Get Mystery Box with random crypto!

በአገርና በሕዝብ አይኮረፍም! **** ጦርነትን ትናንትም፥ ዛሬም፥ ነገም አልደግፍም። ይህ ማለት ግ | Christian Tadele Tsegaye

በአገርና በሕዝብ አይኮረፍም!
****
ጦርነትን ትናንትም፥ ዛሬም፥ ነገም አልደግፍም። ይህ ማለት ግን አገር ሲፈርስ፥ ሕዝብ ሲፈልስ እጆቼን አጣጥፌ እቀመጣለሁ ማለት አይደለም። አገርና ወገን የሌለው ሰው ባይኖርስ ምን ሊቀርበት ነው ዝም የሚለው? የአገርን አንድነት፥ የሕዝብንም ደኅንነት ለመጠበቅ በሚደረግ ውቅያኖስ በሚያህል ርብርብ ውስጥ የድርሻችንን አንዲት ጠብታ ብናዋጣ ክብሩ ለየራሳችን አይደለም ወይ? ደግሞስ ለአገር መስዋእት መክፈልን ማነው የፀጥታ ኃይሎች የብቻ ኃላፊነት ያደረገው?

የመንግስት አመራሮች ብሽቅ ሆነው እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ ሁሉ አንጀቴን አሳርረውት ያውቃሉ። አገርንና ዜጎችን የመጠበቅ የቅድሚያ ቅድሚያ ግዴታቸው መሆኑንም እገነዘባለሁ። ይሁንና በብሽቅነታቸው አኩርፌ፥ አገሬና ወገኔ የማንም መፈንጫ እንዲሆኑ በዝምታ ልተባበር አልችልም። አገር ለማፍረስ የመጣ ኃይል፥ ሕዝብን ለመጨረስ የተሰለፈ ኃይል፥ እንኳንስና በዝምታ በዱላም አይመለስም። ደግሞም በአገርና በሕዝብ አይኮረፍም። ድል ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት! ድል ለአማራ እና አፋር ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች! ድል ከጥንት እስከ ዛሬ ለአገርና ሕዝብ ክብርና ነፃነት ሕይወታቸውን ለመስጠት ለማይሳሱ ፋኖዎቻችን!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ልጆቿን ይባርክ!