Get Mystery Box with random crypto!

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ medhanialem — የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ medhanialem — የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @medhanialem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-14 18:14:39
351 views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 18:14:19 ምናልባት በዚህ ዓመት ከሚሄዱት ጉዞዎች ከአእምሮዎ የማይጠፋ መንፈሳዊ ቦታ ለመሄድ አስበዋል።ታዲያ
በብዙ ዓመት አንዴ በዕለተ እሁድ የሚውለውን የመስቀለ ኢየሱስን በዓል ለየት ያለ መንፈሳዊ ቦታ ብንወስድዎስ። ነፍስዎን መንፈሳዊ ሀሴትና በረከት ሞልተው መመለስ ከፈለጉና በሚቀጥሉት ዓመታት እለተ እሁድ የማይውለውንና በብዙ ሀሴት ደርሰው የሚመለሱበት መንፈሳዊ ቦታ ጉዞ አዘጋጅተናል ይህ ቦታ እንዠራ መስቀለ ኢየሱስ ገዳም ይባላል።
ከጅሩ መንፈሳዊ ቦታወች እንዠራ መስቀለ ኢየሱስ ገዳም በከፊል እናስተዋውቃችሁ!!!!!!


ሞረትና ጅሩ ወረዳ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዷነች የወረዳው ርዕስ ከተማ እነዋሪ ስትሆን ከክልሉ ርዕስ ከተማ ከባህርዳር 750 ኪ.ሜ ከመዲናችን ከአዲስ አበባ 195 ኪ.ሜ ከዞኑ ዋና ከተማ ደ/ብረሃን 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

እንዠራ ደብረ ቅዱሳን መስቀል ኢየሱስ ገዳም በሞ/ጅ/ወ በላም ዋሻ ቀበሌ በእንጀራ ጎጥ የሚገኝ ጥንታዊ ገዳም ሲሆን ገዳሙ በ1113 ዓ/ም እንደተመሰረተ የሚነገር ሲሆን ፃድቁ አባት አቡነ ዜና ማርቆስ ደብረ ብስራትን ከመገደማቸው/ገዳም ከመሆኑ/ በፊት ከአቡነ ተክለሐይማኖት ጋር በቦታው ፀልየውበታል፡፡ ገድለ ዜና ማርቆስ ገፅ 36 ምዕራፍ 5 ቁጥር 17/‹‹…ይህ ነገር የተደረገው እንዠራ በሚሏት ሀገር ኢማ ነበር፡፡ ያቺም ለዚህ ለሞረትና ጅሩ ሀገረ ገዥ የላም ዋሻ ማርቢያ ቦታ ናት፡፡››
እንዠራ መስቀል ኢየሱስ ገዳም ከእነዋሪ ከተማ በስተ ሰሜን በግምት 15 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ዋሻ ነው፡፡ ገዳሙ የሚገኘው በደንና በገደል ውስጥ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ በመሆኑ እንኳን ከርቀት ቀርቶ በአቅራቢው ሆኖ መለየት አይቻልም፡፡ አካባቢው ወጣ ገባ ከመሆኑ የተነሳ ከ200 ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ እንኳን ደኑን እንጂ ዋሻውን ማየት አይቻልም፡፡
ይህን ቦታ ከሌሎች ቦታዎች ለየት የሚያደርገው በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የሚገኘው ዋሻ ውስጥ ሲሆን ዙሪያውን እንደማንኛውም ቤተ ክርስቲያን ግንብ ሲሆን ጣሪያው ግን ዋሻው እርሱ መሆኑ ነው፡፡
በዚህ ገዳም ውስጥ የተቀበረ አፅመ ቅዱሳን አፈር አይበላውም፡፡ በእንዠራ ደብረ ቅዱሳን መስቀል ኢየሱስ ገዳም ውስጥ የተለያዩ ታሪካዊ መስህቦች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል፡-
የቅዱሳን አፅሞች
የጊወርጊስ ፈረስ ማሰሪያ የድንጋይ ምሶሶ
የመሬት ውስጥ ጉተራዎች የመሳሰሉት የሚገኝበት ቦታ ነው፡፡
ቦታው በጥንቃቄና በክብር ቢያዝ በተለይ ለሳይንስ ጥናት ምርምር ለተማሪዎች ትልቅ ትምህርትና ምርምር ቦታ እንደሆነ በርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ በተለይ አንዳንድ ጎብኝዎች ካለማወቅ የተነሳ በተለይም የ5ቱ ሰሞነኞች አፅም ፣የአካባቢው ገዥ የሆነችው የፅዮን ሳምራ እና የአቃቢቷን አፅም በተለያየ ቁስ በመንካት እያበላሹት ስለሚገኝ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ እንዲሁም የምድር ጎተራው በወቅቱ የአባቶችን ጥበብ የሚገልፅ በመሆኑ ከማድነቅም አልፈን ልንጠብቅ ይገባል፡፡
የጊወርጊስ ፈረስ ማሰሪያ እየተባለ የሚጠራው የድንጋይ ምሶሶ በራሱ ትልቅ ምርምር የሚጠይቅ ቅርስ ነው፡፡ ይህንን ቅርስ ለመጠበቅ ደግሞ የሁሉም አካል ድርሻ የራሱ የሆነ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡
የጊዮርጊስ ፈረስ ማሰሪያ
ያንን ህዝቡ የሚያመልኩበትን ዘንዶ ከገደሉ በኋላ አቡነ ዜና ማርቆስና ፣ አቡነ ተክለሃይማኖት ህዝቡን አስተምረው አጥምቀው ክርስትያን አድርገውታል፡፡ ›› (ምንጭ ገድለ ዜና ማርቆስ 9ኛ ተአምር ገፅ 234 ና 235) እንዲሁም ፅዮን ሳምራ ቤተ ክርስቲያን ካሳነፀች በኋላ ያነፀውን አሽከሯን ይህንን ሙያ እዚህ እኔጋ አትቀመጥልኝም በማለት ቀኝ እጁን አስቆርጣዋለች፡፡
የድንጋይ ምሶሶ
አቃቢቷ በጥንቃቄ መገበሪያውን ባለማዘጋጀታቸው እና ከ5ቱ ሰሞነኞች ጋር በመመሳጠራቸው አቃቢቷ እስከ ወንፊቷና እስከ ሰፌዷ በአለችበት ደርቃ ቀርታለች፡፡
አምስቱ ሰሞነኞችና አቃቢቷ እስከ ወንፊቷና እስከ ሰፌዷ
እነዚሁ 5ቱ ሰሞነኞችና ፅዮን ሳምራን አፅማቸው
366 views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 18:44:59 ለሰንበት ት/ቤታችን አባላት በሙሉ
የእህታችን ትርሲተወልድ አባት ስላረፉ ቀብር ነገ ስለሆነ ሁላችንም ሀዘን እንድንደርስ
28 views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 10:07:01
68 views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 15:20:04
99 views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 14:48:20
91 views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 11:31:02 አስደሳች ዜና ለጨሪና ሰፈራ ወጣቶች
ለጨሪ መድኃኔዓለም ቤ/ክ አካባቢ ወጣቶች ሰንበት ትምህርት ቤታችን በወር አንዴ ወርሃዊ የመድኃኔዓለም በዓል በዋለ ቀጣዩ እሁድ ከ5:00-7:00 ልዩ ወርሃዊ የትምህርትና የዝማሬ ጥናት ስለተዘጋጀ በአካባቢያቹ ባሉ ወጣት አስተባባሪዎች እንድትመዘገቡ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
230 views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 16:11:13
ሰበር አስደሳች ዜና

በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት "አባ" ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ  ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል።
በይቅርታ ደብዳቤያቸውም ሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖዶሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ።

በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሆኔን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ። በመሆኑም በዛሬው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል ።

26 _ አባ ጸጋ ዘአብ = 25
25_ አባ ንዋየ ሥላሴ= 24
ለ24ቱ ደግሞ አሁንም የይቅርታ በራችን ክፍት ነው! በሉልኝ!
አበቃ!

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube Subscribe በማድረግ አዳዲስ መረጃ ይከታተሉ!
https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

@seratebtkrstian
8 views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 19:39:03 የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው መልዕክተዮሀንስ(ምስጋናው) እናቱን ተረድቶ ስለመጣ እንደሰንበት ት/ቤት ነገ እሁድ 8:00 ሰዓት ቤቱ ስለምንደርስ እንድትገኙ።
31 views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 07:16:54
#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ

የፀጥታና ደኅነት የጋራ ግብረ–ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ መገምገሙን ገልጿል።

አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለኝ ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ " በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት አጋጣሚ እንዲፈጠር ቅስቀሳዎች እየተደረጉና ሌሎችም ግጭት ቀስቃሽተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ " ብሏል።

ግብረሃይሉ ሰልፎቹ በሃይማኖቱ ሽፋን የሚደረጉ እና ሕገወጥ ሰልፎች ናቸው ያለ ሲሆን " በሚመለከተው አካል የተፈቀደ ሰልፍ የሌለ መሆኑ ታውቆ ኅብረተስቡ ከዚህ ሕገ ወጥ ሰልፍና ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት ራሱን ይጠብቅ " ብሏል።

የጋራ ግብረ-ኃይሉ " ከዚህ ውጭ ሰልፍ አደርጋለሁ ብሎ በሕገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ኃይል እንዲሁም ሰልፎቹን ለማስተባበር እና ለመሳተፍ የሚሞክሩ አካላት ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ተጠያቂ ናቸው " ያለ ሲሆን " ለዜጎችና ለሀገር ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ሲባል ሕጋዊእርምጃ ይወሰዳል " ሲል አስጠንቅቋል።

ግብረ ኃይሉ " በየክልሉ የምትገኙ የፀጥታ ኃይሎችም በአካባቢያችሁ ሕገወጥ ሰልፎች እንዳይካሄዱ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያኗ፣ለእምነቱ አባቶች እና ተከታዮች በአጠቃላይ ለሕዝቡ ተገቢውን የደኅንነት ጥበቃ እንድታደርጉ " ሲል አዟል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
21 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ