Get Mystery Box with random crypto!

@CR7 viva: እንዲህ_ይመስለኛል ~±±±~±±±~~~ ከእለታት አንድ ቀን ስም እየተሰጠ | 💌💌💌💌MESSAGE 💌💌💌💌

@CR7 viva:
እንዲህ_ይመስለኛል

~±±±~±±±~~~

ከእለታት አንድ ቀን ስም እየተሰጠ
ለፍጥረታት ሁሉ እየተመረጠ
አንድ ሰው መጥቶ መድረክ ላይ ቆመና
”አባት” ነህ ተባለ ምግባሩም ታየና

ከዛም ባለተራ አንዲት ሴት ብቅ አለች
”እህት” ነሽ ተብላ እሷም ተሰየመች
ደግሞ አንዱ ሲመጣ እሱም ደርሶት እጣ
”ወንድም” ነህ ብለውት ከመድረኩ ወጣ
”አክስት፣አጐት፣አያት” ሁሉም ጥሪ አገኙ
እንደ ምግባራቸው በስሞች ተቀኙ፤

በስተ መጨረሻ አንዲት ሴት ብቅ አለች
በመልካምነቷ ከኋላ የቀረች ፣
ስም አውጭውም ያኔ በጣም ተጨነቀ
ስሟን ምን እንደሚል ፍፁም አላወቀ፣
”ተናገር! ተናገር!” ብለው አጣደፉት
አንድ ስም ስለሷ መናገር አቅቶት
ጭንቀት ሲበዛበት አንዲት ቃል አምልጣ
”እ…” ሲል ተሰማች ከፀጥታው በልጣ፤

ስም ሳይገኝላት ይህ በእንዲህ እያለ
ስም ማውጫው ዳቦ አልቆ ትሪው ተሰቀለ፣
ከዛም ”ማን ናት?” ሲባል ያች መልካሟ ሴት
”’እ’ ናት ” ብለው አሉ ስም ሳይገኝላት
ስም አውጭውም ሰምቶ ዝም ስላላቸው
መስሏቸው ቀጠሉ የተቀበላቸው
እንጂማ ቢሞከር ምግባሯን ለመስፈር
ስንት ስም ተጠርቶ ምን ይበቃት ነበር።

ፈጣሪ ለእናቶቻችን ረጅም እድሜ ይስጥልን።

ይ ላ ሉ
@yenagtm
@yenagtm
@yenagtm