Get Mystery Box with random crypto!

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘመን ተሻጋሪ ግ | ልዩ መረጃ ®

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነት እንደምታጠናክር ተናገሩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጡ ነው።
በመግለጫቸውም÷ በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት ላይ በሁለቱም ወገን የተጠናከረ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አንስተዋል።
ዘላቂ ሰላም ለማምጣትም የሽግግር ፍትህን አጠናክሮ መተግበር እና ሃገራዊ ምክክር ማከናወን ተገቢ መሆኑን አመላክተዋል፡፡