Get Mystery Box with random crypto!

ሀሪ ማጓየር ብቸኛው የመሀል ተከላካይ ! ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ በነገው እለት ከኮቨንትሪ | ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

ሀሪ ማጓየር ብቸኛው የመሀል ተከላካይ !

ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ በነገው እለት ከኮቨንትሪ ሲቲ ጋር በሚያደርገው የኤፍ ኤ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ወጣቱ ዊሊ ካምብዋላ እንደማይሳተፍ መገለፁ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ በነገው ጨዋታ በቡድናችን ስብስብ ውስጥ የሚካተተው ብቸኛው የመሀል ተከላካይ እንግሊዛዊው የቀድሞ የቡድኑ አምበል ሀሪ ማጓየር ይሆናል።

በቦታው ይሰለፉ የነበሩት ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ፣ ራፋ ቫራን እና ጆኒ ኤቫንስ በተመሳሳይ ጉዳት ማስተናገዳቸው ይታወሳል።

በዚህም ከፍተኛ የቡድን ስብስብ ጥበት ውስጥ የገቡት አለቃ ኤሪክ ቴንሀግ በነገው ጨዋታ ብራዚላዊውን አማካይ ካርሎስ ካሴሚሮ ከሀሪ ጋር በማጣማር የመሀል ተከላካይነት ሚናውን እንደሚሰጡት ይጠበቃል።

@Man_United_Ethio_Fans
@Man_United_Ethio_Fans