Get Mystery Box with random crypto!

የእያደር ሀገር ህዝቦች እያደር ይፋጃል፣የጉድ ሀገር ገንፎ እያደር ውድ ነው፣የጉድ ሀገር ክትፎ እ | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

የእያደር ሀገር ህዝቦች

እያደር ይፋጃል፣የጉድ ሀገር ገንፎ
እያደር ውድ ነው፣የጉድ ሀገር ክትፎ
እያደር ይበላል፣የጉድ ሀገር ቴሌ
የጉድ ሀገር ተስፋ፣ይነጋል ነው ሁሌ
ጉድ አንድ ሰሞን ነው፣የጉድ ሀገር ተረት
ለአንዲት ቀን እንኳን፣ጉድ አልቻለም መቅረት
እያደር እንቧ ነው፣የጉድ ሀገር በረት

የጉድ ሀገር ወሬ፣እያደር ሰቀቀን
የጉድ ሀገር ንጋት፣እያደር አንድ ቀን
እያደር እያደር
አድሮ ቃሪያ መሆን፣ወይም ከርሞ ጥጃ
የጉድ ሀገር ምላሽ፣እያደር እኔንጃ
የጉድ ሀገር ፍርሀት፣እያደር ጠብመንጃ

በላይ በቀለ ወያ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye