Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ቃጠሎ ጕንጭሽ ፅጌሬዳ ሞቆት የፈነዳ ዐይንሽ የጠዋት ጨረር የበራ ማለዳ። የማትጠገቢ የስ | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

የፍቅር ቃጠሎ

ጕንጭሽ ፅጌሬዳ
ሞቆት የፈነዳ
ዐይንሽ የጠዋት ጨረር
የበራ ማለዳ።
የማትጠገቢ የስንዴ ራስ ዛላ አገዳ ጥንቅሽ
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ
ቆንጆ ነሽ አንቺዬ
እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ በአካላቴ
ሆነሻል ሙቀቴ፤ ሆነሻል ሕይወቴ።
የጋለው ትንፋሽሽ
የሞቀው ምላስሽ
ማርኮኝ በከንፈርሽ
እጄን ሰጥቻለሁ።
እስረኛ ሆኛለሁ።
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ
ልቤን አስፈራርቶ ፣ ትኩሳት አምጥቶ።
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ
እቀፊኝ ለቀዝቅዝ ፣ ንከሽኝ ልደንዝዝ።

ገ/ክርስቶስ ደስታ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye