Get Mystery Box with random crypto!

′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት ′ #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን | ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት ′

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

የቀጠለ.......
__
ሃያው ዓለማት በ6 ቀን ከተፈጠሩት ጋር የተፈጠሩ
ቸው።

እነዚህ ሀያው ዓለማትን በአይነታቸው በ4 እንከ
ፍላቸዋለን

እነሱም፦
, ዓለማተ እሳት 9
, ዓለማተ ምድር 5
, ዓለማተ ውሃ 4
, ዓለማተ ነፋስ 2 ናቸው።

1
️⃣, ዓለማተ እሳት፦ ዘጠኝ ሲሆኑ በዝርዝር እንመልከታቸው

1ኛ, መ
በረ መንግስት ወይም መንበረ ጸባኦት፦ አጋአስት ዓለም ስላሴ የክቡር ዙፋናቸውን የዘረጉበት የመጀመሪያው ሰማይ ነው። ይህንንም አለም በአራት ተንቀሳቃሽ ፍጥረታት አምሳል የተፈጠሩ ኪሩቤል የተሰኙ መላአክት በአራት ማአዘን እርስ በርስ ሳይተያዩ በመቆም ዙፋኑን ተሸክመውታል።

አንደኛው ኪሩብ ገፀ ብእሲ/ሰብ ይባላል። የሰው መልክ ያለው ሲሆን ለሰው ልጆች በሙሉ የሚፀልይ ነው።

ሁለተኛው ኪሩብ ገፀ አንበሳ ይባላል። የአንበሳ መልክ ሲኖረው የሚጸልየው ለአራዊት ነው።

ሦስተኛው ኪሩብ ገፀ ላህም ይባላል። የላም መልክ ሲኖረው የሚጸልየው ለእንሰሳ ነው።

አራተኛው ኪሩብ ገፀ ንስር ይባላል። የንስር መልክ ሲኖረው የሚጸልየው ለአእዋፋት በሙሉ ነው።

ሱራፌል የተሰኙ 24 ካህናተ ሰማያት ይህን መንበረ ጸባኦት ዝንተ አለም ያለ እረፍት ያጥናሉ፤ ይሰግዳሉ ምስጋናም እረፍታቸው ነው።


2ኛ, ሰማይ ውዱድ፦ ሰማይ ውዱድ ማለት የተስማማ ሰማይ ማለት ሲሆን መላአክት የምስጋና መስዋኢት ይሰውበታል። ቅዱሳን መላእክትም ለአገልግሎት ወደዚህ ሰማይ ይመጣሉ ሱራፌልም ይገኙበታል።

3ኛ, ጸርሀ አርያም፦ ጸርሀ አርያም ማለት የሰማይ አዳራሽ ሲሆን በዚህ ሰማይ መላእክት አገልግሎት የሚከፋፈሉበት ነው። እረቂቅ የወርቅ ከበሮና እረቂቅ የወርቅ መቋሚያ ይዘው ከፊሉ በቅዳሴ ከፊሉ በስግደት ከፊሉ በልመና ከፊሉ በምስጋና ለማገልገል የሚከፋፈሉበት ነው።

ልክ በሶስት ክፍል እንደምትሠራ ቤተ ክርስቲያን መንበረ መንግስት እንደ መቅደስ ሰማይ ውዱድ ቅድስት ጸርሀ አርያም እንደ ቅኔ ማህሌት ሁነው በአምላካዊ ፍቃድ ተፈጥረዋል። ነገር ግን መንበረ መንግስት ሰማይ ውዱድና ጸርሀ አርያም ከላይ ወደ ታች ሲሆን እኩል ስፋትም አላቸው።

4ኛ, እየሩሳሌም ሰማያዊት፦ እየሩሳሌም ሰማያዊት ከላይ እንደ ተማርነው ለሳጥናኤል መኖሪያ የተፈጠረች ናት ነገር ግን በትእምቱ ምክኒያት ሊኖርባት አልቻለም።

ሳጥናኤል ከወደቀ በኋላ ለአዳም ተሰታው ነበር አዳምም በሳጥናኤል አሳሳችነት ኃጢያትን ሲሰራ ከእየሩሳሌም ሰማያዊት ወጥቷል ነገር ግን ጽድቅ የሰራ የሰው ልጅ በሙሉ በዳግም ምፅዓት ለዛልአለም ይወርሳታል። 12 የበር ደረጃዎች ሲኖሯት የ12ቱ ሐዋሪያት ስም ተጽፎባታል።

5ኛ, ኢዮር፦ ኢዮር ከሱስቱ ዓለመ መላእክት አንዷ ስትሄን ከላይ እንደ ተማርነው የኪሩብ የሱራፊ እና የሚካኤል ነገድ ይኖሩባታል።

6ኛ, ራማ፦ ራማ ልክ እንደ ኢዮር በሦስት ከተማ የተከፈለች ሲሆን የገብርኤል የሩፋኤል እና የሱርኤል ነገድ የኖሩበታል።

7ኛ, ኤረር፦ ኤረር ልክ እንደ ኢዮርና ራማ ሶስት ከተማ ሲኖሯት የሳድካኤል፣ የሰላታኤል እና አናንኤል ነገድ ይኖሩባታል።

8ኛ, ኮሬብ፦ ኮሬብ ምድርን ያጠረ የእሳት ዓለም ነው። ዙሪያውን በነፋስ ታጥሯል ከውቅያኖስ ቀጥሎ ይገኛል። ከምድር በታች ካለው እሳት ጋር በጠፈር ይገናኛል። በኮሬብ ስጋዊም ደማዊም ፍጥረት አይኖርም።

9ኛ, ከምድር በታች ሁኖ ውሀን የተሸከመ እሳት ነው። ይህ ዓለመ እሳት ስፋቱ ምድርን ያክላል ምድርን በውሀ ላይ አፅንቷታል ውሀን ደግሞ በእሳት ላይ አፅንቶታል። ይህ ውሀ የፀናበት እሳተ ዓለም እሳት ይባላል። ውሃን ብቻ ተሸክሞ ሊኖር የተፈጠረ ፍጥረት ነው። በዚህ አለመ እሳት ምንም አይነት ፍጥረት አይኖርም።


, ዓለማተ መሬት፦ አምስት ሲሆኑ በዝርዝር እንያቸው

1ኛ, ብሔር
ብጹአን፦ ብሔረ ብፁዓን ከብሔረ ሕያዋን ከፍ ብላ የምትገኝ ሲሆን በዝች ምድር ሰዎች ይኖራሉ ሰዎችም ያገባሉ ይጋባሉ ልጆችም ይወልዳሉ። ባልና ሚስት በግብር የሚተዋወቁት 3 ጊዜ ብቻ ነው የሚወልዱት ልጅም 3 ብቻ ነው ከ3 ከፍም ዝቅም አይልም የመጀመሪያው ወንድ ልጅ ለአገልግሎት ሁለቱ ሴቲቱና ወንዱ ዘር ለመተካት ይሆናሉ። በዝች ቦታ የሚኖሩ የተነጠቁት በነብዩ ኤርሚያስ ዘመን ነው ከሄዱት መካከል ማቴዎስ ወንጌላዊ እና ቅዱስ ዞሲማስ መጥቀስ ይቻላል።

2ኛ, ብሔረ ሕያዋን፦ ብሔረ ሕያዋን እስከ ምፅዓት ቀን ድረስ የማይሞቱ ሰዎችና እነሱን ሚጠብቁ መላእክት መኖሪያ ናት።

ብሔረ ሕያዋን እንደ ገዳም ናት በዚህ ሚኖሩ ሰዎች አያገቡም አይጋቡም አይወልድምም

በዚች ምድር ሳሉ አግብተው ኑረው ኋላ በመልካም ስራቸው የተነሳ ተነጥቀው ወደ ላይ በመውጣት ይኖሩባታል። ሄኖክ፣ ካላገቡ ኤሊያስ፣ ከ12ቱ ሐዋሪያት 11ዱ ሲሞቱ ዮሐንስ ብቻ ሳይሞት ተነጥቆ በብሔረ ሕያዋን ይኖራል።

3ኛ, ገነት፦ ገነት ከምንኖርባት ምድር በቀኝ ወይም በምስራቅ በኩል ትገኛለች የሲኦል ተቃራኒም ናት ከዚች ምድርም ትሻላለች ኃጢያት የለባትም መላእክት፣ የጻድቃን ነፍሳት፣ እጽዋት እና አእዋፋት ይኖራሉ። የጻድቃን ነፍሳት ከገነት እስከ ዳግም ምፅዓት ይቆያሉ ከዛ በኋለ ወደ መንግስተ ሰማያት/እየሩሳሌም ሰማያዊት ይሄዳሉ።

4ኛ, የምንኖርባት መሬት ወይም ምድር ናት እች ምድር ከሲኦል ትሻላለች ጻድቃንና የኃጥአን ሰው መላእክት እንሰሳትና አጋንትም ጭምር ይኖራሉ።

ምድር ሰማይ በተፈጠረበት ቀን እሁድ ስትፈጠር ለሰዎች ወደ ሲኦልና ገነት መሸጋገሪያ ናት መላእክትም ሰውንና ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ከሰማያት ይወርዳሉ አንድ ሰው ለሊትና ቀን የሚጠብቁት ከናቱ ማህጸን ከተፈጠረ ጀምሮ ሁለት መላእክት ይመደቡለታል። አጋንንት ደግሞ ሰውን ኃጢያት እያሰሩት ይኖራሉ።

5ኛ, ሲኦል/በርባኖስ ወይም እንጦሮጦስ ይባላል። ሲኦል ከገነት በተቃራኒ ከምድር በግራ በምእራብ በኩል ትገኛለች።

በዝች ጽድቅ በማይነገርባት ቦታ እጽዋትም ሆነ ውሃ ባይኖርባትም የመሬት አካልነት አላት እሳት የሚነድባት ጨለማ ናት እሳት ሲነድ ጨለማ ሊገፈፍ ባሕርይው ቢሆንም በሲኦል ግን እንዲህ አይደለም።
~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
ዓለማተ ማይ
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላድቱ ድንግል -ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan


❸➐