Get Mystery Box with random crypto!

ብታውቂ ስትስቂ! ጠፈርን እንደምታደምቂ መንፈስን ካ'ዚም እስራት እንደምታላቅቂ ብታውቂ! ስትስሚ! | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

ብታውቂ

ስትስቂ!
ጠፈርን እንደምታደምቂ
መንፈስን ካ'ዚም እስራት
እንደምታላቅቂ
ብታውቂ!
ስትስሚ!
አጥንት እንደምታለመልሚ
ታማሚ ልብ እንደምታክሚ
ብታውቂ!
ስታወሪ!
ዱዳ እንደምታናግሪ
መነኩሴውን ከሱባኤ፣
ፈላስፋውን ከጉባኤ
እንደምትጠሪ
ብታውቂ!
እንኳንስ በ'ኔ ልትስቂ
ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ
አይሽ ነበር ስትማቅቂ።

በእውቀቱ ስዩም

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye