Get Mystery Box with random crypto!

የዲያሪ ላይ ጥቅሶች ❤️💋💋(1)

የቴሌግራም ቻናል አርማ lovediary1 — የዲያሪ ላይ ጥቅሶች ❤️💋💋(1)
የቴሌግራም ቻናል አርማ lovediary1 — የዲያሪ ላይ ጥቅሶች ❤️💋💋(1)
የሰርጥ አድራሻ: @lovediary1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.16K
የሰርጥ መግለጫ

✍ለምን ወደድኩህ?
እንጃ።
✍ምንህ ተመቸኝ?
እንጃ
✍እንዴት ማረከኝ?
እንጃ
✍ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት፤
✍ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
✍በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
✍ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት::
@vip_vine
@Lovediary1

------------------------

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 13:35:13 ደስታችንን የሚከለክሉ 7 ነገሮች

1) ራስን መጥላት/ራስን መወንጀል
2) ያለፈውን መተው አለመቻል
3) ይቅር ማለት አለመቻል
4) ማንነታችንን አለመንከባከብ
5) የእርስዎን ዋጋ ከሌላ ማረጋጋጫ መፈለግ
6) እርስዎ ማን እንደሆኑ ለሌሎች እንዲገልጹ መፍቀድ
7) ፍጹም ለመሆን መሞከር

ምንም አደጋ ከልተጋፈጥን, ምንም ሽልማት የለም.
ምንም ህመም ከሌለ, እድገት የለም.
ምንም ሐቀኝነት ከሌለ, ግልጽነት የለም.
መተማመን የለም, ጓደኝነት የለም.
ዲሲፕሊን የለም ተሰጥኦ የለም።
ምንም ቁርጠኝነት ከሌለ, ፍቅር የለም.
ምንም ኢንቬስትመንት ከሌለ, ሀብት የለም.
ምንም ድፍረት ከሌለ, ለራስ ክብር መስጠት የለም.
እራስን ማንጸባረቅ ከሌለ, ጥበብ የለም፤
ምናባዊ ፈጠራም የለም.


171 views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 21:20:26 በማላዊ ርዕሱ የፊደል ስህተት እንዳለበት ከመታወቁ በፊት!
"ባለቤትህን በ30 ቀን እንዴት መቀየር ይቻላል" የሚል ርዕስ ያለው መፅሃፍ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት ሚሊዮን ኮፒ ተሽጧል፣

ትክክለኛው ርዕስ፡- "ህይወቶን በ30 ቀናት ውስጥ እንዴት መቀየር ይቻላል" የሚል ነው። ከታረመ በኋላ፣ ወሩን ሙሉ፣ የተሸጡት 3 ቅጂዎች ብቻ ናቸው።

የሞራል ትምህርት፡ ማንም ሰው እራሱን/ራሷን መለወጥ አይፈልግም ነገር ግን ሌላ ሰው ለመለወጥ ሁሉንም ነገር ያደርጋሉ"...
መጀመሪያ እራሳችንን ለመለወጥ እንትጋ።
እርስ በርሳችንም እንታስ። የተወለድነው አብረን ለመኖር ነው። ፍቅር ሕይወት ነው ሕይወትም ፍቅር ነው።
መልካም ምሽት ለእርስዎ
395 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 18:48:38 ክረምት ሲመጣ ሁሌም የማስታውሳት የልጅነት ቅሌት አለችኝ ውርደት በሏት
እኛ ሰፈር አዲስ የመጣች ቆንጅየ ልጅ ነበረች አቤት አይኗ ስታየኝ ውስጤ ደስ
የሚል ተሰምቶኝ የማያውቅ ደስታ ይሰማኝ ጀምሯል በር ላይ እሷን ለማየት ስራየ
ብየ ቆሜ መዋል ሆኗል ስራየ በአይን ሰላም መባባልም ጀምረናል
አሁን እሷን ለመቅረብ ጥሩ አጋጣሚ ተፈጥሮልኛል ከሰፈር ልጆች ጋር የክረምት
ትምህርት ልንማር ተነጋግረናል እናም እሷን ሄጀ ነገ ከኔጋ አብረን ሄደን Class
እንጀምራለን ጠዋት በር ላይ እጠብቅሻለሁ አልኳት እሷም ቤት መዋል ደብሯት
ስለነበር በደስታ ተቀበለችኝ እሺ አብረን እንሄዳለን አለችኝ
ነጋ
ጠዋት ተነስቼ አዲስ የታጠቡልኝን ከላይ ነጭ ቲሸርት ከታች ጂንስ ሱሪ ለብሼ
ወጣሁ ትንሽ ቆይታ የኔ ቃጀል መጣች
በመካከላችን ለውሃ መፋሰሻ የተቆፈረ አነስተኛ ጉድጓድ ነበር እናም በጊዜው
አያቸው የነበሩ የቦሊዉድ ፊልሞች ወለል ብለው ታዩኝ እሷን ማማለል
እንዳለብኝ ተሰማኝ
አብሶ በዛ ሰሞን ክሪሽ የሚል ፊልም አይቼ ነበር እንደውም ሀርቲክ ከ ፈረሱ ጋር
ሩጫ የሚገጥምበት እየዘለለ የሚሄድበት እሱ ፊልም ትዝ አለኝ
እናም ጉድጓዱን በተለየ መንገድ ለመዝለል አስቤ ወደሰማይ ተስፈንጥሬ እግሬን
ጉድጓዱን አልፎ ካለው መሬት ለማሳረፍ ስሞክር መሬት ከዳችኝ የት
አውቅሀለው አለችኝ ጭቃው አዳለጠኝ በሰማይ ላይ ተንሳፍፌ ጭቃው ላይ
በጀርባየ ተነጠፍኩ
እንደሚገነዝ አስክሬን ተዘረጋሁ በማሽን እንደተላገ ጣዉላ ከእግር ጣቴ እስከ ራስ
ቅሌ ቅርፅ ይዤ ንጥፍ አልኩ ወደላይ በጣም ዘልየ ስለነበር ስወድቅ መሬቱ
አናቴን ጠለዘኝ ብዥ አለብኝ መውደቄንም ያወኩት ቆይቼ ነበር የሆነ የመኪና
አደጋ አይነት ነገር የደረሰብኝ ነበር የመሰለኝ ወድቄ ላየኝ ሰው አረብ ሀገር
አሰሪዋ ከፎቅ የወረወረቻት ሰራተኛ እንጂ ሲዘል የወደቀ ሰው አልመስልም
አረ አረ እኔን አፈር ልብላ እኔን ውይ ውይ አልተረፈም እኮ አንሱት እንጂ የሚል
የትልቅ ሰው ድምፅ ይሰማኛል የጓደኛየ እናት ነበሩ ከጓደኞቻቸው ጋር እያለፉ
ነበር አሁን ነቃሁ ቀና ስል በእናቶች ተከብቤ ነበር በራሴ ለመነሳት ሞከርኩ
አልቻልኩም ደጋግፈው አነሱኝ ልብሴ ሙሉ ጭቃ ብቻ ሆኗል
እናቴ መጣች ቀስ ብለህ አቴድም ምን ያንቀለቅልሃል ደሞኮ ትላንት የታጠበ
ልብስ ነው የለበሰው ለነገሩ አንተ አታጥብ ምን አለብህ ና አሁን ግባና ልብስ
ቀይር ጮኸችብኝ
አረ ተይ እንዲህ አይባልም ፈጣሪ እንኳን አተረፈልኝ በይ አሏት እናቴን ጓደኞቿ
ተሸማቅቄ አንገቴን ደፍቼ ከመግባቴ በፊት ዞር ብየ በሀፍረት ፍቅሬን ለማየት
ስሞክር እየሳቀች በእጆቿ ቻው አለችኝ አቤት ውርደት
.
.
ክሪሽና የስራህን ይስጥህ
536 views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 18:01:45 ሰላም ቤተሰቦች። ቆሻሻ ምንም ማንነቱን ቢደብቅ ምንም ውብ ሁኖ ቢቀመጥ በአስቀያሚ ጠረኑ ይለያል። አስመሳይ ሰውም እንደዚያው ነው። የጊዜ ጉዳይ ነው የውርደት ፅዋን ይጎነጫል። እናንተ ደግሞ የክብርን።
664 views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:39:13 መለወጥ ያለበት ነገር!

አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን መለወጥ ሲገባቸው ፍቅረኛ እየለዋወጡ የራሳቸውንና የሰውን ዘመን የሚያባክኑት ነገርስ?
169 views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:38:58 ይድረስ እወድሻለሁ እወድሀለሁ እያላችሁ በሰው ስሜት ለምትቀልዱት። እያመነችህ ስትከዳት፤ እወድሻለሁ እያልክ ስታታልላት፤ ያኔ ስታዝንብህ
እናት እና አባታን በልጅነታ ተነጥቃ ጎዳና እንደወጣች ህፃን። ያያት ሁሉ አሞኝቶ ልጅነታን ሊቀጥፍ እንደሚጎጎ
ብርድ እና ነፋስ ተፈራርቆባት ሆዳ በረሀብ ታጥፋ ርቦኝ ነው 1ብር ስጡኝ የዳቦ ብላ በልጅ ፊታ ስትማፀን <<ሂጅ ከዚህ የዲቃላ ልጅ >> እንደተባለች፣ ምስኪን ሴት ረሀባን ረስታ በሀዘን ልባ እንደደማ ህፃን ከነበረ... ወየውልህ ሴት አይወጣልህም።
169 viewsedited  06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 22:55:30
Yeteleyayu scarfs Maserat metfelgu dewelew yanagrun 0925694983
975 views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 18:03:30 የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ካልተጫወቱ ይጨንቃቸዋል፡፡ ሲጫወቱ ደግሞ የበለጠ ይጨንቃቸውና ከፍ ባለ ገንዘብ ይጫወታሉ፡፡ አንዳንዴ በቁማሩ ምክኒያት ገንዘብ እያባከኑ ወይም ከቤተሰብ ጋር እየተጣሉም መጫወታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እንዴት እንደሚያስቡ ካልተረዳን ድርጊታቸው ትርጉም አይሰጥም፡፡ የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች የሚስቡበት መንገድ በጥቂቱ፦

ሲያሸንፉ በችሎታ ነው፤ ሲሸነፉ በእድል ነው፡፡

ችሎታ የሚያስፈልጋቸው የቁማር ጨዋታዎች አሉ፡፡ እንደ ፑል ወይም አንዳንድ የካርታ ጨዋታዎች፡፡ ወይም እውቀት የሚፈልጉ ውርረዶች እንደ የስፓርት ውድድሮች፡፡ ነገር ግን የፈለገ ችሎታ ቢጠይቁ ሁሉም የቁማር ጨዋታዎች እድል ይፈልጋሉ፡፡ ማሸነፍም መሸነፍም ውስጥ ከችሎታ በተጨማሪ( አንዳንድ ጨዋታዎች ላይ ሙሉ በሙሉ) እድል አለ፡፡ የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ግን ሲያሸንፉ በችሎታ፣ ሲሸነፉ ግን በእድል እንደሆነ ነው የሚያስቡት፡፡

መርጦ ማስታወስ፦

የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ያሸነፉባቸውን ጥቂት ጨዋታዎች ጥርት አድርገው ሲያስታውሱ የተሸነፉባቸውን ብዙ ጨዋታዎች ይረሳሉ፡፡ በተጨማሪም 'ለጥ..ቂት!' የተሸነፉትን እንዳሸነፋ አድርገው ነው የሚያስታውሱት፡፡ ይህ የወደፊቱን ጨዋታ የማሸነፍ እድላቸውን ሲያሰሉ በተዛባ መንገድ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ "ሁሉንም ልክ ነበርኩ። ማንቺስተር ባይሸነፍ 20ሺ በላ ነበር" ይላሉ።

የተወሰነ ጨዋታ ቢበሉም ቁማሩን ከፍ ባለ ገንዘብ እስከቀጠሉ ድረስ የተበሉትን እንደሚያስመልሱ ያስባሉ፡፡ በዚህ ምክኒያት ለሌላ ሰው የሚያስደነግጥ ብር እየተበሉም ምንም አይመስላቸውም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ከተሸነፉ እድል ወደ እነሱ እንደምታዘነብል ያምናሉ፡፡ (they commit Monte Carlo fallacy) ልክ አንድ ልጅ ሲወለድ ሴት ወይም ወንድ የመሆን እድሉ ግማሽ ለ ግማሽ ቢሆንም ከዚህ በፊት ሁለት ሴቶች መውለድ የሚቀጥለውን ወንድ የመሆኑን አድል የሚጨምረው እንደሚመስላቸው ሰዎች፡፡

ስለ ቤቲንግ ሱስ ፌስቡክ ላይ መረጃ ስፈልግ አንድ ግሩፕ አጋጠመኝ። ቤጉማ ይባላል። 26 ሺ አባላት አሉት። የቤቲንግ ጉዳተኞች ማህበር ማለት ነው። የቤቲንግ ሱስ የሚታከም የአእምሮ ህመም ነው።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
1.6K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 04:49:54 #ልሙት_ናፍቀሽኛል

እኔ እየጠበኩሽ...
አእላፍ ክረምቶች እየወጡ ገቡ
ምን እንደሆን እንጃ
ቱቲ መስከረሞች አንዳች ነገር ጠቡ

እኔ እየጠበኩሽ...
ሺህ ጥንዶች ተፋተው ሺዎች ተዋደዱ
ካ'ራት ኪሎው መንግስት
ብዙዎቹ መተው ብዙዎቹ ሄዱ

እኔ እየጠበኩሽ...
"ባ'ስራ ሰባት መርፌ የተሰፋው ቁንጣ"
ለዘመን ቆሽሾ ከነ-እድፉ ተሠጣ

እኔ እየጠበኩሽ...
ጨቅ እድሜ በቃኞች ሞቱና ሲፈርሱ
አራስ ልጃገረድ
ጥሎሽ እያስጣሉ ለትዳር ደረሱ

እኔ እየጠበኩሽ...
ስንት መፈናቀል ስንት አግኝቶ ማጣት
ስነት የድምስስ ዜና አእላፍ መገርጣት

እኔስ ብትይ ሆዴ...
አንቺ እየናፈቅሽኝ አንድ ያልሆንኩት የለም
በዚ ሀሉ መሀል
ምጠብቅሽ አንቺ
ያ'ገሬ ትንሳኤ
ፆታሽ ግልፅ አይደለም!


@dadayle27
1.7K views01:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 04:49:03 የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም በፋሺስት ኢጣሊያ በግፍ የተጨፈጨፉ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት ሲታወሱ......

#ታሪክን_ወደኋላ

የካቲት 12 ቀን በኢትዮጵያ ታሪክ የተለየ ቀን ነው፡፡ የኢጣሊያዋ ኔፕልስ ግዛት ልዑል ልጅ መውለዱን ለመዘከር ግራዚያኒ በዚህ ቀን የአዲስ አበባን ደሃዎች ሰብስቦ ለመመጽወት ባደረገው ጥሪ መሰረት ከ 3ሺ የሚበልጡ አቅመ ደካሞች በጥዋቱ በ 6 ኪሎው ቤተመንግስት ተገኝተዋል፡፡ በዚህ ቀን ኢትዮጵያውያን ጥቃት ሊያደርሱ ይችላሉ የሚለው መረጃ እስከ ሮም በመሰማቱ የቤተመንግስቱ ውስጥና ዙሪያ መትረየስ በታጠቁ ልዩ ወታደሮች እንዲጠበቅ ተደርጓል፡፡ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ይህንን ጠንካራ ጥበቃ አልፈው ውስጥ ገብተዋል፡፡

ከቀኑ ለ6 ሩብ ጉዳይ አካባቢ ሲሆን ከፍተኛ ፍንዳታ በቤተመንግስቱ ተሰማ፡፡ ከፍ ወዳለው የቤተመንግስቱ ደረጃ የተወረወረው ቦምብ ደግሞ ግቢውን በጩሀት አናጋው፡፡ የመጀመሪያው ቦምብ ባለመትረየስ ጠባቂውን አስወገደው፡፡ 2ኛው ቦምብ ከግራዚያኒ አጠገብ የነበረውን ምሰሶ አፈራረሰው፡፡ ግራዚያኒ ወደ ውስጥ ሲሸሽ ጀርባው፣ ትከሻውና የቀኝ እግሩን ከ350 በሚበልጥ የቦምብ ፍንጣሪ ቆሰለ፡፡ የካሜራ ባለሙያውና ወታደሮች ግራዚያኒን ከወደቀበት አንስተው በመኪና በመጫን ወደ ሆስፒታል ይዘውት በረሩ፡፡

3 ኛው ቦምብ ፖጊያሊ ፊት በመውደቅ ፍንጣሪው አቡነ ቄርሎስን ሲያቆስላቸው ጃንጥላ ያዣቸውን ደግሞ ገደለው፡፡ የኢጣሊያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ሊዮታ በቦምብ እግሩን አጣ፡፡ የፋሺስት ፓርቲ ዋና ጸሀፊና የቤተመንግስቱ ጠባቂዎች በድንጋጤ ለምጽዋት በ6 ኪሎ በተሰበሰበው ህዝብ ላይ እሩምታ በመተኮስ ከ1ሺ የሚበልጡትን ገደሉ፡፡ የጥቃቱ ዋና ፈጻሚዎች ሞገስ አስገዶምና አብርሃ ደቦጭ ከጊቢው በመውጣት ተሰወሩ፡፡

በቀጣይ ሰአታት ጥቁር ከነቴራ ለባሽ የኢጣሊያ ልዩ ወታደሮች የቴሌፎንና የፖስታ አገልግሎትን ዘጉ፡፡ ወዲያው መሃል ፒያሳ አራዳ ባለው የፋሽስት ዋና ጽ/ቤት የነበረው ጎዶ ኮርቴሌ የፋሽስት ወታደሮች ለሚቀጥሉት 3 ቀናት ኢትዮጵያውያንን እንዲጨፈጭፉ ትእዛዝ ሰጠ፡፡ በዚሁ ምሽት አዲስ አበባ የእርድ ቄራ ሆነች፡፡ ነዋሪዎቿ ቤት ከውጭ እየተቆለፈባቸው ከውጭ በሚለኮስ እሳት እንዲነዱ ተደረገ፡፡ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች የተገኙት ደግሞ እየታፈሱ በመኪና ተጭነው ተወስደው በግራዚያኒ ዋና መምሪያ ተረሸኑ፡፡ ከሚነዱት ቤቶች አምልጦ ለመውጣት እድል ያገኘውን ደግሞ የኢጣሊያ ወታደሮች ከደጅ ሆነው በጥይት ለቀሙት፡፡

የጥቃቱ አቀናባሪዎችንና አድራሾችን ለመያዝ ጥብቅ ምርመራና አሰሳ ተጀመረ፡፡ የኢጣሊያ ደህንነቶች ከምሽቱ በ2 ሰአት የአብረሃ ደቦጭን ቤት ሰብረው ሲገቡም እጀታው አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ በሆነው የኢትዮጵያ ባንዲራ ቀለማት በተቀባ ሳንጃ የኢጣሊያ ባንዲራ ተቦጫጭቆ አገኙ፡፡ በመቀጠል የሞገስና የአብርሃ ጓደኞችን ማደን ተጀመረ፡፡ አብርሃና ሞገስ ከምሽቱ 1 ሰአት አካባቢ ወደ ጀርመን ሚሽን በመሄድ ጓደኛቸው ስብሀትን በአጥር ቢያስጠሩትም ስብሀት አብሯቸው ለመሄድ ዝግጁ ስላልነበር ብቻቸውን ከተማውን ለቀው ሸሹ፡፡ ከጥቂት ሰአታት በኋላ የኢጣሊያ ወታደሮች የጀርመንን ሚሽን በመክበብ ስብሀትን እያዳፉ ወሰዱት፡፡ አርበኛ ሸዋ ረገድ ገድሌንም በማታ ወስደው በኤሌክትሪክ ንዝረት ቢያሰቃይዋትም ሚስጥር ሳታወጣ ቀረች፡፡

ቅዳሜ ጥዋት በድንጋጤ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ሲሯሯጡ የተገኙ ነዋሪችም ታፍሰው ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አጠገብ ተረሸኑ፡፡ በአሜሪካ ኤምባሲ ተሸሽገው የነበሩ በ100ዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ኤምባሲው አሳልፎ እንደሰጣቸው ኤምባሲው በር ላይ እንደ ውሻ እየተቀጠቀጡ ተገደሉ፡፡ ይህ ለአሜሪካ ህዝብ ይፋ ከሆነ በኋላ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር እና ኢትዮጵያ የሚገኘው አምባሳደር ዜናውን በማግስቱ አስተባበሉ፡፡ ምኒልክ አደባባይ አቅራቢያ ሆኖ ይህንን ግፍ ይመለከት የነበረው ወጣቱ ልጅ እምሩ ዘለቀም ከሰአታት በኋላ ቤቱን ሰብረው በገቡ የኢጣሊያ ወታደሮች ከእናቱና 2 እህቶቹ ጋር ተይዞ ታሰረ፡፡

እሁድ እለት የ3 ቀኑን ጭፍጨፋ ለማስቆም በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች የሚከተለው አዋጅ ተለጠፈ፣

“ሞሶሎኒ እንደ ፈጣሪ ሃያል ነው፡፡ ፈጣሪም ሆነ ሞሶሎኒ ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው፡፡ ሞሶሎኒ ተበሳጭቶባችሁ ነበር፡፡ አሁን ግን ቁጣው በርዷል፡፡ ወደ የቤታችሁ በመሄድ እለታዊ ተግባራችሁን ቀጥሉ፡፡”

ይሁን እንጂ ከዚህ አዋጅ በኋላም ግድያው ቀጥሎ ነበር፡፡ የበቀል ቅጣቱን ለማምለጥ ከቤታቸው ከወጡት ወደ 5ሺ የሚጠጉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ውስጥ ብዙዎቹ የአርበኞችን ትግል ተቀላቀሉ፡፡ በሁለት ቀን ተኩል በኢጣሊያ የግፍ ጭፍጨፋ የተገደሉትን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር አንዳንድ ወገኖች እስከ 30ሺ እንደሚደርስ ሲገልጹ ሌሎች ደግሞ ቁጥሩን ከ17ሺ-18ሺ ያደርሱታል፡፡

የአርበኞች ጀብዱ፣ Jeff Pearce እንደጻፈው፣ ኤፍሬም አበበ እንደተረጎመው፣ ገጽ 205-212

➻ ከታች የተቀመጡት ምስሎች በዕለቱ በህዝቡና በከተማዋ ላይ የተከናወኑት ፎቶዎች ናቸው።

ክብና ዘላለማዊ ዕረፍት ለሰማዕታት


ምንጭ ፦ ከታሪክን ወደኋላየfacebook page(ገፅ)

ላይክ እና ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ አድርሱ
1.4K views01:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ