Get Mystery Box with random crypto!

ፕሬዝዳንት ፑቲን በሩሲያ በተያዘችው የዩክሬኗ ማሪፖል ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ!! ፕሬዝዳንት ቭላ | ልዩ መረጃ ®

ፕሬዝዳንት ፑቲን በሩሲያ በተያዘችው የዩክሬኗ ማሪፖል ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ!!

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሩሲያ በተያዘችው የዩክሬኗ ማሪዮፖል ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል።

የሩሲያ ብሄራዊ ሚዲያ እንደዘገበው ጉብኝቱ የመጣው ፑቲን ክሬሚያ ከዩክሬን ተገንጥላ ሩሲያን የተቀላቀለችቀትን ዘጠነኛ ዓመት ለማክበር ባደረጉት ድንገተኛ ጉብኝት ማግስት ነው።

ጉብኝቱ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ ካወጣ ከሁለት ቀናት በኋላ የተደረገም ነ። ፑቲን በሄሊኮፕተር በመብረር ወደ ማሪፖል እንደደረሱ የሩሲያ የዜና ምንጮች ክሬምሊንን ጠቅሰው ዘግበዋል። ፑቲን ለአንድ ዓመት በዘለቀው ጦርነት ወደ ጦር ግንባር ሲቀርቡ የመጀመሪያ ነውም ተብሏል።

ፑቲን መኪና እያሽከረከሩ በከተማዋ በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች እየተዘዋወሩ ነዋሪዎችን አነጋግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የወታደሮቻቸውን ሞራል ለማሳደግ እና የጦር ስልታቸውን ለማጎልበት ወደ ጦር ሜዳው ብዙ ጉዜ ተመላልሰዋል።

ፑቲን ግን ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ "ልዩ ወታደራዊ ተልዕኮ" በምትለው ጦርነት በዋነኛነት በክሬምሊን ውስጥ ቆይተዋል።ጦርነቱ 13ኛ ወሩን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ኪየቭና አጋሮቿ "የመሬት ዘረፋ" ይሉታል። ጦርነቱ በዩክሬን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለ ነው።