Get Mystery Box with random crypto!

በደባርቅ ከተማ 16 ሰርጎ ገቦች ተያዙ። የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር በምሽት የኬላ ጥበቃ 16 የአ | ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

በደባርቅ ከተማ 16 ሰርጎ ገቦች ተያዙ።

የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር በምሽት የኬላ ጥበቃ 16 የአሸባሪውና ተስፋፊው ትህነግ ወራሪ ቡድን አባላት የኾኑ ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

የአሸባሪውና ተስፋፊው ትህነግ ወራሪ ቡድንን እኩይ ዓላማ ለማስፈፀም በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማዋ ገብተው እየተንቀሳቀሱ የመረጃ ማቀበል ሥራ የሚሠሩ 16 ተጠርጣሪ ሰርጎ ገቦች እና ሶስት ህገ-ወጥ መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደባርቅ ከተማ ከንቲባ ብርሃን ፀጋየ ገልፀዋል።

የአሸባሪውና ተስፋፊው ትህነግ ወራሪ ቡድንን ዳግም ወረራ ለመከላከል በሚደረግ ዘመቻ የመጀመሪያው ተግባር የከተማችን ከሰርጎ_ገብ መጠበቅ እና የደጀንነት ሚና መወጣት ዋነኛና ቁልፍ ተግባር መሆኑ ታውቆ በአደረጃጀት ስምሪት ተሰጥቶ ወደ እየተሠራ መኾኑን ከንቲባው ተናግረዋል።

ደባርቅ ከተማ ውስጥ በጠንካራ የመረጃ መዋቅር፣ የኬላ ጥበቃ እና በሌሎች ስምሪቶች የአሸባሪውና ተስፋፊው ትህነግ ወራሪ ቡድን ተላላኪ ሰርጎ ገብ ዓላማውን እንዳያሳካ የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ የከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

የደባርቅ ከተማ ባለገጀራ ወጣቶች ፣ የሰሜን ጎንደር ጥቁር አንበሳ የቀድሞ ሰራዊት የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር አባላት ፣ አጠቃላይ የፀጥታ መዋቅሩ ፣ ወጣቶችና ማኅበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም እያስጠበቀና የደጀንነት ተግባር እየፈፀመ ይገኛል።
 
የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu