Get Mystery Box with random crypto!

የመፅሐፍ አለም 🇪🇹🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ manbabemuluyadergal — የመፅሐፍ አለም 🇪🇹🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ manbabemuluyadergal — የመፅሐፍ አለም 🇪🇹🇹
የሰርጥ አድራሻ: @manbabemuluyadergal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 930
የሰርጥ መግለጫ

የ መፀሀፍ አለም ቤተሰቦች በዚ ቻናል የሚለቀቁ ◊የተለያዮ መፅሀፍት፣
◊መነባነብ ፣ግጥም እና
◊ትረካዋች ይለቀቃሉ።
leave ከማለታቹ በፊት ችግራችንን ብትነግሩን ደስ ይለናል
ለአስታየት እና ለጥያቄ
@manbabemuluyadergal0_bot
እናመሰግናለን።
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 13:13:55 ትግራይ

ወልዳ ስታሳድግ - አጥብታ ጡቶቿን፣
ሁልጊዜ ለጥይት - ገብራ ልጆቿን።
የሀዘን እንባ አፍስሳ - ፊቷን አጠበችው፣
አዳልጦ እየጣላት - ህልሟን ቀበረችው።
.......
ትግራይ ሰው ፈልጋ - አይዞሽ የሚል አጣች፣
ሚያልፍ እየመሰላት - በተስፋ ተቀጣች።
ወዟ ሁሉ ጠፍቶ - አጥንቶቿ ታዩ፣
በሞቷ ሊጠግቡ - ጥንብ አንሳዎች ቆዩ። 
.......
የልጆቿን ስቃይ - ደግሞ እያሳያት፣
ታሪክ ያላረመው - በዳይ አሰቃያት።
አምናው ነበር እሷ - ልቧ ተቀብሎ፣
ልጆቿን ሲነጥቃት - ለነጻነት ብሎ።
........
የያዘችው መንገድ - ሕይወት አላመጣም፣
ምትናፍቀው ፍቅርም - ወደ እሷ አልመጣም።
ህልሟ ራቀባት - ጸልያም መልስ አጣች፣
እግዚአብሔር ይመስገን - ብትልም ተቀጣች።
እንደ ራሄሌ እንባ - እንባዋን ላከችው፣
ለምን ረሳኸኝ? - ፈጣሪን አለችው።
.......
ያመነችው ይዟት - ሲነክሳት እያየች፣
አፏ ተለጉሞ - በዝምታ ቆየች ።
ወደ ውስጥ የገቡት - ዓይኖቿ ደከሙ፣
ስቃይዋን ቁስሏን - ጠፉ የሚያክሙ።
የሚያሳምማትም - በሽታው ጸናባት፣
ጮሃ እንዳትጣራ - ድምጿን አፈነባት። 
...............
ማመን ያቃታቸው - ያለባትን ስቃይ፣
ታግዛለች ብለው - ያልታረመን በዳይ፣
ጥርጥር ውስጥ ገብተው - ሳይደርሱላት ቀሩ፣
አምልጣም እንዳትሾልክ - ተዘጋባት በሩ።
.........
በሕይወት ለመቆየት - ለነፍሷ ተገዳ፣
መጥላት ሚገባትን - አስመስላ ወዳ።
ስቃይ መቀበሏን - የሚያውቅላት አጣች፣
በሁለት አቅጣጫ - ያለአግባብ ተቀጣች።
........
ዛሬ ምትጠራቸው - ያለልክ አንብታ፣
አንብተው ያውቃሉ - ከቤታቸው ገብታ።
እርሷም በጊዜዋ - ከበሮ ደልቃ፣
ያኔ ስትጨፍር - ይህን መች ጠብቃ?
እልል ያለችለት - ከፍ ያደረገችው፣
አንቆ እንደሚይዛት - መች ጠረጠረችው።
........
ሲበዛ ደክማለች - ጉልበት ጨርሳለች፣
እስኪያልቁባት ድረስ - ልጅ ትገብራለች።
ስታበዛ ለቅሶ - ጊዜው ተገልብጦ፣
ቦታዋን የቀማው - ያሰበውን ውጦ።
በሁለት አቅጣጫ - ጦሮች ተሰለፉ፣
አበቦች ተላኩ - ሊዋጉ እስኪረግፉ።
.........
እናማ ትግራይ

ምትፈሪውን በዳይ - ብለሽው ይበቃል፣
ከፍራቻ ወጥተሽ - እንድትቆሚ በቃል።
ትግራይ ጸለይኩልሽ - አንቺ ስትድኚ፣
የኢትዮጵያ ልጆች - አይረግፉም እመኚ።

መክብብ ወልደገብርኤል 
August 29, 2022
122 viewsMekbib, 10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:39:11 ምነው ለትግራይ ሊታዘንላትና ሊለቀስላት እንዲሁም ሊለመንላት አይገባም ማለት ነው? ለምንድነው ትግራይ የሚለው ግጥም የሚነሳው? ሁሉም ወያኔ አይደለምና በኢትዮጵያዊነታቸው ለሚሰቃዩት የትግራይ ሰዎችን የሚመለከት ነው ግጥሙ። የጅምላ ጥላቻ ውስጥ ሳንገባ የግጥሙን ሀሳብ ለመረዳት እንሞክር።
63 viewsMekbib, edited  07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 15:02:01 ተማጽኖ

ምንም ብንበድል - ምንም ብናስቀይም፣
ቅጣትህ እንደዚህ - ድሮ እኮ አይቆይም።
ግራ ተጋብተናል - ወልደን ሳንጠግባቸው፣
ሳይኖሩ ሚሞቱትን - እባክህ ተዋቸው።
አምላክ በቃሽ በላት - ለዚህች ምስኪን ሀገር፣
እስከ መቼ ድረስ - የእናት ልብ ይሰበር?
ጊዜ እየጠበቀ - እያገረሸባት፣
የጦርነት ህመም - ልጆች ጨረሰባት።
ያልታደለች ሀገር - ግራ ተጋብታለች፣
ልጆቿ ሲባሉ - ዛሬም ታለቅሳለች።
ትናንት ተያይዘው - ከገቡበት ገደል፣
ድጋሚ ተናንቀው - ጀመሩ መጋደል።
እንደ ደረቅ እንጨት - እየተማገዱ፣
ሁለቱም በእሳት - አለቁ ነደዱ።
ውሃ ሚረጭ የለም - ግን አውቀው እፍ ሚሉ፣
በዛም በዚህ በኩል - ሚያራግቡ አሉ።
መፍትሄ ሳያጡ - ጠብ እያከረሩ፣
ከእናት ጉያ ወስደው - ልጅ እየገበሩ።
በገዛ ልጆቿ - ደም እያሰከሯት፣
በስልጣን ሽኩቻ - ኢትዮጵያን ቀበሯት።

መክብብ ወልደገብርኤል 
ነሐሴ ፳፪ / ፳፻፲፬
August 28, 2022
255 viewsMekbib, 12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 22:22:00 በቃን

በጣም ተሰቃየ - የትግራይ ህዝብ በቃው፣
እያልን በመንገር - ካልሆንን ጠበቃው።
ወያኔ እንደልቡ - ወስዶ እየማገደ፣
የትግራይን ወጣት - አስሮ ካነደደ። 
መንግስት አለ ማለት - እጅግ ያስቸግራል፣
የእኛም ዝም ማለት - ሲበዛ ይመራል።
......
ለመኖር ሲሉ ነው - ወጥተው ሚደግፉት፣
ሞልተዋል ወያኔን - እጅግ ሚጠየፉት።
መሞት እየፈሩ - ማምለጫ ስላጡ፣
ደጋፊው ሚመስሉ - መሳሪያ የጨበጡ።
አይምሯቸው ታጥቦ - በቀል በመሞላት፣
ኢትዮጵያን ሚወጉ - ሆነውባት ጠላት።
ጨቅላ ልጆች ናቸው - ትግራይ የምታጣው፣
ያው ኢትዮጵያ እኮ ነች - በዚህ ምትቀጣው።
....
ኧረ በቃን እንበል - ዝምታችን በዛ፣
ምን ያህል ደም ይፍሰስ - ወያኔ እንዲገዛ?
ለብልጽግናውስ - ምን ያህል ሰው አልቆ፣
ይምራ ሀገሪቱን - ወንበሩን ጠብቆ?
ሁለቱም ለፍልሚያ - ቆመው ሚዘጋጁት፣
ለወንበር እኮ ነው - ወጣቱን ሚያፋጁት።
ወንድም ከወንድሙ - እህትም ከእህቷ፣
ፊት ለፊት ተራርደው - ኢትዮጵያ መሞቷ።
ማንንም አይጠቅምም - እልቂት ነው ውጤቱ፣
ካለፈው የባሰ - እንዳይረግፍ ወጣቱ።
ድምፅን እናሰማ - እንውጣ በአንድነት፣
መፍትሄ አያመጣም - ሁልጊዜ ጦርነት።
ልጆቻችን ይዩ - ልዩ የሆነ ዓለም፣
ከቀይ የተለየ - ሰማያዊ ቀለም።
ኢትዮጵያ በቂ ደም - በቃት ጠጥታለች፣
የሰላምን ዝናብ - እጅግ ተጠምታለች።

መክብብ ወልደገብርኤል
August 20, 2022
393 viewsMekbib, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 12:36:11 እንኳን ተወለዳችኹ

እምዬ ምኒልክ - እቴጌ ጣይቱ፣
በሥጋ አረፉ እንጂ - መቼ ሞትን ሞቱ።
ከጨለማ አውጥተው - ብርሃን አሳይተው፣
ቢሄዱም ጥለውን - ሀገርን ገንብተው።
ታሪክ በማህደሩ - ሥራቸውን ይዞ፣
አለ እስከ ዛሬ - ከእኛ ጋር ተጉዞ።
እናንተን መውለዷ - ኢትዮጵያ አርግዛ፣
ሕዝቧን አንድ አድርጎ - ነጻነቷን ገዛ።
ይህንን ነጻነት - መሸጥ ሚፈልጉ፣
ጊዜ ያነሳቸው - አረሞች አደጉ።
የእናንተ ዋርካነት - ከአረሞች ይበልጣል፣
ተናፋቂው ዘመን - አይቀርም ይመጣል።
በልደታችሁ ቀን - እስኪ እናስታውሳችሁ፣
እኛ ብንረሳ - ኢትዮጵያ አትረሳችሁ።

መክብብ ወልደገብርኤል
August 17, 2022
371 viewsMekbib, 09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 22:06:20
በምንችለው አቅም ሁሉ ሳምራዊትን እረድተናት እድትድን እና ሃሳቧ እንዲሞላ ለልጇ ለቤተሰቦቿ እድትኖር እናድርግ! እስኪ ዛሬ ውጪ ምሳችሁን እና እራታችሁን እምትበሉ እምንበላ ሰዎች ለምግቡ ከምንከፍለው ገንዘብ ላይ 10% እንኳን ለሳምሪ እንስጥ

የእርዳታ ጥሪ

#Ethiopia | የ27 አመት ወጣት የሆነችው ሳምራዊት ደስታ ላለፉት አምስት ወራት በመህፀን በር ካንሠር ህመም ስትሰቃይ ቆይታለች።

ወጣት ሳምራዊት የአዲስአበባ ከተማ ነዋሪ ስትሆን የዩንቨርስቲ ትምህርቷን በወለጋ ዩንቨርስቲ በአርክቴክቸር ኢንጂነሪንግ ተመርቃ ዳግም በአዲስአበባ እናት ሀገሯን የምታገለግል ባለትዳር እና የአንድ ወንድ ልጅ እናት ስትሆን ነገን ሰርታ ቤተሰቦቿን መደገፍ ህልሟ ነበር።

ነገር ግን አሁን ላይ ይህን የማህፀን በር ካንሠር በሽታን ወደ ውጭ ሀገር ሄዳ ህክምና እንድታገኝ በጥቁር አንበሳ የህክምና ቦርድ ተወስኗል።

ላለፉት አምስት ወራት በተለያየ የህክምና ማእከል ህክምና ስትከታተል የነበረችው ሳምራዊት ቀጣዩ ህክምና የሚሰጠው በህንድ ሀገር ሲሆን ህክምናውንም ለማድረግ አቅም ስላጠራት ባለን አቅም ሁሉ በመረባረብ ህይወቷን እንታደግ። ለልጇ እናትርፉት!!!

ዘወትር ለበጎ ነገር የማትታክቱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የአቅማችሁን እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንማፀናለን።

ንግድ ባንክ (CBE)
1000180776145 ገነት ጀምበሩ (እናቷ)
ለተጨማሪ መረጃ +251 91 038 4728 / +251 91 337 9447
99 viewsBro ግእዝ ፩, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 19:36:10 "ላሚቷ"

የላሚቷን ወተት - እፍታ እየጠጡ፣
የሚያልቧት ተዋቡ - ሚያምር ወዝ አወጡ።
ወተት ያዘለ ጡት - ጥጃዎቹ ቢያጡ፣
የግድ ሆነባቸው - ደረቅ ሣር መጋጡ።
እስከ ዛሬ ድረስ - ላሟ ጥጃዎችዋን፣
ማጥባት አልቻለችም - ታግላ አላቢዎችዋን።

መክብብ ወልደገብርኤል 
441 viewsMekbib, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 20:40:31 አዲስ አበባና መደመር

እንደ አዲስ አበባ - ሁሉን ተቀብሎ፣
ቤታችን ቢያስገባ - እንደ አቅሙ ችሎ።
አይጎላም ነበረ - ይህ አጉል ጠባችን፣
ዛሬ የሚያባላን - በዘር ማሰባችን።
..........
የአዲስ አበባ ሰው - የማይታማበት፣
ድሮም ቢሆን ኑሮው - መደመር አለበት።
ጎጠኞቹ ናቸው - ሰውነት የናቁት፣
ከመደመር ይልቅ - መቀነስ የሚያውቁት።
..........
የአዲስ አበባ ሰው - መደመርን ችሎ፣
ለዘመናት ኖሯል - ሁሉን ተቀብሎ።
ለምን እራሳቸው - የራሳቸውን ቤት፣
አድርገው አያሳዩም - የድምር ባለቤት?
.............
በመደመር ስሌት - የኖርነውን ኑሮ ፣
ጣልቃ ገብተውበት - ውስጡ ተሸርሽሮ።
መልሰው እንደ አዲስ - መደመር ይሉናል፣
ተግባር ላያሳዩን - ወሬ ያጠግቡናል።
..............
እንደ አዲስ አበባ - በአንድነት ደምሮ፣
ሚያዋህደን ጠፋ - ተካፍለን ዘንድሮ።
አዲስ አበባ ኑ - መደመር ተማሩ፣
ለእኛ አዲስ አይደለም - በአብሮነት መኖሩ።
..........
ይህች አዲስ አበባ - ጠባብ ሆና ሳለ፣
ሆዷ ሁሉን አቅፎ - በመደመር ቻለ።
ከእሷ የበለጠ - እያሉ የሰፉ፣
ቦታ ጠበባቸው - እንግዳውን ገፉ።
..........
ከሩቅ ከያሉበት - ወደ አዲስ ሲመጡ፣
ያላቸው አልነበረም - ተቀነሱ ውጡ።
እነሱ ግን ዛሬ - አብልተው አጠጥተው፣
ስትቆይ ያስወጡሃል - ዘርህን ጎትተው።
..........
የአዲስ አበባ ዓይነት - መደመር ቢስፋፋ፣
ጎልታ ትታይ ነበር - ኢትዮጵያ በይፋ።
ጠላቷ ግን ዛሬ - ለማጥበብ ስፋቷን፣
ሊያጠቃ ይፈልጋል - የአንድነት ጉልበቷን።
.............
ከሩቅ የሚመጡት - አሜሪካኖቹ፣
ከአስራ ሦስት ተነስተው - ሆነው ሃምሳዎቹ።
ምነው ለእኛ ጊዜ - አንድነትን ጠልተው፣
መከፋፈሉ ላይ - አሴሩ በርትተው?
አዲስ አበባንም - አጥብቀው ፈለጓት፣
ሥራዋ ቢተልቅ - ኢላማ አደረጓት።
..............
መክብብ ወልደገብርኤል 
December 30, 2021
964 viewsMekbib, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 18:37:36 የበላዮች ምክር

በኑሮ መወደድ - ለቅሶ ስታበዙ፣ 
ብሉ ተባለ እንዴ - ዳቦውን በሙዙ?
እኔ የሰማሁት - ጎመኑን ቀቅዬ፣
ብላ ነው የተባልኩት - ከዘይት አስጥዬ።
ምንኛ ደስ ባለኝ - ዳቦውን ገዝቼ፣
በሙዝ በበላሁት - ከቤቴ ገብቼ።
ጎመንን ቀቅሎ - ያለዘይት መብላት፣ 
መቼ ያስፈልገዋል - ዘዴና ብልሃት?
ጎመኑ እራሱ - ዋጋው ሰማይ ነክቷል፣
የሀብታም ሥጋ ሆኖ - ከገበያ ጠፍቷል።
.....
የሰጣችሁኝ ምክር - የሰጣችሁኝ ምርጫ፣
ድሮ ለድሃ ነበር - ከችግር ማምለጫ።
አሁን ዘግይታችሁ - ብላ የምትሉት፣
የለም ዋጋው እርካሽ - እናንተ ምትጠሉት።
......
ከላይ ተቀምጣችሁ - ምታዩትን ዓለም፣
ወርዳችሁ በማየት - ሞክሩት ግድየለም።
ያኔ ነው ተገቢው - ምክር ሚያምርባችሁ፣
ስታዩ የእኛን ችግር - እንደ እኛ ሆናችሁ።

መክብብ ወልደገብርኤል 
April 19, 2022
452 viewsMekbib, edited  15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 18:53:49 ማነው እብድ?

አይተው አለባበስ - መኝታና ቤቱን፣
ከሰው ነጥለውት - በመጉዳት ስሜቱን።
እብድ ይሉታል ሰዎች - ጊዜ ስለጣለው፣
ከለበሰው ሌላ - ምንም ስለሌለው።
እርሱ ግን ከዚህ ዓለም - ጣጣ ተለይቶ፣
ከሰው በታች ሆኖ - በማጣት ቆይቶ።
ችግር እየገፋው - ኑሮ አቆራምዶት፣
የሰዉን አስተያየት - ሽሽቱንም ለምዶት።
ምንም ሳያጠፋ - መኖሩን እያዩ፣
ሳይቀርቡት በርቀት - እብድ እያሉት ቆዩ።
......
አለማወቅ ይሁን - ወይ ምክንያት ማግኘት፣
እራስን ሳይዳኙ - ሌላን በመዳኘት።
ብዙ ሰው ይታያል - እራሱ እብድ ሆኖ፣
ሌላውን እብድ ሲል - በፍጥነት ኮንኖ።
በእብድነት ፈርጀው - ያዘኑለት ድሃ፣
ቀርበው ሳይረዱት - ሳያጠጡት ውሃ።
ቤቱን አፈራርሰው - ልጆቹንም ገለው፣
እርሱን ከሰው በታች - አድርገውት ጥለው።
ሁሉን አሳጥተው - በግፍ ቀምተውት፣
እነርሱ እብድ ሆነው - እርሱን እብድ ብለውት።
ሲቀርብ ይሸሹታል - ሥራቸውን አውቀው፣
ቀምተው በበሉት - በሠረቁት ደምቀው።
እነርሱ እየሆኑ - ቅስሙን የሠበሩት፣
እብድ በሚል ቋንቋ - ኑሮውን ያጠሩት።
በጤነኛው መሳይ - ዓለም ተጨማልቆ፣
እብድ ይባላል ዛሬም - ሰው ከታየ ወድቆ።

መክብብ ወልደገብርኤል 
April 18, 2022
1.1K viewsMekbib, edited  15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ