Get Mystery Box with random crypto!

'በኩለ_ቀን ታሪክ በተቀየረው ቀን፣በዚያ ሰአት ሰማይ ጠቆረ ታላቁ ሊቀ ካህናችንም ራሱንም የዘላለ | ማስተዋልና ጥበብ📖

"በኩለ_ቀን
ታሪክ በተቀየረው ቀን፣በዚያ ሰአት ሰማይ ጠቆረ ታላቁ ሊቀ ካህናችንም ራሱንም የዘላለም መሥዋዕት አድርጎ ሊያቀርብ ከጨለማው መጋረጃ ጀርባ ሄደ...

ድንቅ ዋጋ ተከፈለልን፣ ከብዙ እንግልት በኋላ ተጨማሪ ሰአታት በመስቀል ላይ እያንዳንዷን የህይወት ጠብታ ለእያንዳንዳችን ስርየት አድርጎ ተሰቃየ..

ፍቅርህ አስደናቂ ነው ስቃይ በሞላው አንደበት በድል ለቅሶ ተፈፀመ አለ...

በዛች ቅጽበት ሌላ ዳግም የማይከፈል ዋጋ ተከፍለልን ...

በሺዎች የሚቆጠሩ በጎች ከዚያ በፊት ታርደው ነበር አሁን ግን ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ የሆነው የእግዚአብሔር በግ ታርዷል።

እግዚአብሔር ቤተሰቡን ለመመለስ መንገድ አዘጋጅቶ ነበር... ልጅ በከፈለው ዋጋ ለእኛም ለአህዛብ ጥሪው ደረሰን፣ የአንተ ዋጋ መክፈል እኛን እና አብን አገናኘቶ ውስጥ አስባን...

በዚህም መውደድ ወደደን "በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
-ዮሐ 3፥16
@mastewal_tbeb