Get Mystery Box with random crypto!

'ትዝ አኝ High School እያለሁ ልቤ ከብረሀን ፍጥነት በላይ የሚመታለት ልጅ ነበር እርሱም እ | ማስተዋልና ጥበብ📖

"ትዝ አኝ High School እያለሁ ልቤ ከብረሀን ፍጥነት በላይ የሚመታለት ልጅ ነበር እርሱም እንደዛው ያው መሰለኝ በእህታለምነት ቢሆንም ...እሺ ወደ ነገሩ ስገባ አብረን ጊዜ ለማሳለፍ በቻልን ቁጥር አብረን የምናሳልፈው ጊዜ በቂ አልነበረም ላነጋገር እንዲመች፣ 2 ሰአት ልክ እንደ 2 ደቂቃ እንደ ሚባለው ማለት ነው..."ከእርሱ ጋር ለሰአታት ያህል ጊዜ ለማሳለፍ ታግዬ አላውቅም፣ ደግሞም ሰአት በቂ አልነበረም.."የሚያስቀኝ እርሱ የእኔ የእግዚአብሔር ሰው እንኳን አልነበረም ካልገባችሁ እርሱት ...በቃ እወደዋለሁ ያ ብቻ ነበር...

"ከምንወደው ሰው ጋር ጊዜ ለማሳለፍ እራሳችንን ስንታገል አናገኘውም፣ እወደዋለሁ ከምንለው ሰው ጋር ጊዜ ካጣን በእርግጥ ፍቅር ውስጥ የለንም ማለት ነው ... ከምንወደው ሰው ጋር የምናሳልፈው እያንዳንዱ ቅጽበት ለሌላ ጊዜም ደስታን ይተውልንና ዳግም ለማግኘት ያጓጓናል..."የምናወራው ብቻ ሳይሆን በደስታ እና በተግባር የምናደርገውም ነው...በምናደርጋቸው፣ በምናደርግላቸው ነገሮች ሁሉ፣ ጊዜ ስንሰጣቸው በደስታና በእርካታ ነው በጭራሽ ዋጋ እንደመክፈል አንቆጥረውም....

"እና ምን ልል ነው ከመጨረሻው ከውዱ ፍቅረኛችን ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ወይ ደግሞ ለማሳለፍ ሲመጣ ለምን እንታገላለን..? "በህብረት ቦታ ለመቆየት ራሳችንን መገሠጽ ያለብን ለምድነው..? "በጸሎት ፀንተን ለመኖር ከፍ ከፍ የሚያደርግ አበረታች እና ቀስቃሽ የምንፈልገው ለምድነው..? "ቀኑን ሙሉ ከእርሱ ጋር አሳልፈን አዳርም ጨምረንበት ጊዜ ማሳለፍ ከቻልን ለምን ዋጋ እንደመክፈል እንቆጥረዋለን..?

ከእርሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ዋጋ እንደመክፈል አስበህ ታውቃለህ/ሽ..?

ይህን ሁሉ የምናደርገው በውስጣችን ላለው ለእግዚአብሔር ፍቅር ገና ስላልነቃን ነው.."ብዙዎቻችን ጸሎትን እንደ ከባድ ሃይማኖት ሥርዓት እናያለን.."ምክንያቱም ጸሎት ከሥርአትና ከመስፈርት በላይ መሆኑን ስለማናውቅ.."ጸሎት በአንድነት አንድነት ደስታ ውስጥ የጠፋ የሁለት ፍቅረኛሞች የፍቅር ቁርኝት ነው.."ለጸሎት ይህን እውነት ስንረዳ ያኔ ትግሉን እናቆማለን...

ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መቀራረብ ነው... "ከእግዚአብሔር ጋር ያለን አንድነት የፍቅር ጉዳይ ነው... የሚያደክመን ሳይሆን ሁል ጊዜ ልንፈልገው የሚገባውን ነው..ፀሎት የእግዚአብሔርን ፍቅር የምናውቅበትና የምንረዳበት ማረጋገጫ ነው....

በፍጹም ከእርሱ ጋር ጊዜ መውሰድ ዋጋ መክፈል አይደለም የሚሰማን ከሆነ በውስጣችን ላለው ለእርሱ ፍቅር ገና አልነቃንም ማለት ነው...
@mastewal_tbeb