Get Mystery Box with random crypto!

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ medhanialem — የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ medhanialem — የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @medhanialem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-12-21 13:24:20 ሀሌ ሀሌ ሉያ ሶበ ሰቀልዎ/2/ለእግዚእ/2/
አድለቅለቀት ምድር ወተከስቱ መቃብራት ፀሀየ ፀልመ/2
40 viewsedited  10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 19:44:30 የጥር 11(የጥምቀት)ወረብ
ወወፂኦ
ወወፂኦ እማይ ወወፂኦ እማይ ተርኅወ ሰማይ/2/
መጽአ ቃል እምደመና እምደመና
ዘይብል/2/
21 viewsedited  16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 09:58:34 የጥር 7 ወረብ

በፈቃደ

በፈቃደ አቡሁ ወረደ ተአንገደ በደብረ መድኃኒት /2/
በድንግልናሀ ንፁህ በድንግልናሀ ንፁህ እግዚአብሔር
ተወልደ/2/
ነአምን
ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ ወነአምን በመንፈስ ቅድስ/2/
አሀድ ውእቱ አምላክ ፍፁም አሀድ ውእቱ
47 viewsedited  06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 11:22:29 Channel photo updated
08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 21:45:57 አሳዛኝ ሰበር ዜና!
ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም በታጠቁ የኦነግ ኃይሎች እየታመሰ ነው።

የበርካታ መናንያን መኖሪያ ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም ኦነግ ሸኔ በሚል የዳቦ ስም በሚታወቁት ታጠቁ አክራሪ ኃይሎች እየታመሰ ይገኛል። ዛሬ ማምሻውን የታጠቁ አክራሪ ኃይሎች በሁሉም አቅጣጫ ወደ ገዳሙ ሰብረው በመግባት መነኮሳትን በማገት ገዳሙን እያመሱት ይገኛል።

አሁን ከገዳሙ መናኒያን ጋር በመደወል እየደረሰባቸው ያለውን እንግልት ነግረውናል። ከገዳሙ የጥበቃ ኃይሎች የሚገኙትን መሣሪያዎች በከበባ ነጥቀው፦ “የእኛ ግዛት ስለሆነ ከዚህ በኋላ እኛ ነን የምናስተዳድረው እናንተን አይመለከትም!” እንዳሏቸው ነግረውናል።

የሁሉንም መናኒያን እናቶች ስልክ ቀምተዋቸዋል። ቀድመው ከወጡት የገዳሙ አበውና እመው መናኒያን በስተቀር ገዳሙን የሚያስተዳድሩትንና በገዳሙ ለብዙ ዘመናት በጥብዓት ሲያገለግሉ የሚታወቁትን 4ቱን አግተዋቸዋል። ገዳሙን ለመታደግ "ድረሱል ድረሱልን" የሚል ድምፅ እየተሰማ ነው።

ጸልዩ በእንተ ደብረ ከዋክብት ቅዱሳን ገዳም (ዝቋላ)!!!

ለገዢው የብልጽግናው መንግሥት ግልጽ ጥያቄዎች፦
1) የሕዝብን ሰላም መጠበቅ ቀዳሚው የመንግሥት ተግባር መሆኑ አሁን በምንመራበት ሕገ መንግሥታችን ላይ በግልፅ የሰፈረ ሆኖ ሳለ በመላዋ የሃገራችን ክፍል በተለይም በኦሮሚያ ክልል ሕዝቦች ፍትሕ እንደሰማይ ርቋቸው በዘራቸውና በኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖታቸው ብቻ እገታ፣ ዘረፋ፣ የንብረት ውድመትና አሰቃቂ ግድያ ሲፈጸምባቸው አለባብሶ በዝምታ የሚያልፈው የተቀመጠበት ወንበር የሚጠይቀውን ኃላፊነት ማን እንዲያስገነዝበው ፈልጎ ይሆን?

2) መንግሥት ለሕዝብ፣ ለሃይማኖት፣ ለተራድዖና ለግል ተቋማት ተገቢውን ጥበቃና ከለላ ማድረግ የሚጀምረው መቼ ነው?

3) ብልፅግና ወንበሩን ከያዘ ጀምሮ በተለያዩ የሃገራችን ክፍል በፖለቲካዊያን አካላት በተቀነባበረ ሴራ በርካታ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት ዲያቆናትና መናኒያን ተለይተው በግፍ ሲገደሉ፣ ጥንታዊ ገዳማትና አድባራት ሲዘረፉና ሲወድሙ፣ ቁጥራቸው በውል ለመግለጽ የሚያዳግቱ ኦርቶዶክሳዊያን ሕዝበ ክርስቲያን ተለይተው በግፍ ሲገደሉ አንጀታችን እያረረ ለሃገር አንድነትና ለዘላቂ ሰላም ሲባል ዝምታን መርጠን ነበር። ከዚህ በላይ ምን እስክንደረግ ነው የሚጠብቀው? ወይስ ሆን ተብሎ ጉዳዩን ራሱ መንግሥት በሎጀስቲክ እንደሚደግፈውና ስትራቴጂውን እንዳቀነባበረው እንድናምን እየተደረግን ነው? ታዲያ በጊዜው ሥልጣኑን የጨበጠው መንግሥታዊ አካል ነገ በኃላፊነቱ እንደሚጠየቅበት ረስቶት ነው?

ለኢፌዲሪ መከላከያና ለደኅንነት መስሪያ ቤቶቻችን፦
1) እንደ ሕገ መንግሥታችን መከላከያ ገለልተኛ የሕዝብ ተቋም ነው። ነገር ግን ሕዝቦች በዘርና በሃይማኖት ተመርጠው ጉዳት ሲደርስባቸው ተገቢውን ጥበቃ ማድረግ ግዴታው እንጅ ችሮታው አለመሆኑን ተረድቶ መቼ ነው ቅድመ መከላከል የሚያደርገው?

2) በወታደራዊ ሳይንስ ገዢ መሬትን ለጠላት ማስረከብ ትልቅ ኪሳራና ሽንፈት ያስከትላል። የሃገሪቱ አየር ኃይል ቤዝ ደብረ ዘይት እንደሚገኝ ግልጽ ሆኖ ሳለ ከከተማዋ በቅርብ ርቀት የሚገኘውንና ደብረዘይትን፣ ዱከምንና አዲስ አበባን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየውን የዝቋላ ከፍተኛ ተራራ ለአማጺያን ማስረከብ የሚያመጣውን ሃገራዊ ክስረትና ውድመት ለመከላከያም ሆነ ለፌደራል ሰላምና ደኅንነት አካላት ማን ሊተነትንላቸው ፈልገው ይሆን? ዝቋላ ገዳምን በሃይማኖት ተቋምነቱ ለመጉዳት መንግሥት እጁ ካለበት ደግሞ የሃገሪቱ አየር ኃይልን ከመጠበቅ አንፃርስ የዝቋላ ተራራን ፋይዳ በወታደራዊ ሳይንሱ እንዴት ተመልክቶት ነው?

3) የመከላከያ ደኅንነት ከጎረቤትና ሌሎች ሃገራት በኩል ለሚገጥመንም ሆነ በመላዋ ሃገሪቱ ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች ቅድመ ጥናትና ትንበያ በማድረግ ለመከላከል ዝግጅቱ ያለው ፋይዳ በግልጽ ሊታይ እንደሚገባው ማን ሊነግረው ይሆን?

4) አጠቃላይ ሃገራዊ የደኅንነት መስሪያ ቤቶቻችን በውስጥ ጉዳያችን ላይ በመላዋ የሃገሪቱ ክፍል ተገቢውን ሥራ መከወን እንደሚገባቸው ሌላ ነጋሪ ያስፈልጋቸዋል እንዴ?
14 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 11:27:11
29 views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ