Get Mystery Box with random crypto!

በጎንደር ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ በቀዳማዊ | ልዩ መረጃ ®

በጎንደር ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ

በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በጎንደር ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዳቦ እና የዱቄት ፋብሪካ ዛሬ ተመርቆ ስራ ጀመረ፡፡

ፋብሪካውን መርቀው የከፈቱት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የፌዴሬሽን ምክር አቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ፋብሪካው በቀን 400 ሺሕ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን ለጎንደር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ዳቦ ማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ ፋብሪካው 160 ለሚሆኑ ስራ አጥ ወገኖች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው በዘመናዊ የዳቦ ማምረቻ ማሽኖች የተደራጀ ከመሆኑም በላይ የዳቦ ማመላለሻ ተሽከርካሪ የተመደበለት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በከተማው አማካኝ ቦታዎች በተቋቋሙ የዳቦ መሸጫ ሱቆች አማካኝነት የዳቦ ስርጭት በየእለቱ ለከተማው ነዋሪዎች ተደራሽ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡

ለፋብሪካው ግንባታ የከተማ አስተዳደሩ 11 ሺሕ 500 ካሬ ሜትር ቦታ በነጻ የሰጠ ሲሆን ግንባታውንም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉም ተገልጿል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርአቱ ላይ ሚኒስትሮች፣ የአማራ ክልልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የከተማው ነዋሪዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@leyumerga