Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቂት #ስለ #ካትሪን #ኩልማን ካትሪን ጆዋና ኩልማን.በወርሃ ግንቦት የቀኑ ቁጥር ዘጠኝ ፣ ዓ | ነገረ-ፍፃሜ(Eschatology)

#ጥቂት #ስለ #ካትሪን #ኩልማን

ካትሪን ጆዋና ኩልማን.በወርሃ ግንቦት የቀኑ ቁጥር ዘጠኝ ፣ ዓመተ ምህረቱ 1907 ዓ.ም ሳለ በኮንኮረዲያ ሚዚዮሪ ግዛት ተወለደች፡፡ የዘር ሀረጓ ከወደ ጀርመን ነው፡፡ ኋላም አያቶቿ ከጀርመን ወደ አሜሪካ በስደት ነጎዱ እንጂ፡፡ ካትሪን ኩልማን ለወላጆቿ አራተኛ ልክ ናት፡፡ እናቷ በልጅነት ወራቷ እምብዛም ፍቅር አልሰጠቻትም፡፡ አባቷ ሩሩህና ደግ ነበር፡፡ ካትሪን በድምጽ አወጣጧ ሳይቀር የአባቷን ባህሪና ገጽታ ተፈጥሮ እየተከተለች አደገች፡፡ ካትሪን ኩልማን የእግዚአብሔርን ፍቅር ለመትግለጽ ስትፈልግ የአባቷን ተፈጥረአዊ አመለ ሸጋነት ከእግዚአብሔር ጥልቅ ፍቅር ጋር በምሳሌ ማነጻጸር ልማዷ ነበር፡፡
ካትሪን ኩልማን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አደኟ የተቀበለቺው ገና የ14 ዓመት ሳለች ነበር፡፡ በአንዲት የሜቶዲስት ቤተክርስቲያን ውስጥ፡፡ ብዙዎቻችን ከዚህ ቀደም ስለ ካትሪን ኩልማን አገልግሎት በተለያዩ ሚዲያዎች ደጋግመን ሰምተናል፡፡ ጥልቅ የታሪኳን ውቅር በዚህ ፕሮግራም ላይ ማንሳት ተገቢ መስሎ አልታየንም፡፡ ዳሩ ግን ካትሪን ኩልማን በዘመኗ ያመጣቺውን አለም አቀፍ ክርስቲያናዊ የአገልግሎት ተጽእኖ በጥቂቱ ለመዳሰስ እስቲ እንሞክር፤ ከዚህች ጥቂት የካትሪን ኩልማን ታሪክ ተነስተው በከባድ የመንፈስ ቅዱስ ክብር ተሞልተው ለክርስቶስ ወንጌል ለሚነሱ ኢትዮጵያውን እህቶቻችን ፍንጭ ይሰጣል ብዬ አምናለሁ፤
ኦራል ሮበርትስ ስለ ካትሪን ኩልማን ከተናገሩት በጥቂቱ፡-
መጀመሪያ ስለ ካትሪን ኩልማን የሰማሁት በ1960 ዓ.ም ገደማ ነበር፡፡ በዛን ጊዜ ካሊፎኒያ በኔብሲ በርባንክ ስቱዲዮ ውስጥ የራሴን የቴሌቪዥን የወንጌል ሥርጭት በማዘጋጀት ላይ ነበርሁ፡፡ እዛው ስቱዲዮ ውስጥ ሳለሁ ስለ ካትሪን የአገልግሎት በረከት በጥልቀት ያጫወተኝ የፕሮዳክሽን ዳይሬክተሬ ዲክ ነበር፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ እዛው ካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ ውስጥ በበነጋታው የካትሪን ክልማን ወንጌል ስርጭት እንዳለ ሰማሁ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ያዘጋ ልኝ መልካም የህይወት እንዳጋጣሚ እንደሆነ ተረዳሁ፡፡
ማልጄ ሳልሳሳ ካትሪን ኩልማን ወዳዘጋጀቺው ክሩሴድ ተጣድፌ ሄድሁ፡፡ የሚገርም መለኮታዊ ክብር ውስጥ የገባሁበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ካትሪን ኩልማን መድረክ ላይ ቆማ ስታገለግል ከዚህ ቀደም በእኔ አገልግሎት እንደነበረው አገልግሎት የተለየ መንፈሳዊ የአገልግሎት ልምምድ፣ምዕመንን እንደ ቲያትር ተመልካቾች ለማስደነቅ ተብሎ የሚደረግ የቤተስኪያን ተውኔት አላየሁም፡፡ ብቻ አንድ የአሜሪካን አብያተ ክርስቲያናት ከዚህ ቀደም ያልተለማመዱት መለኮታዊ ክብር በካትሪን ኩልማን አገልግሎት ሲከወን አየሁ፡፡ ጥቅጥቅ ያለ፣ ደመናው በሰውነት ላይ እስኪገዘፍ ድረስ የሚከብድ የእግዚአብሔር መገኘት ነበ፡፡በካትሪን አገልግሎት ላይ ጌታ ኢየሱስ በሙሉ ክብሩ እንዳለ ተሰማኝ፡፡ የመንግስተ ሠማይ መዓዛ፣ ማወዱ ብሎም እውነተኛ ትርጉሙ ገባኝ፡፡ ለካ መንግስተ ሠማይን መንግስተ ሠማይ ያደረገው ኃልወተ እግዚአብሔር በሠዎች መካከል በሙላት ሲገለጽ ነው፡፡ እርሱ ካለ ቤተስኪያን መድረክ ላይ ቆሞ ለማገልገል አይጨንቅም፤ ትግልም አይጠይቅም፡፡ ኢየሱስ ያድናል ካልን በእርግጥም የማዳን ክንዱ ያለ መከልከል ይገለጻል፡፡ በካትሪን ኩልማን አገልግሎት ያየሁት እውነታ እንዲሁ ነበር፡፡ጉባኤተኛው በሙሉ ምክንያት አልባ በሆነ የሀሴት ድባብ ውስጥ ገብቶ ዓይኑ በእምባ ራሰ፡፡ ምንም ዓይነት በሽታ፣ ሽባ መሆን፣ ዲዳ መሆን ምንም መሆን እንደ ዋዛ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኃጢያት ኑዛዜ ጋር ከእያንዳንዱ ጉባኤተኛ ውስጥ በርሮ ይጠፋ ጀመር፡፡ ይገርማል ካትሪን ኩልማን በእውቀት ቃልም የተለየ ክብር ውስጥ ነበረች፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በልዩ መረዳት ተዚህ በፊት ከተለመደው የቃል ማብራራት በተለየ መልኩ ሌላኛውን የትርጉም አንድምታ እያብራራች ትተነትን ጀመር፡፡
ካትሪን ኩልማን መድረክ ቆማ እያገለገለች በየመካከሉ እንዲህ የሚል የፀሎት አዝማች ነበራት ‹‹መንፈስ ቅዱስ ሆይ በልቤ ኩራት ነግሶ፣ ሃጢያትም ገዝፎ እንዳልበድልህ አግዘኝ›› ፡፡
የእግዚአብሔር ሰው ቤን ሂን ስለ ካትሪን ኩልማን የተናገረው በጥቂቱ አሁን ላለሁበት የአገልግሎት ስኬት ትልቅ ምክንያት የሆነቺው ካትሪን ኩልማን እንደሆነች ደጋግሜ ተናግሪያለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ለእኔም ሆነ ለሌሎች የእግዚአብሔር ሠዎች የኩልማን መንፈሳዊ አስተዋጽኦና ተጽእኖ እንዲሁ በጥቂት ቃል ብቻ ተነግሮ የሚጨረሽ አይደለም፡፡ ጊዜውን አስታውሳለሁ፡፡ ታህሳስ 21 1973 ዓ.ም ዕለተ አርብ ነበር፡፡ የግል አውቶቡስ ተከራይቼ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር በመሆን ከካናዳ ቶሮንቶ
ተነስተን አሜሪካ ውስጥ ካትሪን ኩልማን ወደምታገለግልበት የፕሪስባይቴሪያን ቤተክርስቲያን ደረስን፡፡ያን ጊዜ ዕድሜዬ 21 ዓመት ሞልቶኝ ነበር፡፡ ጌታን ከተቀበልሁ ደግሞ ገና ሁለት ዓመቴ ነበር፡፡ ይሄ ከካናዳ ወደ አሜሪካ ያደረግሁት ጉዞዬ ግን በህይወቴ አስገራሚ መንፈሳዊ ለውጥ ውስጥ እንድገባ ትልቅ ዕድል ፈጥሮልኛል፡፡
በዘመነ አዲስ ኪዳን ከሴቶች መካከል በእግዚአብሔር መገኘትና በመንፈስ ቅዱስ ተሃምራታዊ አገልግሎት እንደ ካትሪን ኩልማን በቤተክርስቲያን መካከል የተገለፀ አንስታይ የለም ሲሉ ብዙዎቹ የሪቫይቫል ታሪክ ተመራማሪ ፀሐፍት ይስማማሉ፡፡ ይህ የጥቅል ድምዳሚያቸው አነጋጋሪ ቢሆንም ካትሪን ኩልማን በዚህ የአገልግሎት ልዕቀት ውስጥ እንድትገባ ምክንያቱ ምን እንደሆነ መናገር አይዳግትም፡፡ አዎ የካትሪን ኩልማን የአገልግሎት ልዕቀት ምክንያት መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በካትሪን ኩልማን ንጽረተ አለም ያለ መንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በራስ ስብዕና ላይ የተገነባ አገልግሎት ፍፁም ሰዋዊ ነው፡፡ ለዚህ ነው ካትሪን በቆመቺበት መድረክ ላይ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ትለኸኝ እንዳትሄድ እያለች በእምባ በራሰ ፊት ተማጸኖዋን ወደ ሠማይ ዓይኖቿን አንስታ ትፀልይ የነበረው፡፡ ልክ ዳዊት በዝማሬው ‹‹ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ›› ብሎ እንደተናገረ፡፡ ለካትሪን ኩልማን ክርስትና ያለ መንፈስ ቅዱስ እንደ ፖለቲካ ተቋም ነው፡፡ ክርስትና ያለ እግዚአብሔር መገኘት እንደ እቁብና እንደ እድር ስብሰባ ነው፡፡
ይህ ቃል ካትሪን ኩልማን በአንድ ወቅት የቤተስኪያን መድረክ ላይ ቆማ የተናገረቺው ቃል ነው
"God can take everything that I have, I'll live on bread and water for the rest of my life, I'll preach the gospel from the street corner, but take not Thy Holy Spirit from me." ‹‹እግዚአብሔር ከወደደ አለኝ የምለውን ቁሳዊ ነገር ሁሉ ሊወሰድብኝ ይችላል፡፡ ከዛ በኋላ ቀሪ ዘመኔን በዳቦና በውሃ መኖር እችላለሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስን ግን አይውሰድብኝ ከዛ በኋላ እንዴት ወንጌልን እንዴት ማገልገል እችላለሁ?››
የእግዚአብሔር ሰው ቤን ሂን ‹‹Catherine Kulman Her Spiritual Legacy and Its impact on my Life ብሎ በጻፈው መጽሐፉ ላይ በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ካትሪን ኩልማን የሚለው ስም በመላው አሜሪካ ውስጥ እንዲሁም በሌሎች አገራት ውስጥ በእያንዳንዱ ቤት የሚጠራ ስም ሆኖ ነበር›› ይላል፡፡ አለማዊ ሚዲያዎች ሳይቀሩ የዛን ዘመን የመጀመሪያ የዜና ትንታኒያቸው ስለ ካትሪን ኩልማን አገልግሎት ነበር፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት የዝነኛ ሠዎች ፕሮፋይል ዘጋቢ የሆነው People magazine አራት የተለያዩ የካትሪን የአገልግሎት