Get Mystery Box with random crypto!

ናፍቆቴ ፍቅሬ ብሶ ብሶ መላ ቅጥ ቢያሳጣኝ ድንገት ለጊዜያት ከጎንሽ ቢያርቀኝ ናፍቆቴ... ናፍቆቴ | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

ናፍቆቴ

ፍቅሬ ብሶ ብሶ መላ ቅጥ ቢያሳጣኝ
ድንገት ለጊዜያት ከጎንሽ ቢያርቀኝ
ናፍቆቴ...
ናፍቆቴ ልበልሽ
ማፍቀሬ ተሰማኝ ላንድ ቀን ብርቅሽ
ሱስ ሆነሽብኛል
አዎ ሱስ ሆነሽብኛል.....
ልቤ ከአንቺ ውጪ ሌላ መች ይመኛል
መረብ ሆኖ ፍቅርሽ አሳስሮ ይዞኛል
ባንቺ እንዴት ልጨክን ሆነሽ የኔ አካል
ናፍቆቴ አልኩሻ
መባዬ አልኩሻ
አይኔ ካንቺ ውጪ ማንንም አይሻ
ያንቺ ሳቂታነት በልቤ ተስሎ
ጀግና የነበረው ፊቴ ከሰል መስሎ
ሸሸ ተደበቀ ኸጥግ ላይ ቆመ ራሱን ከልሎ
በናፍቆትሽ ምክንያት
ንጉስ የነበርኩት ባንቺ የተነሳ አገልጋይ ቢያረጉኝ
....ጀብደኛ የነበርኩት ባሪያ እንኳን ቢያረጉኝ
አንቺን እስካገኘው ሃብታም ቢሉኝ ደሀ ጌታ ቢሉኝ ሎሌ ምንም አይሰማኝ
ናፍቆቴ.....
ናፍቆቴ ሳገኝሽ
ደስታዬን አልችልም እጅሽን ብስምሽ

በ𝐻𝑒𝑛𝑎

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye