Get Mystery Box with random crypto!

ማህደረ ጤና☞

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahderetena — ማህደረ ጤና☞
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahderetena — ማህደረ ጤና☞
የሰርጥ አድራሻ: @mahderetena
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.04K
የሰርጥ መግለጫ

♣በዚ ቻናላችን የምናቀርባቸው
ጠቅላላ ጤንነት
ሰለ ኮሮና በየቀኑ መረጃ እንሰጣለን 💑
ጤና ነክ እውነታዎች🍇🍉2 : 4
ጤናማ አመጋገብ🍔 4 : 6
የጤና በረከቶች🍓 6 : 8
ልጆችና ጤና👪 8 : 10
ተላላፊ በሽታዎች💀10 : 12
እርግዝና እና ልጅ ማሳደግ 12 : 2
☞ተቀላቀሉን እና ተጠቀሙበት
@mahderetena
ለጥያቄዎ በአፋጣኝ መልስ ያገኛሉ 👇👇 @mahderetena_bot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-16 07:22:02
ተጠንቀቁ

በምናስነጥስበት ጊዜ አፍንጫችንን ማፈን ግፊቱ በጭንቅላታችን ዉስጥ ደም እንዲፈስ ያረጋል፣ አንዲሁም ለአንገት ህመም ያጋልጣል።

@amazing_fact_433
704 views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 07:47:33
እባካችሁ ለልጆቿ እንድትኖር እንድረስላት

ስሟ ወይንሸት ፀጋዬ ይባላል፡፡ ነዋሪነቷ በሀዋሳ ከተማ ባህል አዳራሽ ክፍለከተማ ሀረር ቀበሌ ውስጥ በኪራይ ቤት ውስጥ ነው፡፡ በየሰው ቤት በእሳት እንጀራ በመጋገር እና ምሽት ላይ በየ መንገድ ዳር ቆሎ በመሸጥ የ11 እና የ10 አመት ልጆቿን እያሳደገች አልፎም ደግሞ እያስተማረች የነበረችው ወይንሸት አሁን አቅም ከድቷት በአልጋ ላይ ስቃይ እያሳለፈች ትገኛለች፡፡ በገጠማት የጡት እና የአጥንት ካንሰር ለልጆቿ በእሳት ተቃጥላ የዕለት ጉርሳቸውን ታቀርብ የነበረችሁ እናት ዛሬ ግን አይደለም ለልጆቿ ለራሷ መሆን አቅቷት ህክምና እንዳገኝ እርዱኝ ስትል ለኢትዮጵያ ህዝብ ተማፅኖዋን እያቀረበች ትገኛለች፡፡

እኔም እናንተ ደጋግ የሀገሬ ልጆች ወይንሸትን እንድትደግፏት እና ቢያንስ ለልጆቿ እንድትኖርላቸው ስል በእግዚአብሔር ስም ጥሪዬን አቀርብላችዋለሁ፡፡

ወይንሸት ፀጋዬን መርዳት የምትፈልጉ "በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስሟ በተከፈተው የሂሳብ ቀጥር 1000256462528 እንዲሁም በቀጥታ በመደወል ወይንሸት በስልክ ማግኘት የፈለገ በ0934720273 እና የቅርብ አስታማሚዋ ማርታ መጃ ስልክ 0926044328 በመደወል ማግኘትም ሆነ መርዳት ይችላሉ፡፡

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ታከለ

#ሼር በማድረግ ለሌሎች እንዲደርስ ለምስኪኗ እናት እንድረስላት !
1.3K views04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 08:47:09 • ልጆች ከተወለዱ ጀምሮ እስከ 6 ወር ድረስ ምን እንመግባቸው?
• ልጆቻችን ምግብ ከጀመሩ በኋላ ምን ያህል በቀን ውስጥ መመገብ ይኖርባቸዋል?
• ልጆች እንዴት እና ምን ያህል ሰአት መተኛት ይኖርባቸዋል?
• ልጆች የፎርሙላ ወተት መጠቀም ካለባቸው በምን ያህል መጠን እንስጥ?
• ህፃናት ልጆች ሲያማቸው እንዴት መመገብ ይኖርብናል?
• በጡት ማጥባት ወቅት የህፃናት አቀማመጥ እና የጡት አሰጣጥ ?
#ይህን እና ተያያዥ የሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ያሎትን ጥያቄዎች ለማቅረብ ወደ 8809 ይደውሉ ከባለሙያ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!
9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
በጤና፣ በግንኙነት፣ በስነ-ልቦና እና አመጋገብ ዙርያ ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት 9102 Ok ብለዉ ይጠቀሙ።
ቅድመ-ጥንቃቄ ልናደርግላቸው የሚገቡ በሽታዎች የትኞቹ ናቸው? ብዙ ሰዎችን ከሚያጠቁ በሽታዎች እራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ክብደታችንን ለመቆጣጠር አመጋገባችን እንዴት መሆን አለበት?
ከፍቅረኛ፣ ከቤተሰብ እና ከባልደረባ ጋር በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ የግንኙነት ችግሮችን እንዴት መፍታት እንችላለን?
በነዚህ ጉዳዮች ዙርያ የሚያውጠነጥኑ አጭር መልእክቶችን #በ9102 ማግኘት ይችላሉ።
9102 OK

በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን፡
የዶክተር አለ የአጭር መልእክት
9102 OK
የዶክተር አለ የስልክ ምክክር
8809
የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
http://tiny.cc/gf606y
የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
T.ME/DOCTORALLE8809
የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ
Icon for this message
Doctor Alle , ዶክተር አለ 8809
Health & wellness website
1.4K views05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 08:47:09 #የአይን #ግፊት #መጨመር #(glaucoma)

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
#ግላኮማ የአይንን ነርቭ (Optic Nerve) የሚጎዱ የአይን በሽታዎች መጠሪያ ስያሜ ነው፡፡ እነዚህ የአይን ነርቮች ለተስተካከለ እይታ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ መሰል ጉዳቶች የአይን ግፊት በመጨመሩ ምክንያት ሊመጣ ይችላል፡፡
የአይን ግፊት በሽታ ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ ቀዳሚ የአይነስውርነት ምክንያት ነው፡፡ በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ያለ ሰው ላይ ሊታይ ቢችልም እድሜ በጨመረ ቁጥር ተጋላጭነት ይጨምራል፡፡
#አብዛኛዎቹ የግላኮማ አይነቶች በጊዜ ምልክት አያሳዩም፡፡ ጉዳቱ የሚጨምረው ቀስ በቀስ ስለሆነ ከፍግተኛ ጉዳት እስከሚያመጣ ድረስ ሳይታወቅ ይቆያል፡፡
በግላኮማ ምክንት የሚመጣ አይነስውርነት የሚድን ስላልሆነ በቋሚነት መደበኛ የሆነ የአይን ምርመራ ማድረግ እና የአይን ግፊትን መለካት በሽታው ሳይበረታ እንዲታወቅ እና በጊዜ ህክምና ለመጀመር ይረዳል፡፡ በምርመራ ግላኮማ ሳይዘገይ ከተገኘ እይታን መታደግ ወይም ጉዳቱን መቀነስ ይቻላል፡፡ የግላኮማ ህክምና የሚቋረጥ አይደለም፤ እድሜ ዘመኖትን የሚቀጥል ነው፡፡
#ምልክቶች
እንደየአይነቱ እና የበሽታው ደረጃ ምልክቶቹም ይለያያሉ፡፡
ኦፕን አንግል ግላኮማ (Open-angle Glaucoma)
ብዙ ምልክት አያሳይም፤ አንዳንዶች ላይ ብዙ ነጠብጣብ የነ የእይታ መጥፋት እና መሀል ላይ ብቻ የሚኖር እይታ ናቸው፡፡
# አኪዩት አንግል ክሎዠር ግላኮማ (Acute angle-closure glaucoma)
የአይን ህመም
ከባድ የራስ ምታት
የአይን ህመሙን ተከትሎ የማቅለሽለሽና የማስታወክ መኖር
ድንገታዊ የሆነ የአይን እይታ ችግሮች (በተለይ ደብዘዝ ባለ ብርሃን ዉስጥ)
ብዥታ
የአይን መቅላት
በወቅቱ ካልታከመ ግላኮማ እይታ ማጣትን ያመጣል፡፡ በህክምናም እንኳን 15% የሚሆኑት በ20 ዓመት ውስጥ ቢያንስ የአንዱን አይን እይታ ያጣሉ፡፡
#ሀኪሞት ጋር መቼ ይሒዱ?
ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ካዩ በአስቸኳይ የአይን ስፔሺያሊስት ጋር መሄድ ይኖርቦታል፡፡
#ከፍተኛ የአይን ግፊት በምን ምክንያት ይመጣል?
ግላኮማ የአይን ነርቭ (Optic Nerve) ጉዳት ጋር የሚመጣ ነው፡፡ ይህ ነርቭ ቀስ በቀስ ሲጎዳ እይታ ይቀንሳል፡፡ ጉዳቱ ለምን ከአይን ግፊት መጨመር ጋር እንደሚያያዝ የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡
የአይን ግፊት የሚምረው በአይን ውስጥ ጠሚገኘው ፈሳሽ በብዛት ሲመረት ወይም ፍሰቱ ሲስተጓጎል ነው፡፡ ግላኮማ በዘር ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ጥናቶችም የአይን ግፊት ሊጨምር የሚችል ጂን ለይተዋል፤ ይህም በዘር ይሄዳል፡፡
ተጋላጭነት
ከፍተኛ የውስጥ አይን ግፊት
ከ60 ዓመት በላ መሆን
ዘር - ጥቁር፣ ሂስፓኒክ ወይም ሩቅ ምስራቅ
ተጓዳኝ የጤና እክሎች - የስኳር በሽታ፣ የልብ በሽታ፣ ደም ግፊት….
የእይታ ችግር
ማናቸውም የአይን ቀዶ ጥገና ካደረጉ
አይን ላይ አደጋ ወይም ጉዳት ከነበረ
አንዳንድ የአይን ጠብታዎችን (Corticosteroid) ለረጅም ጊዜ መውሰድ
#እንዴት እንከላከል?
መደበኛ የሆነ የአይን ምርመራ ማድረግ
በቤተሰብ ተመሳሳ ችግር ካለ ቶሎ ቶሎ ምርመራ ማድረግ
በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
የሚታዘዝሎት የአይን ተታ ሳያቋርጡ ማድረግ
የአይን መከላከያዎችን ሲያስፈልግ መጠቀም
#ይህን እና ተያያዥ የሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ያሎትን ጥያቄዎች ለማቅረብ ወደ 8809 ይደውሉ ከባለሙያ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!
9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
በጤና፣ በግንኙነት፣ በስነ-ልቦና እና አመጋገብ ዙርያ ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት 9102 Ok ብለዉ ይጠቀሙ።
ቅድመ-ጥንቃቄ ልናደርግላቸው የሚገቡ በሽታዎች የትኞቹ ናቸው? ብዙ ሰዎችን ከሚያጠቁ በሽታዎች እራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ክብደታችንን ለመቆጣጠር አመጋገባችን እንዴት መሆን አለበት?
ከፍቅረኛ፣ ከቤተሰብ እና ከባልደረባ ጋር በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ የግንኙነት ችግሮችን እንዴት መፍታት እንችላለን?
በነዚህ ጉዳዮች ዙርያ የሚያውጠነጥኑ አጭር መልእክቶችን #በ9102 ማግኘት ይችላሉ።
9102 OK

በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን፡
የዶክተር አለ የአጭር መልእክት
9102 OK
የዶክተር አለ የስልክ ምክክር
8809
የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
http://tiny.cc/gf606y
የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
T.ME/DOCTORALLE8809
የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ
(#በጤና #ባለሙያ #ማክዳ)
1.2K views05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 21:12:25
#ጥቆማ

ለሰሜን ወሎ ዞንና አጎራባች ማህበረሰብ ክፍሎች ፦

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሀረር ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር እንዲሁም ከአንገት በላይ እባጭ ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች #በነፃ_የህክምና አገልግሎት ለመስጠት አቅዷል።

በሆስፒታሉ ቢሮ ቁጥር 12 ላይ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ 0333311680 / 0920218203 በመደወል ከ1/09/2014 ዓ/ም ጀምሮ በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል።

(ላልሰሙትም አሰሙ)

@tikvahethiopia
1.4K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 07:26:32
ዲቪ (DV) 2023 ይፋ ሆኗል።

የ2023 ዲቪ ሎተሪ ዛሬ ማታ ይፋ የሆነ ሲሆን ሞልታችሁ ስትጠባበቁ የነበራችሁ በሙሉ የዲቪ ውጤታችሁን በዚህ ሊንክ https://dvprogram.state.gov/ESC/Default.aspx መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

@tikvahethiopia
1.4K views04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 07:26:32
1.2K views04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 23:11:41
#ጥንቃቄ

በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሦስት መድኃኒቶችን ህብረተሰቡ እናዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጠ እና በጤና ላይ ከቀላል እስከ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ፦

Titan gel፣
Mara Moja
Relief የተባሉ መድኃኒቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አሳስቧል።

መድኃኒቶቹ በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ያልተመዘገቡና በህጋዊ መንገድም ወደ አገር ዉስጥ ያልገቡ ናቸው።

Titan gel የተባለው መድኃኒት በሐኪም ብቻ በመታዘዝ ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ሲሆን ነገር ግን በድብቅና በህገወጥ መንገድ ገበያ ላይ አንደሚገኝ ታውቋቃ።

መድኃኒቶቹን ማንኛውም ግለሰብ ወይም አካል በህጋዊ ተቋማት ሆነ በህገወጥ መንገድ ሲያገኛቸው እንዳይጠቀማቸውና በባለስልጣን መስሪያቤቱ ነጻ የስልክ መስመር 8482 በአቅሪያባቸው ለሚገኙ የክልል ተቆጣጠሪዎች ወይም ለጸጥታ አካላት በመጠቆም አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
1.2K views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 22:37:22 #ልጆ #የንግግር #ሕክምና/speech #therapy #ያስፈልገዋል?

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮች ዛሬ ይዘን የቀረብነው ፁሁፍ ስለ ንግግር
ሕክምና/speech therapy ሲሆን የንግግር ሕክምና ምን እንደሆነ እና ሕክምናው ለማን
እንደሚያስፈልግ እና የንግግር ሀኪም/ቴራፒስት ስራው ምን እንደሆነ የሚገልፅ ፁሁፍ ነው፤ ከ
ልጆ የአእምሮ እድገት ጋር በተያያዘ ከስነ-ልቦና ባለሙያ ጋር በመመካከር ችግሩ ስር ሳይስድ
መከላከልይቻላል፡፡ከልጆ እድገት እና አስተዳደግ ጋር በተያያዘ ከስነ-ልቦና ባለሙያ ጋር
ማማከር ከፈለጉ ዶክተር አለ 8809 ላይ እየደወሉ እንመካከር፡፡
የንግግር ሕክምና ምንድን ነው?
የንግግር ህክምና የንግግር እና የቋንቋ ችሎታዎትን ለማሻሻል የሚደረግ ህክምና ነው።
የንግግር ቴራፒስት ምን ያደርጋል?
የንግግር ቴራፒስት - የንግግር-ቋንቋ ፓቶሎጂስት ተብሎ ይጠራሉ፡፡ የንግግር እክሎችን እና
የግንኙነት/ communicationችግሮችን ይገመግማል ፣ ይመረምራል እና ያክማል። የልጆችን
በእድገት መዘግየት እንዲሁም በአካል ጉዳት ወይም በህመም ምክንያት የንግግር እክል
ያለባቸውን አዋቂዎችን ያክማሉ፡፡
የንግግር ሕክምና የሚያስፈልገው ማነው?
የንግግር ሕክምና የንግግር ችግር / communication disorders ላለባቸው ልጆች እና
ጎልማሶውች ጠቃሚ ነው፡፡እንዲሁም የመስማት ችግር/ hearing impairments
ያለባቸውን ወይም የመዋጥ ችግር /difficulty swallowing ያለባቸውን ሊረዳ ይችላል።
ለሚከተሉትን እክሎች የንግግር ሕክምና ያስፈልጋቸዋል:-
አፋሲያ/ Aphasia ፡- አፋሲያ ያለባቸው ሰዎች ማንበብ፣ መጻፍ፣ መናገር እና ቋንቋ
መረዳት ሊቸገሩ ይችላሉ። ቋንቋን የሚያስተናግደው የአንጎልዎ ክፍሎች በስትሮክ ወይም
በአካል ጉዳት ሲጎዱ አፋሲያን ሊያዳብር ይችላል።
አፕራክሲያ/ Apraxia ፡- አፕራክሲያ ያለባቸው ሰዎች ምን ማለት እንደሚፈልጉ ያውቃሉ፤
ነገር ግን ቃላት መመስረት ላይ ይቸገራሉ። የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመዋጥ ወይም ሌላ የሞተር
ችሎታዎች ላይ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል።
አርቲኩሌሽን እክሎች/ Articulation disorders፡- የንግግር እክል ያለባቸው ልጆች
ለተወሰኑ ቃላቶች ድምፆችን መፍጠር አይችሉም፡፡ ለምሳሌ፡- አንዱን ድምጽ በሌላው
ይተካሉ፣ ልክ እንደ “ሚኪ” ለማለት “ሚካ” እንደማለት። አርቲኩሌሽን እክል በቶሎ ወደ
ሕክምና በመሂድ ችግሩን መግታት ይቻላል፡፡
የግንዛቤ-ግንኙነት እክሎች/ Cognitive-communication disorders፡- የማሰብ
ችሎታዎን የሚቆጣጠረው የአዕምሮዎ ክፍል ሲጎዳ የመግባባት ችግርን ያስከትላል። የግንዛቤ-
ግንኙነት ችግር ያለባቸው ሰዎች የመስማት፣ የመናገር፣ የማስታወስ እና ችግርን መፍታት
ያለመቻል እክሎች ሊኖራቸው ይችላል።
ዳይስአርትሪያ/Dysarthria: - አንዳንድ ጊዜ ንግግርዎን የሚቆጣጠሩት ጡንቻዎች
በስትሮክ፣ ብዙ ስክለሮሲስ (ኤምኤስ)፣ አሚዮትሮፊክ ላተራል ስክለሮሲስ ወይም ሌሎች
የነርቭ ሥርዓቶች መዛባት ምክንያት ደካማ ይሆናሉ። የአርትራይተስ ችግር ያለባቸው ሰዎች
የደበዘዘ ንግግር ሊኖራቸው ይችላል።
ኤክስፕረሲቭ እክሎች/Expressive disorders:- ያለባቸው ሰዎች ቃላትን ለማውጣት
ወይም ሃሳባቸውን ለማስተላለፍ ሊቸገሩ ይችላሉ። ከስትሮክ፣ነርቭ ፣ከእድገት መዘግየት ወይም
ከመስማት ችግር ጋር የተቆራኘ ነው።
የቅልጥፍና እክል/ Fluency disorders፡- የቅልጥፍና እክል የንግግር ፍጥነት፣ ፍሰት
እና ምትን ያበላሻል እናም የመንተባተብ (የተቋራረጠ ንግግር) የቅልጥፍና እክል ነው፤እንዲሁም
የተዋሃደ እና ፈጣን የሆነ የንግግር ውጤት ነው።
ሬሴፕቲቭ እክሎች/Receptive disorders፡-ሬሴፕቲቭ እክሎች/ያለባቸው ሰዎች
ሌሎች የሚናገሩትን ለመረዳት ይቸገራሉ።ሬሴፕቲቭ እክሎች ጉዳቱ የተወሰኑ ቃላትን
እንዲያውቁ ያደርጋል፣መመሪያዎችን ያለመከተል ችግር ወይም ንግግርን የማይፈልጉ ሊመስሉ
ይችላሉ፡፡
ሬሶነአንሰ እክሎች/Resonance disorders፡- የአፍ ወይም የአፍንጫ ካቪቲ የአየር
ፍሰትን ሲዘጉ ለድምፅ መስረት የሆኑ የንዝረቶችን ይዘት ይቀይራሉ፡፡ ሬሶነአንሰ እክሎች
የላንቃ መሰንጠቅ፣ የቶንሲል እብጠት እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን አወቃቀር ከሚነኩ
ሁኔታዎች ጋር የተቆራኘ ነው።
ከንግግር ሕክምና በተያያዘ ከስነ-ልቦና ባለሙያ ጋር ማማከር ከፈለጉ ዶክተር አለ 8809 ላይ
እየደወሉ እንመካከር፡፡ ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 2 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ
የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!
9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
በጤና፣ በግንኙነት፣ በስነ-ልቦና እና አመጋገብ ዙርያ ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት 9102 Ok ብለዉ ይጠቀሙ።
ቅድመ-ጥንቃቄ ልናደርግላቸው የሚገቡ በሽታዎች የትኞቹ ናቸው? ብዙ ሰዎችን ከሚያጠቁ በሽታዎች እራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ክብደታችንን ለመቆጣጠር አመጋገባችን እንዴት መሆን አለበት?
ከፍቅረኛ፣ ከቤተሰብ እና ከባልደረባ ጋር በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ የግንኙነት ችግሮችን እንዴት መፍታት እንችላለን?
በነዚህ ጉዳዮች ዙርያ የሚያውጠነጥኑ አጭር መልእክቶችን #በ9102 ማግኘት ይችላሉ።
9102 OK

በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን፡
የዶክተር አለ የአጭር መልእክት
9102 OK
የዶክተር አለ የስልክ ምክክር
8809
የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
http://tiny.cc/gf606y
የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
T.ME/DOCTORALLE8809
የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ
(#የሥነ #ልቦና #ባለሙያ #ሃና #በየነ
1.1K views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 07:14:54 #የፅንስ #አልባ #እርግዝና #ምልክቶቹ

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
#ዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው ጽንስ አልባ እርግዝናን በተመለከተ ሲሆን ይህ አቻ የአማርኛ ትርጓሜ ትንሽ ሊያደናግጥ የሚችል ፍቺ ቢሆንም በህክምና አጠራሩ molar pregnancy ይባላል፡፡
#ይህ የእርግዝና አይነት በሁለት አይነት መልኩ ሊከሰት ይችላል፡፡ የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ ጽንስ የሌለው የእንግዴ ልጅ መፈጠር ሲሆን ትንሽ ጽንስ የመሰለ ግን ያልሆነ ውሀ የቋጠረ ከረጢት ሊኖር ይችላል ፡፡ ሁለተኛው አይነት ደግሞ ዘላቂ ባይሆንም ጽንስ ያለው እንዴ ልጅ ሊፈጠር ይችላል ሆኖም ጽንሱ የመጀመሪያዎቹ ወራቶች ላይ የሚወርድ ይሆናል፡፡
#ምልክቶቹ
በጣም ደማቅ ቀይ ወይም ጥቁር የሆነ ከማህጸን የሚወጣ ደም
ከፍተኛ ማስመለስ እና ማቅለሽለሽ
የወይን ፍሬ የመሰለ ነገር ከብልት መውጣት
ከፍተኛ ሆድ ቁርጠት
ከጤነኛ እርግዝና የተለየ የሆድ መጠን መጨመር
የፅንስ የልብ ምት አለመሰማት እና እንቅስቃሴ አለመሰማት
በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት
የደም ማነስ
#መንስኤው
የዘረ መል ችግር
የሴት እድሜ ከ35 ሲበልጥ ወይም ከ20 አመት በታች ከሆነ
ከዚህ በፊት ፅንስ አልባ እርግዝና ከነበረ
2እና ከዛ በላይ ፅንስ መጨንገፍ
#ውስብስብ #ችግሮች
በደም ውስጥ ኢንፌክሽን መኖር
የማህፀን ኢንፌክሽን መኖር
በወሊድ ጊዜ ለደም ግፊት መጋለጥ
የደም ማነስ
#ህክምናው
ውሃ የቋጠረው ከረጢት በራሱ በብልት ይወጣል ወይም ህክምና እርዳታ ያስፈልጋል ፡፡
ወድ የዶክተር አለ ተከታታይ ስለ ፅንስ አልባ እርግዝና እና እንዲሁም አጠቃላይ ስለጤናዎ ወደ ዶክተር አለ ደውለው መመካከር ይችላሉ ለመመካከር ካሻዎ 8809 ይደውሉ ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 2 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!

9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
በጤና፣ በግንኙነት፣ በስነ-ልቦና እና አመጋገብ ዙርያ ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት 9102 Ok ብለዉ ይጠቀሙ።
ቅድመ-ጥንቃቄ ልናደርግላቸው የሚገቡ በሽታዎች የትኞቹ ናቸው? ብዙ ሰዎችን ከሚያጠቁ በሽታዎች እራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ክብደታችንን ለመቆጣጠር አመጋገባችን እንዴት መሆን አለበት?
ከፍቅረኛ፣ ከቤተሰብ እና ከባልደረባ ጋር በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ የግንኙነት ችግሮችን እንዴት መፍታት እንችላለን?
በነዚህ ጉዳዮች ዙርያ የሚያውጠነጥኑ አጭር መልእክቶችን #በ9102 ማግኘት ይችላሉ
9102 OK

በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን፡
የዶክተር አለ የአጭር መልእክት
9102 OK
የዶክተር አለ የስልክ ምክክር
8809
የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
http://tiny.cc/gf606y
የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
T.ME/DOCTORALLE8809
የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ
(#በጤና #ባለሙያ #ትዕግስት)
1.5K views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ