Get Mystery Box with random crypto!

ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከትላንቱ ጨዋታ በኋላ የሰጠው ሰፋ ያለ አስተያየት:- 'ጎል ሳይቆጠርብን ስለመው | ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከትላንቱ ጨዋታ በኋላ የሰጠው ሰፋ ያለ አስተያየት:-

"ጎል ሳይቆጠርብን ስለመውጣት ሁልጊዜ እናወራለን እና ይህንን ማሳካትም ፍላጎታችን ነው ግን ዛሬ አላደረግነውም ክብር ለሼፊልድ ዩናይትድ አለን። በመጨረሻ ወደጨዋታው ተመልሰን እራሳችንን ጨዋታን ለማሸነፍ ወደሚያስፈልገው ብቃት አድርሰናል።"

"ልክ እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታዎችን ከተቆጣጠርን የምናገኛቸውን የጎል እድሎች ማስቆጠር እንዳለብንም ማወቅ አለብን። ብዙ ጎሎችን እያስቆጠርን ነው እንደ ቡድን ሊኖረን የሚገባው ዝግጁነት ይህ ነው።"

"ጎል በማስቆጠሬ በጣም ደስተኛ ነኝ ነገርግን ጎል ከማስቆጠር በላይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ እፈልጋለሁ። ጎል ማስቆጠርም ከእኔ ድርሻዎች አንዱ ነው ነገር ግን ለእኔ ዋናው ነገር ጨዋታዎችን ማሸነፍ ነው ምክንያቱም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማሸነፍ የሚገባንን ያህል ጨዋታዎች እያሸነፍን አይደለም።"

"ትችቶች የስራው አካል ናቸው። በተከታታይ ስምንት እና ዘጠኝ ጨዋታዎችን አሸንፈክ ልክ አንድ ጨዋታ እንደተሸነፍክ ትችቶች እንደሚደርሱብህ ታውቃለህ። የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ለመሆን ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይጠይቃል።"

@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans