Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለኵልክሙ ኦ! ፍቁራነ ግእዝ ➙እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት በአካል የግእዝ ትምህርትን ከደረ | ልሳነ ቀደምት

ሰላም ለኵልክሙ ኦ! ፍቁራነ ግእዝ

➙እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት በአካል የግእዝ ትምህርትን ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ ሦስት በርካታ ተማሪዎችን ለማፍራት ተችሏል፡፡ቢሆንም ግን ዘመኑን ከመዋጀት አንጻርና ግእዝ ቋንቋን ለሁሉም ከማዳረስ አንጻር በቂ ሆኖ አልተገኘም። ስለዚህ ዘመን በወለደው ቴክኖሎጅ ማስተማር አስፈላጊ መሆኑ ተረጋግጦ ማስተማር ከተጀመረ ሰንበትበት ብሏል።

➙በመሆኑም ግእዝ ለጀማሪዎች በሚል የቴሌግራም ቻናል አንደኛ ዙርና ሁለተኛ ዙር ተመዝግበው በመማር ላይ ሲሆኑ ለሦስተኛ ዙር ለማስተማር ደግሞ ይህ ቻናል ተከፍቷል።

➙ስለዚህ ማነኛውም ግእዝ ቋንቋን ለመማር ፍላጎት ያለው ሁሉ በዚህ ቻናል መመዝገብና መማር ይችላል። ፈጥኖ መመዝገብ ብልህነት ነው። ለበለጠ ማብራሪያ ከምዝገባ በኋላ የምንሰጥ መሆኑን ስንገልጽላችሁ በአክብሮት ነው።
የሚቀጥለውን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ ይቻላል።

ወደ ቻናሉ መግቢያው ሊንክ

@HaileyesusMengist

መ/ር ኃ/ኢየሱስ መንግሥት
@HaileyesusMengist
ሸር በማድረግ ይተባበሩ