Get Mystery Box with random crypto!

#MoE የአቅም ማሻሻያ  (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ ዛሬ ያበቃ | ልዩ መረጃ ®

#MoE

የአቅም ማሻሻያ  (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ ዛሬ ያበቃል።

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫቸውን በየት/ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እንዲያስተካክሉ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዛሬ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ያበቃል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ ናቸው።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከዚህ ቀደም 50 % እና ከዛ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ምደባ ያካሄደ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት የሚከታተሉ ተማሪዎችን ምደባ ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል።

@leyumerga