Get Mystery Box with random crypto!

ትላንት ምሽት ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች። እጅግ አስከፊው የመሬት መንቀጥቀጥ (7.8) ከተ | ልዩ መረጃ ®

ትላንት ምሽት ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች።

እጅግ አስከፊው የመሬት መንቀጥቀጥ (7.8) ከተከሰተ ከሁለት ሳምንት በኃላ ቱርክ ትላንት ምሽት በሬክተር ስኬል መለኪያ 6.3 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቷ ተሰምቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የመታው አካባቢ ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከባድ ጉዳት ባጋጠመው በሃታይ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ደቡባዊዋ ሳማንዳግ ከተማ አቅራቢያ ነው ተብሏል።

አሁን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክ ውስጥ እስካሁን የሀገሪቱ መንግስት ባስታወቀው 3 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከ200 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በሰሜን ምዕራብ #ሶሪያ ውስጥ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን እስካሁን በታወቀው 130 ሰዎች ተጎድተዋል።

ምናልባት በአዲሱ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጨማሪ ተጎጂዎች ይኖሩ ይሆን እንደሆነ ተብሎ ፍለጋዎች መቀጠላቸው ታውቋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው በሬክተር መለኪያ 7.8 በተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርክ እና በሶሪያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ47,000 አልፏል።

@leyumerga