Get Mystery Box with random crypto!

'ዛሬ ሕይወቴን በአዎንታዊ ማረጋገጫ እያነጽኩ ነው' ፈጣሪ አለምን የፈጠረው በቃሉ ነው። ቃል ህይ | Master Mind Group

"ዛሬ ሕይወቴን በአዎንታዊ ማረጋገጫ እያነጽኩ ነው"

ፈጣሪ አለምን የፈጠረው በቃሉ ነው። ቃል ህይወት ነው።
መጽሐፍ እንደሚል ሰው የአፉን ፍሬ ይበላል። ቃል ዘር ነው። መልካሙን መዝራት አረም መዝራትም ምርጫ ነው።
አዎንታዊ ማረጋገጫ ስለ ራሳችን ፣ ስለ ሰው፣ ስለ አለም ፥ ስለ ህይወት ያለንን እምነት፣ አመለካካት፣ እይታ ለማቅናት ሁነኛ መንገድ ነው። በአዎንታዊ ማረጋገጫ ልምድን እናዳብራል የውስጥ አእምሯችንን እናንጻለን። በዚህም ግባችን እናሳካለን።
አዎንታዊ ማረጋገጫችን ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን
* መቀየር የምንፈልገው የህይወት ክፍል ላይ ይበልጥ እናተኩር
* ሊሳካ ይችላል ብለን የምናምነው ቢያንስ አውንታዊ ግብ ላይ እናተኩር
*አሉታዊ ሃሳቦችን እና ስሜቶችን እና የውስጥ ንግግሮች በአዎንታዊ እንተካ
* አዎንታዊ ማረጋገጫችን በአሁን ጊዜ አረፍተነገር ይጻፍ
*በጥሩ ስሜት እንበለው ( አዎንታዊ ማረጋገጫችንን ስንል ስሜት ካጣንበት ወይም ምቾት ከነሳን ቃላቶቹን በማሻሻል አዎንታዊ ስሜት እንፍጠርለት )
* አዎንታዊ ማረጋገጫን ከበምናብ ማየት እና ግልጽ ግብ ማስቀመጥ ቢጠመር ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል።

ቃል ህይወት ነው

እስቲ ይሄን እንበል

ዛሬ ህይወቴን በአዎንታዊ ማረጋገጫ አያነጽኩ ነው

መልካም ቀን!