Get Mystery Box with random crypto!

#JawarMohammed የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (OFC) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመ | ልዩ መረጃ ®

#JawarMohammed

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (OFC) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ የኦሮሚያን የሰላም ጉዳይ በተመለከተ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያሰፈሩት ሃሳብ ፦

" የኦሮሚያ የሰላም ጉዳይ መስመር እየያዘ ይመስላል።

የሰላም ሂደቱ ከሽማግሌዎች አልፏል ፤ ይህ ዕድል በ2011 ዓ.ም ላይ ያመለጠ ነው።

መንግስት በውጪ አደራዳሪዎች ላይ ያለውን ጥርጣሬ ማንሳት አለበት ፤ ለቴክኒክ፣ ለሎጅስቲክስ እንዲሁም ለህጋዊና ለጋራ ትምምን ሲባል የውጭ አካላት ድርድሩን እንዲመሩት ያስፈልጋል።

የፖለቲካ አመራሩ፣ ምሁራኑ እና አጠቃላይ ህብረተሰቡ ለሁለቱም ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ለዚህ ተስፋ በፍጥነት ተግባራዊ መሆን የበኩሉን መወጣት አለበት።

በአሁን ሰዓት ሰላምን ከማስፈን እና ህዝባችንን ከከባድ ጥፋት ከማዳን የተሻለ ነገር የለም። "

@leyumerga