባባት ሁሉ ከተነበቡ በኋላ ካህኑ ምንተኑ ብሎ ስምዑ እነግረክሙ ብሎ አንድ ተአምር ያንብብ ከተአምረ ማርያም በኋላ በነግህ ብቻ ሁሉምተአምራት ይነበባሉ

ከዚህ ቀጥሎ ምስባክ ይሰበካል
ካህኑ ወንጌል ያነባል ቀጥሎ ድህረ ወንጌል ቀጥሎ በእንተ ጽንዓ ዛቲ መካን ከተነበበ በኋላ
በመሪ ክርሰቶስ አምላክነ ዘመጽ ወሐመ በእንቲአነ ወበሕማማቲሁ ቤዘወነ ይላሉ
በተመሪ ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ህቡረ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በሐማማተ ዚአሁ

ቀጥሎ ኪርያ ላይሶን ይባላል
ኪርያ ላይሶን ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይን ኪርያ ላይሶን
ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ታዖስ ናይን ኪርያ ላይሶን
ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ትሱጣስ ናይን ኪርያ ላይሶን
ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ማስያስ ናይን ኪርያ ላይሶን
ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ኢየሱስ ናይን ኪርያ ላይሶን
ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ክርስቶስ ናይን ኪርያያ ላይሶን
ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን አማኑኤል ናይን ኪርያ ላይሶን
ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ኪርያላይሶን
በመሪ 21 ጊዜ
በተመሪ 20 ጊዜ =41 ይሆናል
እስከ ዕለተ ዓርብ ድረስ በዚህ መንገድ የየሰዓቱ ስግደትና ምንባብ ይከናወናል

በአራቱ ወንጌላት ያለው ምርሃት
በማቴዎስ ወንጌል የሚመራው
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ስምዕዎኬ ለእግዚእነ ኩልክሙ አብያተ ክርስቲያናት ከመ ዘአክበሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት በወንጌለ መንግሥት እንዘ ይብል ክርስቶስ ወልደ ዳዊት አሜን አሜን እብለክሙ እስከ አመ የሐልፍ ሰማይ ወምድር የውጣ እንተ አሐቲ ሕርመታ ወአሐቲ ቅርፀታ ኢተሐልፍ እምኦሪት ወእምነቢያት እስከ ሶበ ኩሉ ይትገበር ወይከውን ይቤ እግዚእ ዘበእብራይስጢ ልሳን በወንጌለ ማቴዎስ ብርሃን ዘእምብርሃን

በማርቆስ ወንጌል የሚመራው
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ስምዕዎኬ ለእግዚእነ ኩልክሙ አብያተ ክርስቲያናት ከመ ዘአክበሮሙ ለኦሪት ወለነቢያተ በወንጌለ መንግሥት እንዘ ይብል ክርስቶስ ወልደ ዳዊት ኢይምሰልክሙ ዘመጻእኩ እስአሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት ወኢ ከመ እንስቶሙ አላ ዳእሙ ዘእንበለ ከመ እፈጽሞሙ ይቤ እግዚእ በወንጌለ ሰላሙ አማኑኤል ስሙ ማርያም እሙ

በሉቃስ ወንጌል የሚመራው
ሃሌ ሉያ ይቤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ኤንዘ ይሜሕረነ በወንጌለ ሉቃስ ወባሕቱ ይቀልል ሰማይ ወምድር ይኅልፍ እምትደቅ አሐቲ ቃል እምኦሪት

በዮሐንስ ወንጌል የሚመራው
ሃሌ ሉያ ስብሐት ለአብ ወወልድ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ በወንጌል ለዘመሐረነ በኦሪት ወበነቢያት ለዘናዘዘነ በከመ መሐረነ እግዚእነ ስብሐት ለእግዚአብሔር ከመ ናምልኮ ለዘፈጠረነ

የሰላም አምላክ ሰላሙን ያድለን

ጸልዩ በእንተ ሰላም
ስለ ሰላም እንጸልይ
ስለ ሀገራችን እንጸልይ
በጭንቅ በመከራ ስላሉት እንጸልይ
በጽኑ ሕመም ተይዘው ስላሉት እንጸልይ
ስለ ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ
የሰላም አምላክ ሰላሙን ይስጠን

አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ
ዝዋይ ገዳም -ኢትዮጵያ
02/08/2015
ሼር ይደረግ
በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw