Get Mystery Box with random crypto!

ነገረ-ፍፃሜ(Eschatology)

የቴሌግራም ቻናል አርማ m3mebratu — ነገረ-ፍፃሜ(Eschatology)
የቴሌግራም ቻናል አርማ m3mebratu — ነገረ-ፍፃሜ(Eschatology)
የሰርጥ አድራሻ: @m3mebratu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 324
የሰርጥ መግለጫ

Your word is true
ቃልህ እውነት ነው
ይህ ቻናል መንፈሳዊ መጽሐፍቶች÷መዝሙሮች÷ወቅታዊ ፅሁፎች
የምለቀቁበት ቻናል ነው
“እንዲህም አሉ፦ እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።”
— ሐዋርያት

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-28 16:51:55 የዮሐንስ ራዕይ መፅሐፍ ጥናት 2.8

በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ

“በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፥”ራእይ 1፥10

የጌታ ቀን ምንድነው መቼ ነው?

✥በመፅሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ "የጌታ ቀን" ለምለው አሳብ በብሉይና በአዲሱ ኪዳን የተለያዩ አውዳዊ ትርጉሞች አሉት።
በዝህ ቦታ ለተጠቀሰው የጌታ ቀን ምንድነው ለምለው የተለያዩ አመለካከቶች አሉ።

1.የፍርድ እና የእግዚአብሔር ቁጣ ቀን
2.የሳምንቱ መጀመሪያ ቀን(እሁድ)

➤የጌታ ቀን የፍርድ እና የእግዚአብሔር ቁጣ ቀን ስሆን፦ሰው እግዚአብሔርን በለመታዘዙ ሀጢያቱ ምክንያት በተፈጠረው መዘዝ አሁን ዓለም ላይ የሚታየውን ክፋት እና የጨለማውን መንግስት ለማስወገድ እግዚአብሔር ቀን ቀጥሯል። ያም ቀን የጌታ ቀን በመባል ይታወቃል። ራዕ 11፥17 ኢሳ 2፥12 ኢዩ 1፥15 ህዝ 13፥5

➤የጌታ ቀን የሳምንቱ መጀመሪያ ቀን(እሁድ) ስሆን፦ በቀደምት ቤተከርስቲያን ክርስቲያኖች የጌታን ከሙታን መነሳት ለማክበርና ለማምለክ የምሰበሰቡበትን ቀን ያመለክታል። ሀዋ 20፥7 1ቆሮ 16፥2

እንግዲህ ብዙዎች እንደምሰማሙት በዝህ ቦታ(ራዕ 1፥10) የጌታ ቀን ተብሎ የተጠቀሰው የሳምንቱን መጀመሪያ ቀን እሁድን ለማመልከት ነው። ይህ ቃል በመፅሐፍ ቅዱስ እሁድን ለማመልከት እዝህ ቦታ ብቻ ተጠቅሷል።ዮሐንስ ይህንን ራዕይ የተቀበለው በዝህ ቀን ነበር።

በመንፈስ ነበርሁ ማለት ምን ማለት ነው?
✥ሀዋርያ ዮሐንስ በመንፈስ ነበርሁ ስል፦
➤መንፈስ ቅዱስን እየሰማሁ ነበር
➤በአምልኮ እና በፀሎት ውስጥ ነበርሁ
➤በህልውናው ውስጥ ነበርሁ
➤መንፈሳዊ ነገር እያሰብኩ ነበርሁ
➤ቅዱስ ቃሉን እያሰላሰልኩ ነበርሁ
➤በመንፈስ ቅዱስ እየተነዳሁ(እየተመራሁ) ነበርሁ ማለቱ ነው።
እንግዲህ መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን ሁሉንም መልእክት ጸሀፊዎች ይፃፉልን በመንፈስ ሆነው ነው እንጅ ዝም ብለው በስጋ ህይወት እንደ ልብወለድ እንጻፍ እንጻፍ ብለው አይደለም። የእግዚአብሔርን መልእክት ልዩ የሚያደርገውም ይህ ነው። ሰው በመንፈስ የምሆንበት ግዜ አለ ደግሞም በስጋ የሚሆንበት ግዜ አለ።
በመንፈስ ስሆን፦ ይፀልያል፣መንፈሳዊ ነገርን ያስባል፣ራዕይ ያያል፣ያመልካል፣የእግዚአብሔርን ቃል ያሰላስላል፣የእግዚአብሔርን ድምፅ ይሰማል።የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችን ያንፀባርቃል።
በስጋ ስሆን፦ ስጋዊ ነገሮች ያስባል(መብላት፣መጠጣት፣የስጋ ፍሬዎችን መተግበር፣ሀጢያት መስራት ......የመሳሰሉትን ነገሮች ያደርጋል)።ከእግዚአብሔር ሀሳብ በተቃራኒው ይቆማል።

ሃዋሪያው ዮሐንስ ቀጥሎ የሚለን "በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ"ይላል።
ይህ ማለት ምን ማለት ነው?
የመለከት ድምፅ የሚሰማው በተለያዩ ምክንያቶች ነው።
1.ሰንብት መግባቱን ለማሳወቅ
2.የእስራኤል በዓላት ስደርሱ
3.ንጉሥ ስቀባ
4.ጦርነት ስሆን
5.ስብሰባ ስጠራ
6.በኢየሱስ መምጫ ግዜ
7.በዝህ ቦታ በተገለጸው መሰረት "ለአስቸኳይ መልእክት" ይነፋል።
ዮሐንስ ዞር ይህንን ድምፅ ሰማ

መልእክቴ
✥ይህ አስቸኳይ የመለከት ድምፅ ተሰምቷልና
ከእንቅልፍ እንነሳ
ግዜው ደርሷልና ወንጌልን እንመስክር
ግዜው አልቋልና እንዘጋጅ
እንፀልይ እናንብብ እናገለግል
✥ለዘመናት የሚሆን ራዕይ የሚመጣው በመንፈስ ስንሆን ነውና በመንፈስ እንሁን።
✥የእግዚአብሔርን ድምፅ ከሌላ ድምፅ እንለይ።
✥መንፈሳዊ ነገርን የሚናስብበት ግዜ አለን? ብለን ራሳችንን እንጠይቅ።
✥በመንፈስ ሆነን ሰማያዊ መገለጥ እንቀበል። ኢየሱስ ይመጣል
ይቀጥላል ....

ታናሽ ወንድማችሁ #መብራቱ መንግሥቱ ነኝ

https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp
255 viewsMebratu Mengistu Ministry(MMM), 13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 11:32:36 ፎቶዎችን በፊት ለፊት ገፁ ላይ ይዞ ብቅ ማለቱ ይታወሳል፡፡ በዘመኑ ዝነኛው የTonight Show አቅራቢ ጆኒ ካርሰን በካትሪን ኩልማን አገልግሎት ዙሪያ ሠፊ ዘገባ ይዞ ቀርቧል፡፡ በአሜሪካ የዘመኑ ቁንጮ ኮሜዲያን የነበሩት እነ ፍሊፕ ዊልሰንና ሩት ቡዚ የካትሪንን የአሰባበክ ለዛና የተክለ ሰውነት ገፅታ እያስመሰሉ በየመድረኮቻቸው ላይ ያቀርቡ እንደነበር የእግዚአብሔር ሰው ቤን ሂን በመጽሐፉ ላይ ሳይጠቅስ አላለፈም፡፡ ይህንን የካትሪን ኩልማን በምድር አጽናፍ ሁሉ መግነንን ሳስብ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰፈሩት እነዚህ ህያው የእግዚአብሔር ቃሎች ይባርኩኛል፡- አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ (መሃ2፡12)።
የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ (ነህ 12፡43)።
በዚያ ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ፥ … ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤
በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ ፈወሳቸውም። … ዝናውም ወዲያው በየስፍራው
ወደ ገሊላ ዙሪያ ሁሉ ወጣ … ወገኔ የእግዚአብሔር ሰው በአንተ ውስጥ ያደረውን መንፈስ ቅዱስ እውቅና ከሰጠኸው በቀሪ ዘመኔ ሁሉ ይጠቀምብኝና ልሙት የሚል የወንጌል ፅናት ካለህ መታሰቢያህ ፈጽሞ ጎጥ ውስጥ ተሸሽጎ አይቀርም፡፡ እግዚአብሔር አምላክህ ስለ ስሙ ሲል ተጽኖህን አለማቀፋዊ ያደርገዋል፡፡ በአንተ እውቅና ውስጥም የዘላለም አ ንዳው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አብዝቶ ያገነዋል፡፡
የካትሪን ኩልማን ወርቃማ አባባሎች
በእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ተቀብቶ ለማገልገል ምንም ዓይነት የሃይማኖት ፎርሙላ አያስፈልግም፡፡ ሚስጥሩ አንድ ነው ልክ ጌታ ኢየሱስ እንደተናገረው በርሃብ የታጀበ የማገልግል ፍቃደኝነት ብቻ፡፡
ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ። ‹‹ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ›› ብሎእንደተናገረው ማለት ነው (ዮሐ 7፡37)፡፡
• በአለም ላይ ትልቁ ስኬት ማለት ራስን ለእግዚአብሔር ፍቃድ ማስገዛት ነው፡፡
• እግዚአብሔር በዱሮ መንገድ መሄድ አይወድም፤ እንዲሁም አሮጌን ነገር አያድስም፡፡ ይልቁንም አዲስን ነገር ማድረግ እጅግ ደስ ይለዋል፡፡
• ግና የሆኑ የመርከብ ካፒቴኖች ሻካራማና አለታማ በሆኑ ባህሮች ውስጥ አልፈው ያሰቡት ቦታ መድረስ ይወዳሉ፡፡ እንዲሁ ግና የሆኑ የክርስቶስ አገልጋዮች ጠማማና አዳጋች በሆኑ የህይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፈው ከፍጻሚያቸው ጋር ይገናኛሉ፡፡
•  የእግዚአብሔር ኃይል በሙላት በእኛ ውስጥ እንዲገለጥም ሆነ እንዲሰወር ሚስጥሩ ፍቃዳችን ውስጥ ተሸሽጓል፡፡
• ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው ለደህንነታችን ብቻ ሳይሆን ለበሽታችንም ጭምር ነው፡፡ ‹‹ተፈፀመ›› ብሎ የተናገረው ስለ መዳናችን ብቻ ሳይሆን ስለ ተግዳሮቶቻችንም ያካትታል፡፡

ጃሚ ቡኪንግሃም ጎስት ሪትን ብላ በጻፈቺው መጽሐፏ ውስጥ የካትሪን ኩልማንን በርካታ የፈውስና የተሃምራት አገልግሎቶችን በሰነድ መልክ ዘግባለች፡፡ ከብዙዎቹ ጥቂቶችን የሚከተሉት ናቸው፡፡
• ቁጥራቸው ወደ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሠዎች ኪም በማስረጃ ከሚያውቀው ከተለያዩ በሽታዎችን ክሮኒክ ካንሰርንም ጨምሮ ተፈውሰዋል፡፡
• በሃይማኖት የፈውስ ተሃምራት ዙሪያ ተደጋጋሚ ጥናቶችን በማድረግ የሚታወቁት ፕሮፌሰር ከርነር የካትሪን ኩልማንን የፈውስ አገልግሎት እውነተኛነት ለማረጋገጥ በቅርብ ጊዜ ባደረጉት ጥናት መሠረት የሚከተለውን ፅሐፍ በጥናታዊ ፅሑፎቻቸውን ውስጥ አካተዋል፡፡
‹‹አንዳንድ ሠዎች በካትሪን የፈውስ አገልግሎት ዙሪያ ያለቸውን ጥርጣሬ ሲያንፀባርቁ ሰምቺያለሁ፡፡ ለዚህም ነው በካትሪን ኩልማን የፈውስ አገልግሎት ዙሪያ እውነተኝነቱን ለማረጋገጥ በርካታ ታሪካዊ ሰነዶችን ሳገላብጥ የከርምኩት፡፡ ምናልባት ከሰነድ አያያዝ ችግር ግነቶችና አጠራጣሪ ግንዛቤዎች ቢኖሩም የካትሪን ኩልማን የፈውስ አገልግሎት እውነተኛነት የሚያረጋግጡ በቂ ማስራጃዎችን እነሆ በእጆቼ ላይ ይገኛሉ፡፡ በብዙ በሽተኞች ላይ የተካሄዱት ፈውሶች አምላካዊ እጅ ካልሆነ በስተቀር በሰው ልቦና የሚታሰቡ አይደሉም›› ብለዋል፡፡
ራልፍ ዊክርሰን የደቡብ ካሊፎኒያ የክርስቲያን ሴንተር ባለራዕይና መስራች ነው፡፡ በእርሱ ላይ የመጣው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ክብር ምንጩ ካትሪን ኩልማን እንደነበረች ይናገራል፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ቤን ሂን በቆመበት አደባባዮች ሁሉ አሁን ላለው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት
መነሳሳትና መቀጣጠል ካትሪን ኩልማን ምክንያት እንደሆነቺው ይመሰክራል፡፡ እንደውም ቤን ሂን
አግዝፎ ሲናገር ‹‹የካትሪን ኩልማን የአገልግሎት ሌጋሲ የቀጠለው በእኔ አገልግሎት ነው›› እያለ ይመሰክራል፡፡ እውቋ የፔንቴኮስታል ታሪክ ዘጋቢዋ ቪንሰን ሲናን "She was a woman minister at a time when most healing evangelists were men›› ብላ ስለ ካትሪን ኩልማን ትመሰክራለች፡፡
ወገኖቼ ኢትዮጵያም በመንፈስ ቅዱስ ክብር በቅርብ ጊዜ ትወረሳለች፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሙላታዊ ክብሩን ልክ እንደ ካትሪን ኩልማን እንደውም አልቆ በእኛም አገር እናቶችና እህቶችም ላይመጠቀም ይጀምራል፡፡ ሙታን ይነሳሉ፤ አንካሶች ይዘላሉ፤ መስማትና ማየት የተሳናቸው ወንጌልን ይሰማሉ ክብሩን ይመለከታሉ፡፡ ዘመኑ ሩቅ አይደለም፡፡ እነሆ በደጅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በከባድ የመንፈስ ቅዱስ ክብር ትታረሳለች፡፡
92 viewsMebratu Mengistu Ministry(MMM), 08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 11:32:36 #ጥቂት #ስለ #ካትሪን #ኩልማን

ካትሪን ጆዋና ኩልማን.በወርሃ ግንቦት የቀኑ ቁጥር ዘጠኝ ፣ ዓመተ ምህረቱ 1907 ዓ.ም ሳለ በኮንኮረዲያ ሚዚዮሪ ግዛት ተወለደች፡፡ የዘር ሀረጓ ከወደ ጀርመን ነው፡፡ ኋላም አያቶቿ ከጀርመን ወደ አሜሪካ በስደት ነጎዱ እንጂ፡፡ ካትሪን ኩልማን ለወላጆቿ አራተኛ ልክ ናት፡፡ እናቷ በልጅነት ወራቷ እምብዛም ፍቅር አልሰጠቻትም፡፡ አባቷ ሩሩህና ደግ ነበር፡፡ ካትሪን በድምጽ አወጣጧ ሳይቀር የአባቷን ባህሪና ገጽታ ተፈጥሮ እየተከተለች አደገች፡፡ ካትሪን ኩልማን የእግዚአብሔርን ፍቅር ለመትግለጽ ስትፈልግ የአባቷን ተፈጥረአዊ አመለ ሸጋነት ከእግዚአብሔር ጥልቅ ፍቅር ጋር በምሳሌ ማነጻጸር ልማዷ ነበር፡፡
ካትሪን ኩልማን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አደኟ የተቀበለቺው ገና የ14 ዓመት ሳለች ነበር፡፡ በአንዲት የሜቶዲስት ቤተክርስቲያን ውስጥ፡፡ ብዙዎቻችን ከዚህ ቀደም ስለ ካትሪን ኩልማን አገልግሎት በተለያዩ ሚዲያዎች ደጋግመን ሰምተናል፡፡ ጥልቅ የታሪኳን ውቅር በዚህ ፕሮግራም ላይ ማንሳት ተገቢ መስሎ አልታየንም፡፡ ዳሩ ግን ካትሪን ኩልማን በዘመኗ ያመጣቺውን አለም አቀፍ ክርስቲያናዊ የአገልግሎት ተጽእኖ በጥቂቱ ለመዳሰስ እስቲ እንሞክር፤ ከዚህች ጥቂት የካትሪን ኩልማን ታሪክ ተነስተው በከባድ የመንፈስ ቅዱስ ክብር ተሞልተው ለክርስቶስ ወንጌል ለሚነሱ ኢትዮጵያውን እህቶቻችን ፍንጭ ይሰጣል ብዬ አምናለሁ፤
ኦራል ሮበርትስ ስለ ካትሪን ኩልማን ከተናገሩት በጥቂቱ፡-
መጀመሪያ ስለ ካትሪን ኩልማን የሰማሁት በ1960 ዓ.ም ገደማ ነበር፡፡ በዛን ጊዜ ካሊፎኒያ በኔብሲ በርባንክ ስቱዲዮ ውስጥ የራሴን የቴሌቪዥን የወንጌል ሥርጭት በማዘጋጀት ላይ ነበርሁ፡፡ እዛው ስቱዲዮ ውስጥ ሳለሁ ስለ ካትሪን የአገልግሎት በረከት በጥልቀት ያጫወተኝ የፕሮዳክሽን ዳይሬክተሬ ዲክ ነበር፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ እዛው ካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ ውስጥ በበነጋታው የካትሪን ክልማን ወንጌል ስርጭት እንዳለ ሰማሁ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ያዘጋ ልኝ መልካም የህይወት እንዳጋጣሚ እንደሆነ ተረዳሁ፡፡
ማልጄ ሳልሳሳ ካትሪን ኩልማን ወዳዘጋጀቺው ክሩሴድ ተጣድፌ ሄድሁ፡፡ የሚገርም መለኮታዊ ክብር ውስጥ የገባሁበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ካትሪን ኩልማን መድረክ ላይ ቆማ ስታገለግል ከዚህ ቀደም በእኔ አገልግሎት እንደነበረው አገልግሎት የተለየ መንፈሳዊ የአገልግሎት ልምምድ፣ምዕመንን እንደ ቲያትር ተመልካቾች ለማስደነቅ ተብሎ የሚደረግ የቤተስኪያን ተውኔት አላየሁም፡፡ ብቻ አንድ የአሜሪካን አብያተ ክርስቲያናት ከዚህ ቀደም ያልተለማመዱት መለኮታዊ ክብር በካትሪን ኩልማን አገልግሎት ሲከወን አየሁ፡፡ ጥቅጥቅ ያለ፣ ደመናው በሰውነት ላይ እስኪገዘፍ ድረስ የሚከብድ የእግዚአብሔር መገኘት ነበ፡፡በካትሪን አገልግሎት ላይ ጌታ ኢየሱስ በሙሉ ክብሩ እንዳለ ተሰማኝ፡፡ የመንግስተ ሠማይ መዓዛ፣ ማወዱ ብሎም እውነተኛ ትርጉሙ ገባኝ፡፡ ለካ መንግስተ ሠማይን መንግስተ ሠማይ ያደረገው ኃልወተ እግዚአብሔር በሠዎች መካከል በሙላት ሲገለጽ ነው፡፡ እርሱ ካለ ቤተስኪያን መድረክ ላይ ቆሞ ለማገልገል አይጨንቅም፤ ትግልም አይጠይቅም፡፡ ኢየሱስ ያድናል ካልን በእርግጥም የማዳን ክንዱ ያለ መከልከል ይገለጻል፡፡ በካትሪን ኩልማን አገልግሎት ያየሁት እውነታ እንዲሁ ነበር፡፡ጉባኤተኛው በሙሉ ምክንያት አልባ በሆነ የሀሴት ድባብ ውስጥ ገብቶ ዓይኑ በእምባ ራሰ፡፡ ምንም ዓይነት በሽታ፣ ሽባ መሆን፣ ዲዳ መሆን ምንም መሆን እንደ ዋዛ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኃጢያት ኑዛዜ ጋር ከእያንዳንዱ ጉባኤተኛ ውስጥ በርሮ ይጠፋ ጀመር፡፡ ይገርማል ካትሪን ኩልማን በእውቀት ቃልም የተለየ ክብር ውስጥ ነበረች፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በልዩ መረዳት ተዚህ በፊት ከተለመደው የቃል ማብራራት በተለየ መልኩ ሌላኛውን የትርጉም አንድምታ እያብራራች ትተነትን ጀመር፡፡
ካትሪን ኩልማን መድረክ ቆማ እያገለገለች በየመካከሉ እንዲህ የሚል የፀሎት አዝማች ነበራት ‹‹መንፈስ ቅዱስ ሆይ በልቤ ኩራት ነግሶ፣ ሃጢያትም ገዝፎ እንዳልበድልህ አግዘኝ›› ፡፡
የእግዚአብሔር ሰው ቤን ሂን ስለ ካትሪን ኩልማን የተናገረው በጥቂቱ አሁን ላለሁበት የአገልግሎት ስኬት ትልቅ ምክንያት የሆነቺው ካትሪን ኩልማን እንደሆነች ደጋግሜ ተናግሪያለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ለእኔም ሆነ ለሌሎች የእግዚአብሔር ሠዎች የኩልማን መንፈሳዊ አስተዋጽኦና ተጽእኖ እንዲሁ በጥቂት ቃል ብቻ ተነግሮ የሚጨረሽ አይደለም፡፡ ጊዜውን አስታውሳለሁ፡፡ ታህሳስ 21 1973 ዓ.ም ዕለተ አርብ ነበር፡፡ የግል አውቶቡስ ተከራይቼ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር በመሆን ከካናዳ ቶሮንቶ
ተነስተን አሜሪካ ውስጥ ካትሪን ኩልማን ወደምታገለግልበት የፕሪስባይቴሪያን ቤተክርስቲያን ደረስን፡፡ያን ጊዜ ዕድሜዬ 21 ዓመት ሞልቶኝ ነበር፡፡ ጌታን ከተቀበልሁ ደግሞ ገና ሁለት ዓመቴ ነበር፡፡ ይሄ ከካናዳ ወደ አሜሪካ ያደረግሁት ጉዞዬ ግን በህይወቴ አስገራሚ መንፈሳዊ ለውጥ ውስጥ እንድገባ ትልቅ ዕድል ፈጥሮልኛል፡፡
በዘመነ አዲስ ኪዳን ከሴቶች መካከል በእግዚአብሔር መገኘትና በመንፈስ ቅዱስ ተሃምራታዊ አገልግሎት እንደ ካትሪን ኩልማን በቤተክርስቲያን መካከል የተገለፀ አንስታይ የለም ሲሉ ብዙዎቹ የሪቫይቫል ታሪክ ተመራማሪ ፀሐፍት ይስማማሉ፡፡ ይህ የጥቅል ድምዳሚያቸው አነጋጋሪ ቢሆንም ካትሪን ኩልማን በዚህ የአገልግሎት ልዕቀት ውስጥ እንድትገባ ምክንያቱ ምን እንደሆነ መናገር አይዳግትም፡፡ አዎ የካትሪን ኩልማን የአገልግሎት ልዕቀት ምክንያት መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በካትሪን ኩልማን ንጽረተ አለም ያለ መንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በራስ ስብዕና ላይ የተገነባ አገልግሎት ፍፁም ሰዋዊ ነው፡፡ ለዚህ ነው ካትሪን በቆመቺበት መድረክ ላይ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ትለኸኝ እንዳትሄድ እያለች በእምባ በራሰ ፊት ተማጸኖዋን ወደ ሠማይ ዓይኖቿን አንስታ ትፀልይ የነበረው፡፡ ልክ ዳዊት በዝማሬው ‹‹ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ›› ብሎ እንደተናገረ፡፡ ለካትሪን ኩልማን ክርስትና ያለ መንፈስ ቅዱስ እንደ ፖለቲካ ተቋም ነው፡፡ ክርስትና ያለ እግዚአብሔር መገኘት እንደ እቁብና እንደ እድር ስብሰባ ነው፡፡
ይህ ቃል ካትሪን ኩልማን በአንድ ወቅት የቤተስኪያን መድረክ ላይ ቆማ የተናገረቺው ቃል ነው
"God can take everything that I have, I'll live on bread and water for the rest of my life, I'll preach the gospel from the street corner, but take not Thy Holy Spirit from me." ‹‹እግዚአብሔር ከወደደ አለኝ የምለውን ቁሳዊ ነገር ሁሉ ሊወሰድብኝ ይችላል፡፡ ከዛ በኋላ ቀሪ ዘመኔን በዳቦና በውሃ መኖር እችላለሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስን ግን አይውሰድብኝ ከዛ በኋላ እንዴት ወንጌልን እንዴት ማገልገል እችላለሁ?››
የእግዚአብሔር ሰው ቤን ሂን ‹‹Catherine Kulman Her Spiritual Legacy and Its impact on my Life ብሎ በጻፈው መጽሐፉ ላይ በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ካትሪን ኩልማን የሚለው ስም በመላው አሜሪካ ውስጥ እንዲሁም በሌሎች አገራት ውስጥ በእያንዳንዱ ቤት የሚጠራ ስም ሆኖ ነበር›› ይላል፡፡ አለማዊ ሚዲያዎች ሳይቀሩ የዛን ዘመን የመጀመሪያ የዜና ትንታኒያቸው ስለ ካትሪን ኩልማን አገልግሎት ነበር፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት የዝነኛ ሠዎች ፕሮፋይል ዘጋቢ የሆነው People magazine አራት የተለያዩ የካትሪን የአገልግሎት
64 viewsMebratu Mengistu Ministry(MMM), 08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 18:02:51 የዮሐንስ ራዕይ መፅሐፍ ጥናት ክፍል 2.7

“እኔ ወንድማችሁ ዮሐንስ፣ ከእናንተ ጋር አብሬ በኢየሱስ መከራውንና መንግሥቱን፣ ትዕግሥቱንም ተካፋይ የሆንሁ፣ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክርነት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።”
— ራእይ 1፥9 (አዲሱ መ.ት)

ምስክርነት፣መከራ፣ትዕግሥትና መንግሥት

❖ይህ ክፍል የሚያስተረን በጥልቀት ካየነው ብዙ እውነት አለ።

የፈጥሞ ደሴት

➜የፈጥሞ ደሴት ሮማውያን የሞት ፍርድ ያልተፈረደባቸወን የፖለቲካ እስረኞችን የሚታከማችበት ስፍራ ነው። በኤፌሶን ቤተከርስቲያን በመጋቢነት እያገለገለ በነበረበት ግዜ ተወስዶ በፈጥሞ እንደታሰረ የታሪክ ፀሀፊዎች ይገልፃሉ። ይህ የዮሐንስ ራዕይ መፅሐፍ የተወለደው ከዛ ከፈጥሞ ደሴት ነው። እስር ቤት ሰው አይገባም የተዘጋ ነው። ለዮሐንስ ግን ከጌታ ጋር ለመገናኘት የሰማይ በሮች ክፍት ነበሩ። ሀዋርያው ዮሀንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር መከራ እዛው ተቀብሏል። ፀሀፊዎች እንደምናገሩት ለ18 ወራት እዛው ታስሮ እንደቆየ ነው።
❖በዝህ ቁጥር በአስደናቂ ሁነታ ምስክርነት፣መከራ፣ትእግስትና መንግስት በአንድ ላይ ተገልፀው እናገኛለን።

ምስክርነት

➜ዮሐንስ የተሰደደበት ምክንያት ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ከመሆኑ የተነሳ ነው። ይህ ምስክርነትም ወንጌልን መሰበክ ነው። በዝያ ግዜ ክርስቲያኖች መከራን የሚቀበሉበት ምክንያት ከአምላክ በቀር ለሰውና ለጣኦት አንሰግድም በማለት ነበር። በዘህም የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት ሳይሸሽጉ በድፍረት ይመሰክሩ ነበር። ዮሐንስም የእግዚአብሔርን ቃል ይመሰክራቸው ነበር። ምስክርነት ያስከተለው መከራን ነበር።

መከራ(ስዴት)

➜በወንጌል ምክንያት በዛ ግዜ ያሉ ክርስቲያኖች ይሰቃዩ፣ይሰቀሉ፣ይገደሉ፣በብዙ ይንጌላቱ እንደነበር እናውቃለን። ዮሐንስና በክርስቶስ ወንድሞቹ የነበሩት ክርስቲያኖች በዝያው የመከራው ተካፋዮች ነበሩ። መከራውም በዶመቲያን ዘመን የነበረ ክርስቲያን ሁሉ ይቀበል የነበረ ነው። በአምነታቸው የተነሳ መከራወን ይቀበሉ ነበር። በክርስቶስ ማመንና መከራን መቀበል ሁልጊዜ አይነጣጠሉም። ማቲ 20፥22 ዮሐ 16፣33 ሐዋ 12፥2 14፥22 ሮመ 8።17
ይህ መከራ ወደፊት የሚገለጸው ታላቁ መከራ አይደለም። በዝያ ግዜ እየተቀበሉ ያሉት እንጅ። በእግዚአብሔር መንግሥት ተካፋይነት ያላቸው ሁሉ የዘህ ዓለም መከራ ተካፋዮች ናቸው። ቤተከርስቲያንና መከራ በታሪክ ተለያይተው አያውቁም። በዘህ ሁሉ ግን አሸናፊዎች ናቸው።

ትዕግሥት(ፅናት)

➜በመፀሀፉ ወስጥ በብዙ ቦታ ተጠቅሶ እናገኛለን። 2፣2 3፥19 3፥10 14፥22
ይህ የሚያሳየን በስዴቱ መካከል በእምነት ፀንተው መቆማቸውን ነው። እስከ መጨረሻ መፅናት ነው ለድል የሚያበቃን። ዮሐንስን 7 አብያተክርስቲያናት የትዕግስት ተካፋዮች ነበሩ።

መንግስት

የእግዚአብሔር መንግሥት አሁን የገባንበትና ወደፊት በሙላት ለመግባት በትእግስት የምንጠባበቅበት ነው። ዮሐንስ የዝህ መንግሥት ወራሾች መሆናቸውን ይነግራቸዋል። እኛም የመንግሥቱ ወራሾች ነን ሮመ 8፥17 ሉቃ 12፥32 1ተሰ 2፥12 ያዕ 2፥5

መልእክቴ

እኛ ምስክሮች እንደመሆናችን መጠን ምድራዊ ፍላጎታችና እቅዶች ግዜያችንና ትኩረታችንን ውጠው እንዳያስቀሩ እንጠንቀቅ።
መፅሐፍ የሚለው
እናንተ ምስክሮች ናችሁ
ያየነውንና የሰማነውን እንመሰክራለን
ስበኩ ነው
ስለዘህ በህይወታችን ምስክሮች እንሁን
ይህንን ምስክርነት በማጣቷ ዓለም በመጥፋ ላይ እንዳለች አንዘንጋ።
ስልጠና የወሰደውን ወጣት ሰራዊት ይዘን ለወንጌል እንነሳ
በወንጌል ምስክርነት ስራ እንጠመድ
በተለይ አያለ ወጣቶች በሴይጣን ስራ እየተማረኩ እንደሆነና ዲያብሎስ ሀይሉን አስተባብሮ እየሰራ እንዳለ በማወቅ ወጣቶች እንደ ጢሞቲዎስ ለወንጌል ምሰክርነት እንነሳ።

ይቀጥላል.......

ተጻፈ በወ/ም መብራቱ መንግሥቱ
https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp
543 viewsMebratu Mengistu Ministry(MMM), edited  15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-21 17:12:55
103 viewsMebratu Mengistu Ministry(MMM), 14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 20:41:12 የዛሬ ደስታዬ በአብርሆት ቤተመጽሐፍት

❖ይህ ቦታ ብርሃን የሚገኝበት ቦታ ነው።አብርሆት ማለት Enlightenment ብርሃን የሚገኝበት(በራ) የሚለውን ቃል ያመለክታል። ቃሉ ከነገረ-መለኮት ጋር ይገናኛል። አብርሆተ መንፈስ ቅዱስ።በቅርቡ በመንግሥታችን የተሰራው ትልቁ የጥበብ ቦታ አብርሆት Library። የእውቀት ወዳጆች እውቀትንና ጥቤብን የሚሸምቱበት ቦታ።ለእኔ ደግሞ ከጠበኩት ልዩ የሆነልኝ መንፈሳዊ ትላልቅ መፅሐፎች ተደርድረው ማግኘተ ነው። ከእውቀት ትልቁ እውቀት የተሰቀለውን ክርስቶስን ማወቅ ነው። በመጀመሪያ ዓይነ ውስጥ የገባው መፅሐፍ በወ/ዊ ፀጋአብ በቀለ የተፃፈልን "የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት የህብረትና ዓለምን በወንጌል የመድረስ ጥር"የሚለው ድንቅ መፅሐፍ ነው።
ከዝህ መፅሐፍ ያነበብኩትን ትንቢታዊ መልእክት እነሆ

........በወንጌል ስም ራስንና ገንዘብን መስበክ ሌላ ወንጌል ነው። ሌላ ወንጌል ደግሞ ፀረ ወንጌል ነው።እውነተኛ ቤተክርስቲያን ደግሞ የፀረ ወንጌል ፀር ናት። ከእንግዲህ ኢየሱስን የማይገልጥ ኢየሱስ የማይከበርበት ኢየሱስ ከፍ ብሎ የማይታይበት ኢየሱስ በቃሉና በመንፈሱ ያልነገሰበት መድረክ ሆነ አገልግሎት ከኢትዮጵያ በስሙ ስልጣን የተወገደና የተገለበጠ ይሆናል። ምድርቷ የታረደውን በግ በከፍታ የሚታከብርበት በዓል ይሆናል። ኢትዮጵያውያን በወንጌል ለወንጌል በዓለም ይታወቃሉ ይፈልጋሉ። ይህ ዘመን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የወንጌል እንቅፋት የሆኑ የኑፋቄ ትምህርቶችን፥ራስ ተኮር አካሄዶችንና አገልግሎቶቸን በቃሉ በማጥራት ወንጌልን በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ለዓለም ህዝብ በመስበክ በገሀድ የምትገለጥበት መለኮታዊ የቀጠሮ ዘመኗ ነው። አሜን
ወንጌል ከኢትዮጵያ ለዓለም ሁሉ!!
አብርሆትን ይጎብኙ!!

@መብራቱ መንግሥቱ 2015 ዓ.ዓ አ አ ኢትዮጵያ
https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp
157 viewsMebratu Mengistu Ministry(MMM), 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 09:11:17
144 viewsMebratu Mengistu Ministry(MMM), 06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 15:33:09 የዮሐንስ ራዕይ መፅሐፍ ጥናት 2.6

““ያለውና የነበረው፣ የሚመጣውም፣ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ፣ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ” ይላል።” ራእይ 1፥8 (አዲሱ መ.ት)

የእግዚአብሔርን ባህርይ የሚገልጹ መለኮታዊ ስሞች

❖በመፅሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ብዙ የእግዚአብሔርን ባህርይ የምገልፁ ስሞች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ በራዕይ መፅሐፍ ውስጥ እግዚአብሔር አብንና ወልድን ባህርያቸውን የሚገልፁ ስሞች ተጠቅሰው እናገኛለን። እነዝህ ስሞች የሚያሳዩን እግዚአብሔር መለኮታዊ ዓላማዎቹን በሰው ልጆች ውስጥ እንደምፈፅም ነው። በተጨማሪም የእግዚአብሔርን አለመለወጥንና ዘላለማዊነትን እንረዳለን። እንዝህ ስሞች እግዚአብሔር በይበልጥ እንድናወድሰው ያነሳሱናል።ይህ ክፍል እግዚአብሔር አብ በራዕይ መፅሐፍ ውስጥ ስለ ራሱ ዘላለማዊነትና ሁሉ ቻይነት የተናገራቸው የመጀመሪያ ክፍል ነው። ለላው እግዚአብሔር ስለ ራሱ የተናገረው ቦታ 21፥5-8። በራዕይ መፅሐፍ ውስጥ 5 እኔ እኔ ነኝዎች አሉ።1፥8 2፥27 26፥6 22፥16 1፥17። እኔ እኔ ነኝ ብሎ መለኮታዊነቱን የሚናገረው እግዚአብሔር ብቻ ነው።ዘፀ 3፥14 እሳ 48፥14
➜በዘህ ስፍራ የእግዚአብሔርን ማንነት የሚገልፁ ስሞች ተጠቅሰዋልሷ።

1.ያለውና የነበረው የሚመጣም፦ የእግዚአብሔርን ዘላለማዊነት የሚገልጽ ስም ነው። አምላካችን ኗሪ አምላክ ነው አይለወጥም።
❖እግዚአብሔር ወደፊታችንን የሚያውቅ እና የሚቆጣጠር አምላክ ነው።
❖እግዚአብሔር ዛሬም በምን ሁነታ ውስጥ እንዳለን የሚያውቅና የሚቆጣጠር አምላክ ነው።
ኤል-ኦላም፦ እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው።

2. ሁሉ ቻይ El-Shadi፦ በራዕይ ውስጥ ይህ ቃል 9 ግዜ ተጠቅሷል። 1፥8 4፥8 11፥7 15፥3 16፥7፣14 19፥6፣15 21፥22

3.ጌታ አምላክ፦ ከእግዚአብሔር ቁጥጥር ውጭ የሆነ ፍጥረት የለም። ሁሉ ይገዛለታል ለሁሉም ጌታ እርሱ ብቻ ነው። ጌታችንና አምላካችን እርሱ መላእክት(የወደቁትና ያልወደቁት)፣ ነገስታትና ፍጥረታት ሁሉ የምገዛለት ጌታ ነው። ያህዌ-ሳባኦት ጌታችን ሀያል አምላክ ነው። የተፈጥሮንም ይሁን ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ይቆጣጠራል።

4. አልፋና ኦመጋ፦ የግሪክ ቃል ነው። የግሪክ ቋንቋ 24 ፍዴሎች ያሉት ስሆን የመጀመሪያው "አልፋ" የመጨረሻው "ኦመጋ" ነው። በእኛ ሀ እና ፐ ማለት ነው። ይህ ቃል በራዕይ ውስጥ 3 ቦታ ተጠቅሷል። 1፥8 21፥6 22፥13
ይህም የእግዚአብሔርን መለኮታዊነት፥ ዘላለማዊነቱን የሚያውጅ ነው።እርሱ ፊተኛና ኋለኛ ነው ከእርሱ በፊት የኖረ የለም ያለ እርሱ የሚኖርም የለም። የሁሉም ጀማሪ ነው።

ታሪክን የሚቆጣጠር አምላክ እርሱ ነው።
በእኛም ህይወት ውስጥ የሆነው ሁሉ በእርሱ ነው።
የኖርነውና የሚንኖረው በእርሱ ነው።
የዳንነውና የሚንድነው በእርሱ ነው።
❖እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው።
❖የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ ነው።
❖አፅናኛችን መንፈስ ቅዱስ ዘላለማዊ ነው።
“አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፣ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”
— ራእይ 22፥13 (አዲሱ መ.ት)

ይቀጥላል.....

#ተጻፈ በወ/ም መብራቱ መንግሥቱ
https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp
627 viewsMebratu Mengistu Ministry(MMM), 12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 10:07:53
102 viewsMebratu Mengistu Ministry(MMM), 07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 10:06:19 ረድኤታችን የሆንከው ጌታችን ሆይ፣ “ክብርህን ተጠሚዎች፣ ለራሳቸው ፈቃድ የሞቱ ባሪያዎችና ታማኝ የወንጌል ዐደራ ጠባቂዎች አድርገን። በመከራችን ደግሞ ጸጋህን አብዛልን”። አሜን!

* ተስፋፍቶ በድጋሚ የቀረበ *

በ Girma Bekele (ዶ/ር) የተጻፈ።

#ተሐድሶው_ሲታወስ
#ጆን_ካልቪ
https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp
98 viewsMebratu Mengistu Ministry(MMM), 07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ