Get Mystery Box with random crypto!

ስኬታማ ሰዎች ያሏቸው 5 ነገሮች 1. ጠንክረው ይሰራሉ ዛሬ ላይ ጠንክረው ለመስራት ቁርጠኛ ና | Master Mind Group

ስኬታማ ሰዎች ያሏቸው 5 ነገሮች

1. ጠንክረው ይሰራሉ

ዛሬ ላይ ጠንክረው ለመስራት ቁርጠኛ ናቸው የዛሬ ጠንካራ ስራ እና ውሳኔ ለነገ የተሻለ ህይወት መሰረት ነው። ስኬታማ ሰዎች ጠንካራ ሰራተኛች ናቸው።

2. በፍፁም አያቋርጡም

ከባድ ና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢገጥሟቸውም በፍፁም አያቋርጡም ።
ስኬት በመጀመር ብቻ ሳይሆን በመጨረስ ውስጥ ናት!!

3. መስዋዕት ይከፍላሉ

የስኬት ጉዞ ቀላል ላይሆን ይችላል ብዙ ጥልፍልፎሽ ና አስቸጋሪ አቀበቶች፣ ውጣ ውረድ ይኖረዋ። ስኬታማ ለመሆን ከምቾት ቀጠና ወጥቶ መስዋዕት መክፈል ግድ ይላል። ስኬት በቀላሉ አትገኝም።  ስኬታማ ሰዎች የሚከፈለውን ዋጋ ( መስዋዕት) ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።

መስዋዕት ከፍለህ ወጥረህ ካልሰራህ ህይውት ጀርባዋን ታዞርብሃለች። የስኬት ሚዛኗ የሚያጋድለው መስዋዕት ከፍለው ለሚተጉ ነው። ነፃ ቁርስ የለም!!!

4. አዕምሯቸውን ይመግባሉ

ስጋችን ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ አዕምራችንም መመገብ አለበት "እውቀት" ! ማንበብ፣ መማር ... አስፈላጊ ነው። ስኬታማ ሰዎች ሁሌም ያነባሉ፤ መሪዎች ሁሌም አንባቢዎች ናቸው።

5. ኃላፊነት ይወስዳሉ

ስኬታማ ሰዎ በሚሰሩት ስራ ሁሉ ሃላፊነት ይወስዳሉ፣ ከማማረር ይልቅ መፍተሔ ፣ ከመውቀስ ይልቅ ማመስገን መለያቸው ነው። ለችግሮች መፍትሔ ፈላጊ እንጂ ችግር ፈጣሪ አይደሉም።

እርስዎስ ስኬታማ ለመሆን ምን እያደረጉ ነው ?

መልካም ቀን