Get Mystery Box with random crypto!

#ልጆ #የንግግር #ሕክምና/speech #therapy #ያስፈልገዋል? #በቅን | ማህደረ ጤና☞

#ልጆ #የንግግር #ሕክምና/speech #therapy #ያስፈልገዋል?

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮች ዛሬ ይዘን የቀረብነው ፁሁፍ ስለ ንግግር
ሕክምና/speech therapy ሲሆን የንግግር ሕክምና ምን እንደሆነ እና ሕክምናው ለማን
እንደሚያስፈልግ እና የንግግር ሀኪም/ቴራፒስት ስራው ምን እንደሆነ የሚገልፅ ፁሁፍ ነው፤ ከ
ልጆ የአእምሮ እድገት ጋር በተያያዘ ከስነ-ልቦና ባለሙያ ጋር በመመካከር ችግሩ ስር ሳይስድ
መከላከልይቻላል፡፡ከልጆ እድገት እና አስተዳደግ ጋር በተያያዘ ከስነ-ልቦና ባለሙያ ጋር
ማማከር ከፈለጉ ዶክተር አለ 8809 ላይ እየደወሉ እንመካከር፡፡
የንግግር ሕክምና ምንድን ነው?
የንግግር ህክምና የንግግር እና የቋንቋ ችሎታዎትን ለማሻሻል የሚደረግ ህክምና ነው።
የንግግር ቴራፒስት ምን ያደርጋል?
የንግግር ቴራፒስት - የንግግር-ቋንቋ ፓቶሎጂስት ተብሎ ይጠራሉ፡፡ የንግግር እክሎችን እና
የግንኙነት/ communicationችግሮችን ይገመግማል ፣ ይመረምራል እና ያክማል። የልጆችን
በእድገት መዘግየት እንዲሁም በአካል ጉዳት ወይም በህመም ምክንያት የንግግር እክል
ያለባቸውን አዋቂዎችን ያክማሉ፡፡
የንግግር ሕክምና የሚያስፈልገው ማነው?
የንግግር ሕክምና የንግግር ችግር / communication disorders ላለባቸው ልጆች እና
ጎልማሶውች ጠቃሚ ነው፡፡እንዲሁም የመስማት ችግር/ hearing impairments
ያለባቸውን ወይም የመዋጥ ችግር /difficulty swallowing ያለባቸውን ሊረዳ ይችላል።
ለሚከተሉትን እክሎች የንግግር ሕክምና ያስፈልጋቸዋል:-
አፋሲያ/ Aphasia ፡- አፋሲያ ያለባቸው ሰዎች ማንበብ፣ መጻፍ፣ መናገር እና ቋንቋ
መረዳት ሊቸገሩ ይችላሉ። ቋንቋን የሚያስተናግደው የአንጎልዎ ክፍሎች በስትሮክ ወይም
በአካል ጉዳት ሲጎዱ አፋሲያን ሊያዳብር ይችላል።
አፕራክሲያ/ Apraxia ፡- አፕራክሲያ ያለባቸው ሰዎች ምን ማለት እንደሚፈልጉ ያውቃሉ፤
ነገር ግን ቃላት መመስረት ላይ ይቸገራሉ። የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመዋጥ ወይም ሌላ የሞተር
ችሎታዎች ላይ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል።
አርቲኩሌሽን እክሎች/ Articulation disorders፡- የንግግር እክል ያለባቸው ልጆች
ለተወሰኑ ቃላቶች ድምፆችን መፍጠር አይችሉም፡፡ ለምሳሌ፡- አንዱን ድምጽ በሌላው
ይተካሉ፣ ልክ እንደ “ሚኪ” ለማለት “ሚካ” እንደማለት። አርቲኩሌሽን እክል በቶሎ ወደ
ሕክምና በመሂድ ችግሩን መግታት ይቻላል፡፡
የግንዛቤ-ግንኙነት እክሎች/ Cognitive-communication disorders፡- የማሰብ
ችሎታዎን የሚቆጣጠረው የአዕምሮዎ ክፍል ሲጎዳ የመግባባት ችግርን ያስከትላል። የግንዛቤ-
ግንኙነት ችግር ያለባቸው ሰዎች የመስማት፣ የመናገር፣ የማስታወስ እና ችግርን መፍታት
ያለመቻል እክሎች ሊኖራቸው ይችላል።
ዳይስአርትሪያ/Dysarthria: - አንዳንድ ጊዜ ንግግርዎን የሚቆጣጠሩት ጡንቻዎች
በስትሮክ፣ ብዙ ስክለሮሲስ (ኤምኤስ)፣ አሚዮትሮፊክ ላተራል ስክለሮሲስ ወይም ሌሎች
የነርቭ ሥርዓቶች መዛባት ምክንያት ደካማ ይሆናሉ። የአርትራይተስ ችግር ያለባቸው ሰዎች
የደበዘዘ ንግግር ሊኖራቸው ይችላል።
ኤክስፕረሲቭ እክሎች/Expressive disorders:- ያለባቸው ሰዎች ቃላትን ለማውጣት
ወይም ሃሳባቸውን ለማስተላለፍ ሊቸገሩ ይችላሉ። ከስትሮክ፣ነርቭ ፣ከእድገት መዘግየት ወይም
ከመስማት ችግር ጋር የተቆራኘ ነው።
የቅልጥፍና እክል/ Fluency disorders፡- የቅልጥፍና እክል የንግግር ፍጥነት፣ ፍሰት
እና ምትን ያበላሻል እናም የመንተባተብ (የተቋራረጠ ንግግር) የቅልጥፍና እክል ነው፤እንዲሁም
የተዋሃደ እና ፈጣን የሆነ የንግግር ውጤት ነው።
ሬሴፕቲቭ እክሎች/Receptive disorders፡-ሬሴፕቲቭ እክሎች/ያለባቸው ሰዎች
ሌሎች የሚናገሩትን ለመረዳት ይቸገራሉ።ሬሴፕቲቭ እክሎች ጉዳቱ የተወሰኑ ቃላትን
እንዲያውቁ ያደርጋል፣መመሪያዎችን ያለመከተል ችግር ወይም ንግግርን የማይፈልጉ ሊመስሉ
ይችላሉ፡፡
ሬሶነአንሰ እክሎች/Resonance disorders፡- የአፍ ወይም የአፍንጫ ካቪቲ የአየር
ፍሰትን ሲዘጉ ለድምፅ መስረት የሆኑ የንዝረቶችን ይዘት ይቀይራሉ፡፡ ሬሶነአንሰ እክሎች
የላንቃ መሰንጠቅ፣ የቶንሲል እብጠት እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን አወቃቀር ከሚነኩ
ሁኔታዎች ጋር የተቆራኘ ነው።
ከንግግር ሕክምና በተያያዘ ከስነ-ልቦና ባለሙያ ጋር ማማከር ከፈለጉ ዶክተር አለ 8809 ላይ
እየደወሉ እንመካከር፡፡ ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 2 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ
የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!
9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
በጤና፣ በግንኙነት፣ በስነ-ልቦና እና አመጋገብ ዙርያ ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት 9102 Ok ብለዉ ይጠቀሙ።
ቅድመ-ጥንቃቄ ልናደርግላቸው የሚገቡ በሽታዎች የትኞቹ ናቸው? ብዙ ሰዎችን ከሚያጠቁ በሽታዎች እራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ክብደታችንን ለመቆጣጠር አመጋገባችን እንዴት መሆን አለበት?
ከፍቅረኛ፣ ከቤተሰብ እና ከባልደረባ ጋር በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ የግንኙነት ችግሮችን እንዴት መፍታት እንችላለን?
በነዚህ ጉዳዮች ዙርያ የሚያውጠነጥኑ አጭር መልእክቶችን #በ9102 ማግኘት ይችላሉ።
9102 OK

በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን፡
የዶክተር አለ የአጭር መልእክት
9102 OK
የዶክተር አለ የስልክ ምክክር
8809
የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
http://tiny.cc/gf606y
የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
T.ME/DOCTORALLE8809
የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ
(#የሥነ #ልቦና #ባለሙያ #ሃና #በየነ