Get Mystery Box with random crypto!

#ዙልም ( ግፍ) የሚፈፅምን ሰው ራቅ! ኢስላም ፍትህን በሚያዛባና ግፍን በሚፈፅም ሰው ላይ ከ | Fezekir _ فَذَكِّرْ

#ዙልም ( ግፍ) የሚፈፅምን ሰው ራቅ!

ኢስላም ፍትህን በሚያዛባና ግፍን በሚፈፅም ሰው ላይ ከፍተኛ የሆነ ቅጣት እንዳለበት ይደነግጋል። ወደግፈፈኞች መዘንበልና አጫፋሪ መሆንን ፈፅሞ ይከለክላል።
የላቀው ጌታችን አላህ እንድህ ይላል:

[ وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ]


"ወደእነዚያም ወደ በደሉት አትጠጉ፡፡ እሳት ትነካችኋለችና፡፡ ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም፡፡ ከዚያም አትረድዱም፡፡ "
[ ሱረቱ ሁድ - 113 ]

ففي هذه الآية: التحذير من الركون إلى كل ظالم، والمراد بالركون، الميل والانضمام إليه بظلمه وموافقته على ذلك، والرضا بما هو عليه من الظلم.
وإذا كان هذا الوعيد في الركون إلى الظلمة، فكيف حال الظلمة بأنفسهم؟!! نسأل الله العافية من الظلم.
تفسير السعدي

ማንኛውንም አይነት ግፍና በደል የሚሰራን አካል ማንም ይሁን ማን መራቅ ይገባል። ከላይ በተጠቀሰው አንቀፅ "መዘንበል" የሚለው ቃል መጥፎ ድርጊቱን መቀበል፣ መውደድ፣ መጠጋት የሚለውን ይይዛል። ይህ ዛቻ የመጣው ግፍ የሚፈፅሙ ሰዎች ዘንድ በመዘንበል ሲሆን፣ ግፍ (ዙልም) ራሱ በሚፈፅም ሰው ላይማ የአላህ ዛቻ ከባድ ነው።

Join me https://t.me/MdJemal