Get Mystery Box with random crypto!

#የአይን #ግፊት #መጨመር #(glaucoma) #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን | ማህደረ ጤና☞

#የአይን #ግፊት #መጨመር #(glaucoma)

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
#ግላኮማ የአይንን ነርቭ (Optic Nerve) የሚጎዱ የአይን በሽታዎች መጠሪያ ስያሜ ነው፡፡ እነዚህ የአይን ነርቮች ለተስተካከለ እይታ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ መሰል ጉዳቶች የአይን ግፊት በመጨመሩ ምክንያት ሊመጣ ይችላል፡፡
የአይን ግፊት በሽታ ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ ቀዳሚ የአይነስውርነት ምክንያት ነው፡፡ በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ያለ ሰው ላይ ሊታይ ቢችልም እድሜ በጨመረ ቁጥር ተጋላጭነት ይጨምራል፡፡
#አብዛኛዎቹ የግላኮማ አይነቶች በጊዜ ምልክት አያሳዩም፡፡ ጉዳቱ የሚጨምረው ቀስ በቀስ ስለሆነ ከፍግተኛ ጉዳት እስከሚያመጣ ድረስ ሳይታወቅ ይቆያል፡፡
በግላኮማ ምክንት የሚመጣ አይነስውርነት የሚድን ስላልሆነ በቋሚነት መደበኛ የሆነ የአይን ምርመራ ማድረግ እና የአይን ግፊትን መለካት በሽታው ሳይበረታ እንዲታወቅ እና በጊዜ ህክምና ለመጀመር ይረዳል፡፡ በምርመራ ግላኮማ ሳይዘገይ ከተገኘ እይታን መታደግ ወይም ጉዳቱን መቀነስ ይቻላል፡፡ የግላኮማ ህክምና የሚቋረጥ አይደለም፤ እድሜ ዘመኖትን የሚቀጥል ነው፡፡
#ምልክቶች
እንደየአይነቱ እና የበሽታው ደረጃ ምልክቶቹም ይለያያሉ፡፡
ኦፕን አንግል ግላኮማ (Open-angle Glaucoma)
ብዙ ምልክት አያሳይም፤ አንዳንዶች ላይ ብዙ ነጠብጣብ የነ የእይታ መጥፋት እና መሀል ላይ ብቻ የሚኖር እይታ ናቸው፡፡
# አኪዩት አንግል ክሎዠር ግላኮማ (Acute angle-closure glaucoma)
የአይን ህመም
ከባድ የራስ ምታት
የአይን ህመሙን ተከትሎ የማቅለሽለሽና የማስታወክ መኖር
ድንገታዊ የሆነ የአይን እይታ ችግሮች (በተለይ ደብዘዝ ባለ ብርሃን ዉስጥ)
ብዥታ
የአይን መቅላት
በወቅቱ ካልታከመ ግላኮማ እይታ ማጣትን ያመጣል፡፡ በህክምናም እንኳን 15% የሚሆኑት በ20 ዓመት ውስጥ ቢያንስ የአንዱን አይን እይታ ያጣሉ፡፡
#ሀኪሞት ጋር መቼ ይሒዱ?
ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ካዩ በአስቸኳይ የአይን ስፔሺያሊስት ጋር መሄድ ይኖርቦታል፡፡
#ከፍተኛ የአይን ግፊት በምን ምክንያት ይመጣል?
ግላኮማ የአይን ነርቭ (Optic Nerve) ጉዳት ጋር የሚመጣ ነው፡፡ ይህ ነርቭ ቀስ በቀስ ሲጎዳ እይታ ይቀንሳል፡፡ ጉዳቱ ለምን ከአይን ግፊት መጨመር ጋር እንደሚያያዝ የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡
የአይን ግፊት የሚምረው በአይን ውስጥ ጠሚገኘው ፈሳሽ በብዛት ሲመረት ወይም ፍሰቱ ሲስተጓጎል ነው፡፡ ግላኮማ በዘር ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ጥናቶችም የአይን ግፊት ሊጨምር የሚችል ጂን ለይተዋል፤ ይህም በዘር ይሄዳል፡፡
ተጋላጭነት
ከፍተኛ የውስጥ አይን ግፊት
ከ60 ዓመት በላ መሆን
ዘር - ጥቁር፣ ሂስፓኒክ ወይም ሩቅ ምስራቅ
ተጓዳኝ የጤና እክሎች - የስኳር በሽታ፣ የልብ በሽታ፣ ደም ግፊት….
የእይታ ችግር
ማናቸውም የአይን ቀዶ ጥገና ካደረጉ
አይን ላይ አደጋ ወይም ጉዳት ከነበረ
አንዳንድ የአይን ጠብታዎችን (Corticosteroid) ለረጅም ጊዜ መውሰድ
#እንዴት እንከላከል?
መደበኛ የሆነ የአይን ምርመራ ማድረግ
በቤተሰብ ተመሳሳ ችግር ካለ ቶሎ ቶሎ ምርመራ ማድረግ
በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
የሚታዘዝሎት የአይን ተታ ሳያቋርጡ ማድረግ
የአይን መከላከያዎችን ሲያስፈልግ መጠቀም
#ይህን እና ተያያዥ የሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ያሎትን ጥያቄዎች ለማቅረብ ወደ 8809 ይደውሉ ከባለሙያ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!
9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
በጤና፣ በግንኙነት፣ በስነ-ልቦና እና አመጋገብ ዙርያ ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት 9102 Ok ብለዉ ይጠቀሙ።
ቅድመ-ጥንቃቄ ልናደርግላቸው የሚገቡ በሽታዎች የትኞቹ ናቸው? ብዙ ሰዎችን ከሚያጠቁ በሽታዎች እራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ክብደታችንን ለመቆጣጠር አመጋገባችን እንዴት መሆን አለበት?
ከፍቅረኛ፣ ከቤተሰብ እና ከባልደረባ ጋር በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ የግንኙነት ችግሮችን እንዴት መፍታት እንችላለን?
በነዚህ ጉዳዮች ዙርያ የሚያውጠነጥኑ አጭር መልእክቶችን #በ9102 ማግኘት ይችላሉ።
9102 OK

በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን፡
የዶክተር አለ የአጭር መልእክት
9102 OK
የዶክተር አለ የስልክ ምክክር
8809
የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
http://tiny.cc/gf606y
የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
T.ME/DOCTORALLE8809
የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ
(#በጤና #ባለሙያ #ማክዳ)