Get Mystery Box with random crypto!

LUPET

የቴሌግራም ቻናል አርማ love_unity_peace_for_ethio — LUPET L
የቴሌግራም ቻናል አርማ love_unity_peace_for_ethio — LUPET
የሰርጥ አድራሻ: @love_unity_peace_for_ethio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.66K
የሰርጥ መግለጫ

ምን አጥተዋል
ምንስ መግዛት ፈልገዋል
ሁሉም አለ በውስጥ መስመር ይፃፉልን
@abriimaya
@afomiabri

ሰላም ለሀገራችን
ኢትዮጲያ ለዘለአለም ታፍራና ተከብራ ትኑር!

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-11-04 18:40:47 ሰበር ዜና!

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ሀገር የማፍረስ እቅዱን ለማሳካት በርካታ እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሚገኝ በደሴ ግንባር የተማረከው የሽብር ቡድኑ ሜይዴይ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ጉዕሽ ገብረ ተናገረ።

አሸባሪው ትህነግ ሀገር የማፍረስ እቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ድፍን አንድ ዓመት ተቆጥሯል። ቡድኑ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ ያሰበው እቅድ እንዳሰበው አልሆን ሲለው የትግራይን ህዝብ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰባሰብ ለዳግም የክህደት ተግባር በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት ከፍቶ ይገኛል።

የሽብር ቡድኑ ሰሞኑን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ኀይል በማሰለፍ በደሴ ግንባር ውግያ ቢከፍትም በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ሊደርስበት ችሏል።

በዚህ ግንባር ሰራዊቱ ባደረገው ዘመቻም በርካታ የጠላት ሃይልን የደመሰሰ ሲሆን በርካቶችንም ማርኳል። ከተማረኩት ውስጥም የሜይዴይ ክፍለ ጦር አዛዥ የሆነው የ64 አመቱ ኮ/ል ጉዕሽ ገብሩ ይገኝበታል።

እንደ ምርኮኛው ገለፃ የሽብር ቡድኑ ያሰማራው ሃይል ዲስፒሊን የሌለው በመሆኑ በወረራቸው አካባቢዎች በርካታ የግድያና ዘረፋ ተግባራትን አከናውኗል ።

የሽብር ቡድኑ ያሰባሰበው የሰው ሃይል ብዛት ከታጠቀው የመሳሪያ ብዛት ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ አብዛኛውን የሰው ሃይሉን በባዶ ዕጅ በማሰለፍ የጥይት ሲሳይ እያደረገው እንደሚገኝም ተናግሯል ።

በአሁኑ ሰዓት በሽብር ቡድኑ አመራሮች እብደትና ቅሌት ምክንያት የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ የሰላም እጦትና ችግር ውስጥ እንደሚገኝ የገለፀው ምርኮኛው ፣ የብሽር ቡድኑ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል ብቸኛው መፍትሄ እንደሆነም ተናግሯል

@Love_unity_peace_for_ethio
3.6K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-04 16:13:03 የዪኒቨርስቲ ምደባ !

ለመቐለ ፤ አክሱም ፤ አዲግራት ፤ ራያ እና ወልዲያ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ

ከላይ በተጠቀሱት ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና በፀጥታ ምክንያት ትምህርታችሁን መቀጠል ያልቻላችሁ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረዉን ትምህርታችሁን እንድትቀጥሉ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በወሰነው መሰረት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በጊዜያዊነት የተመደባችሁ ስለሆነ በተቀመጠዉ አድራሻ https://www.placement.ethernet.edu.et/ የተመደባችሁበትን ዩኒቨርስቲ ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የተመደባችሁበት ዩኒቨርስቲ ጥሪ ሲያደርግላችሁ ብቻ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡


ማሳሳቢያ

1. ምደባዉ እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. የነበረዉን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን ጨርሰው የወጡት ተማሪዎችን ብቻ ይመለከታል፡፡

2. ምደባዉ የተካሄደዉ መረጃዎችን በትክክል ላሰገቡ ተማሪዎች ሲሆን፣ በተጠየቀዉ መሰረት መረጃዎችን በትክክል ያላስገቡ ተማሪዎችና የኦን ላይን ፎርሙን በተለያየ ምክንያት በወቅቱ መሙላት ያልቻላችሁ ተማሪዎች ስማችሁን ኦንላይን ምደባ በሚረጋገጥበት ሶፍትዌር ላታገኙ ስለምትችሉ፣ በነበራችሁበት የትምህርት ክፍልና ዩኒቨርሲቲን መነሻ በማድረግ በዲፓርትመንት ስለተመዳባችሁ፣ የተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ፡፡

3. ተመዝግባችሁ ሳትመደቡ የቀራችሁ ተማሪዎች በቂና ግልፅ መረጃ ያላቀረባችሁ በመሆኑ ያልተመደባችሁ መሆኑን በመገንዘብ ትምህርት ክፍላችሁ የተመደበበትን ዩነቨርስቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳዉቃለን፡፡

4. ያልተመዘገባችሁ እና ቅሬታ ወይም አቤቱታ ያላችሁ ተማሪዎች በተቀመጠዉ የቴሌግራም ቦት አድራሻ(@moeplacementbot) አቤቱታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን አቤቱታዎችን በአካል የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

5. በዩኒቨርስቲዎቻችሁ ተፈቅዶላችሁ እረፍት(Withdrawal) ላይ የነበራችሁ ተማሪዎች የትምህርት ክፍላችሁ ለተመደበበት ዩኒቨርስቲ ማስረጃቻዉን አቅርባችሁ የሚታይላቸዉ ይሆናል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር
ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም

@Love_unity_peace_for_ethio
3.6K viewsedited  13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-04 16:05:22 የድል ዜና!!

በአፋር የተከፈተው የተቀናጀ የማጥቃት ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ ወደፊት ቀጥሏል፡፡ የወገን ጦር አድማሱን በማስፋት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

ዝርዝር ጉዳዩን ወታደራዊ ሚስጥር እንደመሆኑ ከመግለፅ እቆጠባለን፡፡

@Love_unity_peace_for_ethio
3.3K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-04 15:57:13
ልዩ መረጃ

በጅቡቲ ሆልሆል የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ በመሆን የህወሃት የሽብር ቡድን ሲመራና ሲያስተባብር የነበረዉ ኮ/ል ደስታ (ወዲ ሸዊት) ከጁቡቲ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል።

ግለሰቡ በትናንትናው እለት በቁጥር ሃያ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞችን አደራጅቶ ወደ ኢትዮጵያ አስርጎ ለማስገባት ሲሞክር መያዙ ተገልፆል፡፡

@Love_unity_peace_for_ethio
4.1K viewsedited  12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-04 11:10:44 ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የሉፔት ቤተሰቦች ሉፔት በአዲስ መልኩ ስራ ለመጀመር ወደናንተ ወደ ተመልካቾቹና ወደ ተከታዮቹ ለመድረስ ውጥን ይዟል::

እንደከዚህ ቀደሙ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ወደናንተ ለማድረስ ተነስተናል ስለዚህ እንደ ከዚህ ቀደሙ አጋርነታችሁን ተከታይነታቸሁ ከኛ ጋር የነበራችሁ ትስስር ይቀጥል ስንል ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን እንወዳቹዋለን

#LUPET

@Love_unity_peace_for_ethio
4.2K viewsedited  08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ