Get Mystery Box with random crypto!

35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ  ድህረ ጨዋታ ትንተና ማን ዩናይትድ - | ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ 

ድህረ ጨዋታ ትንተና

ማን ዩናይትድ -  በርንሌይ
      #አንቶኒ 79'.              #አምዱኒ 87'

  ኦልድትራፎርድ

ክለባችን ዛሬ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በርንሌን ያስተናገደ ሲሆን በመጀመሪያቹ 25 ደቂቃ ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ የጨዋታ ብላጫ የነበረው ሲሆን

በተደጋጋሚ የበርንሌን በረኝ ሲፈትኑ ነበር የብሩኖ አንግል የመለሰበት እንዲሁም የጋርናቾ በተደጋጋሚ ያባከናቸው ኳሶች ተጠቃሽ ናቸው

በመጀመሪያ አጋማሽ የመጨረሻ 15 ደቂቃ ግን ሙሉ ለሙሉ በርንሌ የጨዋታም የጎል እድልም በፈጠር ጥሩ ጊዜ አሳልፈዋል

በዛሬ ጨዋታ ድንቅ በነበረው ኦናና በተደጋጋሚ ጎል ሊሆኑ የተቃረቡ ኳሶችንም ሲያድን ተመልከትነዋል

በሁለተኛ 45 ክለባችን ተሻሽሎ የቀረበ ሲሆን በተደጋጋሚ የጎል እድል እየፈጠረን የነበረ ሲሆን የተፈጠሩትን የጎል እድሎች በአግባቡ አለመጠቀማችንም ዋጋ አስከፎሎና በስተመጨረሻ

ጨዋታው ሊገባደደ ወደ 10 ደቂቃ ሲቀረው አንቶኒ በራሱ ጥረት ለክለባችን የመጀመሪያ ጎል በማስቆጠረ ክለባችንን አሸነፊ የምታረግ ጎል ማስቆጠር ቢችልም

ኦናና በሰራው ጥፋት የተገኘውን ፔናሊቲ በርንሌዎች በሚገባ በመጠቀም ከታላቁ ኦልድትራፎርድ 1 ነጥብ ይዘው ሄደዋል!

አንቶኒ በዛሬው ጨዋታ በማጥቃቱም በመከላከሉም በጣም ድንቅ ነበር እንዲሁም ኦናና በዛሬው ጨዋታ ግሩም ነበር

ብሩኖ እንደ ሁልጊዜውም ጥሩ የጨዋታ ቀን አሳልፋል ያለመታከት የጎል እድል እየፈጠረ ነበር!

ኤሪክሰን በእኔ እያታ ከኮቢ በፊት መቀየር የነበረበት ሲሆን ነገር ግን ኤሪክ አላደረገውም ያላደረገበት የእራሱ እይታ ሊኖር ይችላል!

በአጠቃላይ በዛሬው ጨዋታ ዳኝነቱም በጣም አስከፊ ነበር ማለት ይቻላል ግልፅ ፍፁም ቅጣት ምት አለተሰጠንም

@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans