Get Mystery Box with random crypto!

አብነት ገብረመስቀል በአላሙዲ ላይ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ 'ስለሚፈለግ ከሃገር ሸሽቶ ጠፍቷል | ልዩ መረጃ ®

አብነት ገብረመስቀል በአላሙዲ ላይ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ

"ስለሚፈለግ ከሃገር ሸሽቶ ጠፍቷል" በሚል በፍርድ ቤት የተነገረበት የአላሙዲ የረዥም ጊዜ ሠራተኛ አብነት ገብረመስቀል፤ ከሼኩ ጋር በገባበት ውዝግብ ከአሜሪካ ሆኖ በጠበቆች አማካኝነት በፍርድ ቤት ይግባኝ ቢጠይቅም ውድቅ እንደተደረገበት ዘ-ሐበሻ እጅ የገባው የፍርድ ቤት ሠነድ አመልክቷል።
የቀድሞ የአዲስ አበባ ከንቲባ እና የማዕድን ሚኒስትር ከነበሩት ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአሜሪካ ተቃውሞ ሲያጋጥማቸው፤ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ካፌ ውስጥ ተቀምጦ በቪድዮ የታየው አብነት በቅርቡ ፍርድ ቤት ከቦሌ ታወርስ ጋር በተያያዘ ከአላሙዲ ጋር በገባው ውዝግብ ከስራ አስኪያጅነት እንዲነሳ እና በ እጁ ያለውን የድርጅቱን ዶኩመንት እንዲያስረክብ ፈርዶበት እንደነበር ዘግበን ነበር። ሆኖም አብነት ከአሜሪካ ሆኖ በጠበቃው አማካኝነት ፍርድ ቤቱን ይገባኝ ቢጠይቅም፤ ፍርድ ቤቱ ከሳሽ አላሙዲ ወይም ጠበቆቻቸው መቅረብ ሳያስፈልጋቸው የአብነትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎበታል።