Get Mystery Box with random crypto!

#ጥንቃቄ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሦስት መድኃኒቶችን ህብረተሰቡ እናዳይጠቀም ማሳ | ማህደረ ጤና☞

#ጥንቃቄ

በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሦስት መድኃኒቶችን ህብረተሰቡ እናዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጠ እና በጤና ላይ ከቀላል እስከ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ፦

Titan gel፣
Mara Moja
Relief የተባሉ መድኃኒቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አሳስቧል።

መድኃኒቶቹ በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ያልተመዘገቡና በህጋዊ መንገድም ወደ አገር ዉስጥ ያልገቡ ናቸው።

Titan gel የተባለው መድኃኒት በሐኪም ብቻ በመታዘዝ ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ሲሆን ነገር ግን በድብቅና በህገወጥ መንገድ ገበያ ላይ አንደሚገኝ ታውቋቃ።

መድኃኒቶቹን ማንኛውም ግለሰብ ወይም አካል በህጋዊ ተቋማት ሆነ በህገወጥ መንገድ ሲያገኛቸው እንዳይጠቀማቸውና በባለስልጣን መስሪያቤቱ ነጻ የስልክ መስመር 8482 በአቅሪያባቸው ለሚገኙ የክልል ተቆጣጠሪዎች ወይም ለጸጥታ አካላት በመጠቆም አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።

#ሼር #Share

@tikvahethiopia